የኦሕዴድ ሊቀመንበር ሙክታር ከድርና ምክትሏ ኣስቴር ማሞ ከድርጅቱ ተባረሩ። ኦሮሚያ በጊዜያዊ ርእሰ መስተዳደር መመራት ጀምራለች።

muktar-2ራሳቸውን ከስልጣን ኣሰናብተዋል በሚል ሕወሓታዊ ሽፋን የኦሕዴድ ሊቀመንበር ሙክታር ከድርና ምክትሏ ኣስቴር ማሞ ከድርጅቱ ተባለው በምትካቸው ሌሎች መሾማቸው ተሰምቷል።

በዚህም መሰረት በምትካቸው በወያኔያዊ መተካካት ተኮር ባደረገ መጠጋጋት የተደረገ ሲሆን ለማ መገርሳ ሊቀመንበር (ዶክተር)ወርቅነህ ገበየሁ ምክትል ሆነሁ በሕወሓት ተሹመዋል። ኦሮሚያ በጊዜያዊ ርእሰ መስተዳደር መመራት ጀምራለች።

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

የሙክታርን መንበር የተረከበው ለማ መገርሳ የሚባል ስም እስከዛሬዋ ድረስ ሰምቼ ስለማላውቅ ይሄ “ፀጉረ ልውጥ ” ሰው ማን ይሆን የሚለውን ሳጠያይቅ የጸጥታ ሀላፊ ( ደህንነት) የነበረ ነው አሉ ። አሃ! 🙂 ለካ ባለጭምብል ደህንነት ስለነበር ነው የተሰወረብኝ ።
አሁን የህውሃት መፃኢ አላማ ምን እንደሆነ ብዥታው ጠራልኝ ።
ወርቅነህ ገበየሁ የፌ/ፖ/ኮ ከመሆኑም በፊት በክንፈ ገ/ መድህን ከዛም በኋላ በአሁኑ ጌታቸው አሰፋ በሚመራው ደህንነት ሰራተኛ ነበር ። ወርቅነህ ከደህንነት ነው ወደ ፌደራል ፖሊስ አዛዥነት የተሸጋገረው ። አሁን የሚቀጥለው የህወሃት እቅድ ምን እንደሆነ አመላካች ነው። ኦሮሚያ ከዚህ በኋላ የምትመራው በቀጥታ በጌታቸው አሰፋ የደህንነት ቢሮ ነው ማለት ነው። ይሄ የሚያመለክተው ህውሃት ምን ያክል እብደት ውስጥ እንዳለና ነገሮች ከቁጥጥሩ ውጭ እንደወጡና በደህንነት አገዛዝ የተዝረከረከውን ለመመለስ እየታገለ እንደሆነ ነው። ለማንኛውም ብርጭቆ ከነቃ አይሆንም እቃ ነውና ። የህውሃት ብርጭቆ በመላው አገሪቱ ተሰነጣጥቋል መልሶ እቃ የመሆን እድሉ ዜሮ ነው።
ህወሓት የኦህዴድ አመራሮችን የመቀያየር መብት አለው። የኦሮሞን ህዝብ አላማ መቀየር ግን አይችልም።

 Hailu bitaniya

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.