የእምነት ክህደት ቃል በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት [አብራሃም ሰሎሞን]

habtamu-4
ሀብታሙ አያሌው-, የሽዋስ አሰፋ, – ዳንኤል ሽበሺ, – ….

አለቱ መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም ነበር። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛ ምድብ ችሎት ነበርን። የቀረብነው ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላችንን እንድንሰጥ ተጠየቅንና
በየተራ እየመለሰን ነበር። ለትዝታ ያህል ይሀው እንብቡት።

ዳኛ ሽለመው ፦ መዝገቡ ዛሬ የተቀጠረው የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመጠየቅ ነው። ተከሳሾች በየተረ ስንጠይቃችሁ ትመለሳለችሁ።
የተጠቀሰውን ወንጀል ፈፅመሀል ? ወይስ አልፈፅምክም??

1. ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው፦ በክሱ ላይ የተመለከተውን ድርጊት እንዳልፈፅምኩ እንኳን እኔ ከሳሾቼም በደንብ ያውቁታል። ከሳሾቼ እኔ ድርጊቱን የመፈፅም ፍላጎትም ሀሳብም እንደሌለኝ ይውቃሉ።

2. ተከሳሽ ዳንኤል ሽበሺ ፦ እኔ ሽብርን የሰማሁት ከአልቃይዳው መሪ ከኦሳማ ቢላደን እና ከመለስ ዜናዊ ነው። እኔ አሽባሪ አይደለሁም። ሀሳብም ፍላጎቱም የለኝም። እምነትና ባህሌም አይፈቅድልኝም። ኢህአዲግ ነው አሽባሪ።

3. ተከሳሽ አብርሀ ደስታ ፦ አሽባሪ ማለት የፓለቲካም ሆነ ሌላ አላማ ይዞ ሰላማዊ ዜጎችን በማሸበር ለመስራት የሚፈልግ ነው። ኢትዬጽያ ውስጥ ብቸኛው አሸባሪ ህወሀት/ኢህአዲግ ነው። እኔ ደግሞ የዚህ ድርጅት ተቃዋሚ ነኝ።

4. ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ ፦ ክሱ ቅንብር ነው። ዳኞቹም ምንም ነፃነት አይታይባችሁም። ይህ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ነው የሚመስለው። ለመጨረሻ ጊዜ ስለሆነ እንዳታቆርጡኝ?
አቶ የሽዋስ ያቁሙ ብያለው ፥ ያቁሙ እያልን ነው ፥ በቃ ዝም በል። ስርአት ያዝ!!!!

5. ተከሳሽ ዬናታን ወልዴ ፦ የተዘጋጅብኝን ክስ ያለፍቃዴ እንድተውን እየተገደድኩ ነው።

6. ተከሳሽ አብርሀም ሰለሞን ፦ የተቀናበረ ክስ ላይ ምንም ማለት አይቻልም። ንፁህ ሰው ነኝ።

7. ተከሳሽ ባህሩ ደጉ ፦ ባህሉንና ፈጣሪውን ከሚያከብር ማህበረሰብ ወጥቼ አሸባሪ ልሆን አልችልም።

ሁሉም ተከሳሾች ክደው ቃል በመስጠታቸው ምስክር ለግንቦት 13 ፥ 14 ፥ 15 ይቅረብ። ስለዚህ የትኛው የእምነት ክህደት ቃል ገረማችሁ ? እኔ የዳኒ መልስ ነው የገረመኝ ። የናንተስ ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.