በጎንደር ከተማ የተለያዩ ንብረቶችን ለማቃጠል ከትግራይ የተላኩ ወጣቶች የተያዙ መሆናቸው ታውቋል

gonder-5678-satenaw-newsረቡዕ መስከረም 11 ቀን 2009 ዓም. ከሰዓት በኋላ የፒያሳ ሱቆችን ለማቃጥል ተልእኮ የነበራቸው አራት ግለሰቦች ለማቀጣጠያ ሊጠቁሙበት ከነበረ የነዳጅ እቃ ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል። በተደረገላችው ምርመራ ሱቆችን ለማቃጠል ከትግራይ ተልከው የመጡ መሆናቸውንና ከእነሱም ጋር ከአምሳ የሚበልጡ ወጣቶች ተልከው በከተማዋ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ዛሬ ጠዋት አንዲት ወጣት ከ በቀበሌ 12 የአውቶቡስ ማቆሚያ አውቶቡሶችን ለማቃጥል ስትሞክር ከማቃጠያ ቁሳቁሶቿ ጋር የተያዘች መሆኗ ታውቋል። በተጨማሪ የገበያ ቦታዎችን ለማቃጠል ተልእኮ የነበረው አንድ ሌላ ግለሰብ ሆቴል ሲያፈላልግ የተያዘ ሲሆን በኪሱ አራት የተለያዩ መታወቂያዎች ተገኝቶበታል። እነዚህ ግለሰቦች በወያኔ አገዛዝ መላካቸው አያጠራጥምር ያሉ ወገኖች የሰዎቹ ተልእኮ ቀደም ብሎ ቅዳሜ ገበያ የተቃጠለው በወያኔ ተላላኪዎች የተድረገ መሆኑን ያረጋግጣል ብለዋል ። ወያኔ ይህን የጥፋት የሚከተለው አንድም የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ሲሆን በሌላ በኩል በአማራውና በትግራዩ ብሔረሰቦች መካከል ቅራኔና ክፍፍል በመፍጠር የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም መሆኑ ተድርሶበታል። በተመሳሳይ ዜና ከጥቂት ጊዜ በፊት ከመተማ በአማራው ሕዝብ ተባረው ወደ ሱዳን ገብተዋል የተባሉት የትግራይ ብሔረሰብ አባላት ከመተማ ወደ ሱዳን ያደረጉት
ጉዞ በወያኔ አገዛዝ የተቀነባበርና የተዘጋጀ መሆኑን በአካባቢ የነበሩ የተራዶ ድርጅቶች ያጋለጡ መሆናቸውን አንዳንድ የዜና ምንጮች ተናግረዋል። የወያኔ ባለስልጣኖች ይህን ቁማር የተጫወጡት በዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ የዘር ፍጅት እንደተካሄደባቸው አስመስለው ድጋፍ ትብብር ለማግኘት መሆኑ ይነገራል።
#በተያያዘ ዜና የጎንደር አገር ስብከት በወያኔ አገዛዝ ትዕዛዝ ዘንድሮ የመስቀል በዓል በጎንደር ከተማ የመስቀል አደባባይ እንዳይከበር መመሪያ ያስተላለፈ መሆኑ ታውቋል። መድረኩ ከፍተኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴ መናኸሪያ ሊሆን ይችላል ከሚል ስጋት የወያኔ አገዛዝ ትእዛዙን ለቤተ ክህነት ያስተላለፈ ሲሆን የወያኔ ደጋፊና ተባባሪ የሆነው ቤት ክህነትም ትእዛዙን በመደገፍ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሯሯጠ ነው።
#የወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ኃይለማርያም ደሳለኝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመታዊ ጉባኤ ላይ ባደረገው ንግግር አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመፍጠርም ሆነ ለማባባስ ምክንያቶቹ የማህበረሰብ የመገናኚያ አውታሮች ናችው የሚል አስቂኝ ንግግር ተናግሯል። ኃይለማሪያ በንግግሩ አሸባሪዎች በማህበረሰባዊ መገናኛዎች እውነት ያልሆነ አሉባልታ እያስወሩና ህዝብን እየቀሰቀሱ ሁከት ይፈጥራሉ ብሏል። ለ 25 ዓመታት በዘረኛና ከፋፋይ አገዛዝ ነጻነትና መብቱ ተገድቦ፤ ተጨቁኖና ተረግጦ የኖር ሕዝቦ ብሶቱ ገንፍሎ በከፍተኛ ስሜት ያደረገው እንቅስቃሴ መሆኑ እየታወቀ ኃይለማርያም ጓደኞቹ ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ የማህበረሰብ መገናኚያን እንደምክንያት መውሰዳቸው ራሳቸውን አስገመቱ እንጅ ያስገኙት ፋይዳ የለም ሲሉ ታዛቢዎች ይተቻሉ።
#የወያኔ አገዛዝ አስመርሯቸው ከኢትዮጵያ በብዛት የሚወጡትን ስደተኞችን ለመቀነስና እንዲሁም የወያኔን እድሜ ለማራዘም የአውሮፓው ህብረት 500 ሚሊዮን ዶላር ለወያኔ የሰጠ መሆኑ ተነገሯል። ከዚሁ ውስጥ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው በብድር መልክ የተሰጠ እንዲሁም የተቀረው በስጦታ መሆኑ የታወቀ ሲሆን በገንዘቡ 100 ሺ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ መስኮች ይከፈቱበታል የሚል መግለጫም ተሰጥቷል። በአገሪቱ ውስጥ ላሉ በብዙ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ስራ አጦች ይህ ቋት የማይሞላ መሆኑ ከመታወቁም በላይ ይከፍታል በላይ የአገሪቱ ውስብስብ ችግሮች ተፈተው ከአገር ውስጥ ስደተኛ መውጣት ሊቀንስ የሚችለው የወያኔ አገዛዝ ሲወገድና ለሕዝብ ጥቅም የቆመ ስርዓት ሲመሰረት ብቻ ነው የሚል አስተያየት እየተሰጠ ነው።
#በትናንተናው ዕለት ከግብጽ ተነስታ ወደ አውሮፓ ስትጓዝ በሰጠመችው ጀልባ ምክንያት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ተነግሯል። ጀልባዋ 550 ስደተኞችን አሳፍራ የነበረ ሲሆን እስከዛሬ ድረስ በተደረገው ጥረት 163 ሰዎችን ብቻ ለማዳን የተቻለ መሆኑንና 46 አስከሬኖች የተገኙ መሆናችውን የግብጽ ባለስልጣኖች ተናግረዋል። የተቀሩት ከሶስት መቶ አምሳ በላይ የሚሆኑት ስደተቾች ዕጣ ምን እንደሆነ እስከአሁን አልታወቀም። በህይወት ከተረፉት ውስጥ 100 በላይ የሚሆኑት የግብጽ ተወላጆች ሲሆኑ ሴቶችና ህጽናት የሚገኙበት መሆኑ ታውቋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በሚዲትራኒያን ባህር ላይ ሰጥመው የሞቱት ወደ 10 ሺ የሚገመቱ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዳሉበት ይታወቃል።
Source – #FinoteDemocracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.