የራሷን እያረረባት የሰው ታማስላለች [ከ አካደር ኢብራሂም]

የአፋር ክልል እና የሶማሌ ክልል መንግስት ለበለፀገች ታላቋ ትግራይ የገንዘብ እርዳታ አደረጉ።

አካደር ኢብራሂም

ከመተማ ተፈናቅለዋል ለተባሉት የትግራይ ተወላጆች በሚል ባለፈው የሶማሌ ክልል 10 ሚሊዮን ብር መስጠቱን የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የአፋር  ክልል መንግስት 10.2 ሚሊዮን ብር ሰጥተዋል።

ጥያቄው እርዳታ የሚሰጠው ማነው የሚቀበለውስ ማነው ?

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚባለው እራሱ ወያኔ መሆኑን ማንም ሰው ማወቅ አለብት።

የአፋር ክልል መንግስት የሚባለው ከወያኔ ጋር ከጫካ የመጡ 3 ሰዎች ናቸው።

እነዚህ ሰዎች ዛሬ ምንም አደረጉ ምን ከህወሀት ትዕዛዝ ውጭ ምንም ነገር እንደማይደርጉ የሚታወቅ ሆኖ እያለ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብን ያለ ህዝባዊ ይሁንታ ለ 25 አመታት እየመራ ያለው ይህ የወያኔ ቡድን ዛሬ የአፋር ሽማግለዎችን በማስገደድ የህዝብን ገንዘብ ተሸክመው ለህወሀት እንዲያሰርክቡ አድረገዋል።

ለነገሩ የአፋር ገንዘብ ለህወሀት ተሰጠ መባሉን ለኔ ብዙም አሰደናቂ ነገር አይደለም።

ምክንያቱም በአፋር ክልል ያለው የተፈጥሮ ሀብት አብዛኛው የሚቆጣጠሩት የህወሀት አባላትና ቤተሰቦቻቸው ናቸው።

ለምሳሌ ከቀደሞው የትግራይ ክልል ፕረዝደንት ጸጋይ በርሄ ጀምሮ ብዙ የህወሀት መሪዎች በአፋር አፍዴራ የጨው መሬት እንዳላቸው ይታወቃል።

የዚህ የአፍዴራ የጨው ሀብትን በኢንቨስተርንት የተቆጣጣሩት ደግሞ የህወሀት አባላትና ቤተሰቦቻቸው ናቸው።

ግን ዛሬ የዚህ ፖለቲካዊ ዕርዳታ ይበልጥ ያስቆጣን በይፋ በማወጅ ያለ ምንም ህፍረት ሰላደረጉት ይመስለኛል።

በ 2014 እ.እ.አ በአፋር ክልል በአሚባራ ወረዳ ክፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ደርሶ 36 ሺ ህዝብ ከቀዬቸው ተፈናቅለው ነበረ።

ባለፈው አመት ደግሞ በመላው አገሪቱ የደረሰውና በተለይም በግብሪና የሚተዳደረውን የአፋር ህዝብን በክፉኛ የጎዳው ድርቅ የነበረው ሁኔታ ሁላችንም እናስታውሳለን።

afar-121

የአየር መዛባት ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በአፋር ክልል ብቻ ከ30 ሰዎች በላይ ሞተዋል።

በአፋር ክልል በየቦታው ያለው የውሀ ችግር ተንትነን አንጨርሸውም።

ታዲያ ያኔ ለህዝብ ከውጭ የሚመጣው ዕርዳታ ሰርቆ ሲሽት የነበረው የአፋር ክልል መንግስት ተብዬዎች ዛሬ ለግራይ ተወላጆች ይህን ያህል ገንዘብ ሲሰጥ ምን ይባላል ?

እነዚህ ተፈናቀሉ የሚባሉት የትግራይ ተወላጆች ከየት ወደ የት ነው የተፈንቀሉት ?

ማነው ያፈናቅላቸው ?

እነዚህ ሰዎች አብዛኛው በወያኔ የበላይነት ተጠቅመው በየክልሎች ንግድ ላይ የነበሩ ባለ ሀብቶች ሲሆኑ ማንም የትግራይ ተወላጆች በመሆናቸው ያፋናቀላቸው ባይኖርም ሲሰሩበት የነበረው ክልሎች ህዝቡ እያሳየ ያለው እንቢተኝነት በመፍራት ወደ ክልላቸው የተመለሱ ሰዎች ናቸው።

afar-122

ቆይ በትክክል እርዳታ የምያስፍልጋቸው ኢንኳን ቢሆን ማን ማንን ነው መርዳት ያለበት ?

የትግራይ ክልል መንግስት ራሱ በጀት የለውም እንዴ ?

በእርግጥ ይህ እርዳታ ለትግራይ ህዝብም ቢሆን አይጠቅምም።

ምናልባት ለህወሀት የፖለቲካ ትርፍ፣ ማለትም ህዝብ ውስጥ ልዩነትና መቀያየም ለመፍጠር ታሲቦ ካልሆነ።

ይህ ጉዳይ ብዙ አፋሮችን እንዳስቆጣ አውቃለሁ፣ ግን ደግሞ እኛም በቃን ማለት አለብን።

መነሳት አለብን፣ መብታችን ማስከበር አለብን!

ወያኔ አላማው እኔ ከሞትኩኝ በኃላ  ሳር አይብቀል አይነት ህዝቦችን አባልቶ መሞት ነውና ልብ እንበል።

ኢትዮጺያ ትቅደም