ምኒልክ ጡት ቆርጠዋል ብለው ለማስጠላት ሀውልት ያቆሙ አካላት በድርጊታቸው ማፈርና ያንን አሳፋሪ ሀውልትም ማፍረስ ይገባቸዋል

anole1-satenaw-news”ምኒልክ ጡት ቆርጠዋል ብለው ለማስጠላት ሀውልት ያቆሙ አካላት በድርጊታቸው ማፈርና ያንን አሳፋሪ ሀውልትም ማፍረስ ይገባቸዋል… አብዛኞቹ የአፄ ምኒልክ ወታደሮች ክርስቲያኖች ነበሩ። እነዚያ ወታደሮች የገዛ ሀገራቸውን የተከበሩ ሴቶች ጡት ቆረጡ ማለት ፍፁም የፈጠራ ወሬና ለሰሚው ግራ ነው። እኔ ባደረኩት ምርምር ይህን ድርጊት የሚያረጋግጥ አንድም ማስረጃ አላገኘሁም። ርካሽ ጥላቻን ለመንዛት ይህን ለህዝብ ምንም ጥቅም የሌለውን ሀውልት ያቆሙ ፖለቲከኞች፣ ይልቅስ ለህዝባቸው የሚፈይዱ ፋብሪካዎች ቢያቆሙላቸው ከድህነት ይላቀቃሉ። ይህን የጥላቻ ሀውልት ነቅለው ፋይዳ ያላቸው ፋብሪካዎች ለህዝባቸው እንዲተክሉላቸው በዚህ አጋጣሚ እመክራቸዋለሁ። ሌላው ስለ አፄ ምኒልክ የተነዛው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ‘5 ሚሊዮን ኦሮሞዎችን ፈጁ’ የሚል ነው። ይህም ከእውነት የራቀ ነው። በዚያን ጊዜ የነበረው ጠቅላላ የኢትዮጵያ ህዝብ 10 ሚሊዮን ቢሆን ነው። 5 ሚሊዮኑ ከተገደለ ምን ሰው ተረፈ? ደግሞስ ጀግናው የኦሮሞ ህዝብ ዝም ብሎ አንገቱን ለእርድ የሚጋብዝ ነበር እንዴ? ቢያንስ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት አይዋጋም ነበር እንዴ? የኦሮሞ ህዝብ የማይበገር ጦረኛና ጀግና ስለነበር ተዋግቶ ለራሱ ይመክታል፤ እንዲሁም ይገድላል እንጂ በዝምታ እንደ በግ አይታረድም ነበር። ስለዚህ “የአፄ ምኒልክ ሠራዊት 5 ሚሊዮን ኦሮሞዎችን ፈጅተዋል” የሚለው ወሬም ለርካሽ ፕሮፓጋንዳ የተተረተ ነው!”
ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.