ከአቢዮቱ ደመራ የአራት ኪሎው ይበልጣል ለምን አልከኝ ? [በቶማስ ሰብስቤ]

tom12  የ2009 የደመራ በዓል በብዙ ቤት ሀዘን ላይ የመጣ ነው።አምና ቢያንስ ሰባት መቶ እናቶች ዳመራ ሲያበሩ አጠገቦቻቸው ያሉ ልጆቻቸው ከአንድ አመት በሃላ ዛሬ የሉም።ብዙ ሚሊየኖች ደግሞ በጭቆና፣በአንባገንንነት እና በፍትህ እጦት ተሰቃይተዋል።በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ልጆቻቸው እስር ቤት ታሰረው በዓሉን አላዮትም።በዚህ ሰሜት ውስጥ ላለች ሀገር ከአቢዮት ከታየው ዳመራ ይልቅ የአራት ኪሎው እውነትን ይናገራል።

ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም እውነት ሰለሆነ ብዙ ተከታይ አግኝተው።ለዛውም ጨካኝ ወታደር ፊት ዛሬ አራት ኪሎ ላይ እውነት አሳዮ።ሀዘናን ላይ ሰለሆነች ኢትዮጵያ ጥቁር ቲ―ሸርታቸውን አድርገዋል።በሀዘን ተውጠዋል።በቲ―ሸርቱ ላይ «የሚያደርጉትን አያውቁም እና ይቅር በሏቸው »ይላል። በደመራው ላይ በኢህአዴግ የተገደሉ ንፁሃን ዜጎች ፎቶግራፎች ይታያሉ።በጥቁር መስቀል ፣በጥቁር ቲ―ሸርት ሀዘናቸው በፀሎት የጀመሩት  3 ወጣቶች ግን ብዙዎች ተጋርተዋቸው ለሞቾች እና በጉዳት ላይ ላሉት በፀሎት ደመራ ሰነ ሰርዓት አድርገዋል።ከጥቂት ሰዓታት በሃላ አንባገነኑ የመንግስት ወታደሮች ወደ ጭፍጨፋ፣አፈና እና ቅጥቀጣ ገብተዋል።አሁንም የሚያደርጉትም አያውቁምና ብለናል።

tom2

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.