ምክር በአማራ ተጋድሎ ዉስጥ ለምትንቀለቀሉት ወጣቶች ?? [ሸንኩት አየለ]

Amhara - satenaw 2ምክር ባደባባይ አለ እንዴ? እንዳትሉኝ::አዎን አለ::የአደባባይ ምክር ነዉ ጥሩዉ::ወያኔ እየሰማች ጮክ ብላችሁ የምትነጋገሩት የአደባባይ ነገር ለወያኔዎች እንዴት ግሩም ሚስጥር ትሆንናቸዋለች መሰላችሁ? እሷን ሚስጢር ሲፈልጉ ሁሉም ቦታ ሲባዝኑ በሀሳብ እንዲደክሙ ጭምር መልካም ነዉ::

እናም ዛሬ አቶ ገዱን እና የአማራ ተጋድሎ ሀይላትን አንድ ምክር ላካፍላቸዉ ተነሳሁ::በአደባባይ !

-አቶ ገዱ አለቀሱ አሉ::ምን አስለቀሳቸዉ? አትልም:: የአማራ ህዝብ ፍቅር ነዉ አሉ ያስለቀሳቸዉ::እንዴት ሆኖ? አንዱ ነበልባል የአማራ ወጣት አማራ ልብ ዉስጥ የሚንቀለቀለዉን እዉነት እንዲህ ሲል ገለጸላቸዉ አሉ:: ያዉም በስብሰባ ላይ:: ለማን? ::

ለአቶ ገዱ:: አማራን ወዳጅ ናቸዉ እየተባለ ለሚናፈስላቸዉም: ለሚወራላቸዉም ባለስልጣን:: (ለዛሬ የወያኔ አሽከር የምትለዋን ፍረጃዬን ተወት አድርጊያታለሁ:: ለምን ? አትሉም:: አቶ ገዱን እየመከርኩ ስለሆነ ነዉ::)

– እናማ ነበልባሉ ወጣት “አቶ ገዱ አማራ ሲታረድ እና የአማራ ወጣት በመከራ ሲንገላታ አንተ ምን እየሰራህ ነዉ:: አንተ ዛሬ አማራን ባታድን እኛ በራሳችን የተደረገብንን ሁሉ እንበቀላለን:: አማራ ደምን በደም ሳይበቀል አያርፍም::አማራ ለልጁ እንኳን ስም ሲያወጣ ደመላሽ ብሎ ነዉ::” ብሎ አማራ ወጣት ላይ የሚደርሰዉን ግፍ እና ይሄን ግፍ አማራ እራሱ እንደሚበቀለዉ አስረዳቸዉ አሉ:: ለአቶ ገዱ መሆኑ ነዉ::

-እናም አቶ ገዱ አለቀሱ አሉ::ያዉም ስቅስቅ ብለዉ:: እረ ! እዉነት ከሆነ ይገርማል:: ድራማም ሊሰሩብን ይችላሉ::ወያኔ ተምች ነች::አሽክሮቿንም በደንብ ተምች አድርጋ ታሰለጥናቸዋለች::ወይም ትጋልባቸዋለች:: ለማንኛዉም ለጊዜዉ የአቶ ገዱ ለቅሶን እዉነት ነዉ እንበል ይዘነዉ ወደ ምክራችን እንዝለቅ::

– አንድም መልካም ስሜት አላቸዉ ማለት ነዉ::ሁለትም ምን ያንፈቀፍቃቸዋል::የአማራን የድሮ ጠመዝማዛ ስልት ዘርግተዉ ህዝባቸዉን መታደግ የሚያስችል ስልጣን እጃቸዉ ላይ እያለ የምን መንፈቅፈቅ ነዉ:: እረ ስልጣን የላቸዉም የሚል ሰዉ ካለ ስልጣን ምን መልክ እንዳለዉ ያልገባዉ ነዉ ማለት ነዉ::እንኳን እሳቸዉ የገዱ ሚስትም ስልጣን ይኖራታል:: ሆኖም ስልጣን ማለት አጠቃቀሙን የሚያዉቅ ጀግና ብቻ የሚጠቀምበት የኒኩሊየር ሀይል ነዉ ብለን መጠቅ ባለ የሀሳብ ማማላይ አስቀምጠንዉ እንለፍ::

እረ ጃል ? ምን ማድረግ ይችላሉ? የአቶ ገዱ ደጋፊዎች ጥያቄ ሲያነሱ ይታዬኛል::

እንግዲህ አቶ ገዱ ከኔ ጋር በማህበራዊ ሚዲያ ጓደኛ አይመስሉኝም::ወይም ይሄን ምክር ላያነቡት ይችላሉ:: ስለሆነም ወዳጆቻቸዉ እና አጨብጫቢዎቻቸዉ (ይቅርታ አጀጋኞቻቸዉ ለማለት ፈልጌ ተሳስቼ መሆን አለበት?) ከዚህ በታች ያለችዉን ምክር ለአቶ ገዱ አድርሱልኝ::አቶ ገዱ ለአማራ ተጋድሎ ሀይላት ብዙ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር አለ:: ምን ምን ? አትሉኝም:: እሱም እንደሚከተለዉ ነዉ::

-ከዘመዶቻቸዉ አንድ ሚስጥር አዋቂ ሰዉ ይመልምሉ::ማን? አቶ ገዱ ናቸዋ? እኮ ለምን? ሚስጥር ጥበቃ ነዋ ! ይልቅ ከዚያስ በሉ ::
-ከዚያ ይሄን ሚስጥረኛ ዘመዳቸዉን ገንዘብ እንዲዘርፍ ያመቻቹለት:: እንዴት አድርገዉ? እያላችሁ እንደሆነ የልባችሁ ሹክሹክታ ይሰማኛል::

– እረ ! ይሄን እማ ለኢህዴግ ባለስልጣናት ማስረዳት የለብኝም::እሳቸዉ ስልቱን በደንብ ያዉቁታል::ዋናዉ ተጋድሎዉን ለማገዝ ከቆረጡ ነገሩ ቀላል ነዉ::ይልቅ ከዚያስ በሉ?
-ከዚያማ ይሄን ዘመዳቸዉን የተጋድሎ ሀይላት ሆን ብለዉ በሚስጢር እንዲያፍኑት እና ገንዘቡን እንዲቀሙት ሚስጥር ይመስጠር::ሚስጥር ይመስጠር ሲባል ታዲያ ከዚያ በኩል ከተጋድሎዉ ሀይላት : ከዚህ በኩል ከአቶ ገዱ ዘመድ በኩል ነዉ:: አሁን ነዉ ሱሪ የታጠቀ ወንድ የሚያስፈልገዉ::የሚያለቅስ የሚንፈቀፈቅ አይደለም:: እንግዲህ ጀግና ከሆኑ ሚስጥር አዋቂም: ሚስጢር ደፋሪም መሆን አለባቸዉ::

-እናስ? እናም በቃ ! ተጋድሎዉ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ያልቃል::ይጠናቀቃል:: እንዴት? አትሉም ::
-ተጋድሎዉ እኮ አሁን ዋና የቸገረዉ ነገር ዉሻ ማባረሪያ ዱላ ነዉ::ብሩ ካለ ደግሞ ዱላ ይገዛል::ወይም ዱላዉን ከጫካ መቁረጫ መጥረቢያ በጥበበኛ ይሰራል::ይሰራል እንጅ :: በደንብ አድርጎ ይሰራል:: አሁን የቸገረዉ ብር ነዉ::ብር ደግሞ አቶ ገዱ እጅ አለ::እና አቶ ገዱ የግድ ጦር ማዝመት የለባቸዉም::ወይም ማልቀስና መንፈቅፈቅ የለባቸዉም:: ቡሩን ወደ ህዝብ ይግፉት::ብር ሲባል ታዲያ ባቄላ (ባኤላ) መግዣ አይደለም::ዱላም:: ጠጠጠርም መግዣ ነዉ:: እናም ደግሞ ላንጠረኛዉ ጭምር::

-ከዚህ ዉጭ አቶ ገዱ አለቀሱ::ስልጣን ልለቅ ነዉ አሉ::ቡራ ከረዩ አሉ:: ህዉሃት ላወርዳቸዉ ነዉ አለ:: በዚያ ገባ::በዚህ ተገለበጠ ቢባል ምንም ዋጋ የለዉም::ህዝቡ ዉሻ ማባረሪያ ዱላ ነዉ ያጣዉ::ዱላ ብቻ !!! ዱላ ደግሞ ተወደደ::

-ድሮ ጣሊያን ጥናት አስጠና አሉ::ምን ሲል? “እነዚህ አማሮች ጥሩ ተዋጊ ናቸዉ ይባላል::እስኪ ይሄን የዉጊያ ብቃታቸዉን ገምግሙት::አጥንታችሁ ለታላቁ የሞሶሎኒ መንግስት አቅርቡ” ብሎ::እና ዉጤት ተገኘ? አትልም::አዎ ዉጤቱ አስገራሚ ነዉ:: እንዴት አስገራሚ?

-ፕሮፌሰር ሰባስኪ (ጣሊያናዊ ፕሮፌሰር ነዉ) በታሪክ መጽሀፉ እንደሚተርከዉ እማ ከሆነ “አማራ የሚባለዉ ህዝብ ጦርነት ገጥሞ ፈጽሞ የማይሸሽ ነዉ ብሎ ቁጭ:: ከጀርመኖችም በላይ ጨካኝ ተዋጊ ነዉ:: ጀርመን የሚባለዉን የጣሊያን ጠላት አፈር የሚያልስልን ወታደር ከአማሮች መልምሉልን” ብለዉ ቁጭ:: ማናቸዉ እንዲህ የሚሉት አትልም? እነዚያዉ ጣሊያኖች ናቸዉ::

እና ይሄ ነገር ከአቶ ገዱ ጋር ምን ያገናኘዋል? አትልም::
በብዙ መልክ ይገናኛል ! ጌታዉ ! አማራን የመሰለ ተዋጊ ህዝብ የሚኖርበትን ክልል እየመሩ የምን መንፈቅፈቅ ነዉ? እናማ አቶ ገዱ ምን ያንፈቀፍቃቸዋል? ቀላሉን ስራ ይስሩ::ብሩን ወደ ህዝብ ይግፉት !!! ለዱላ መግዣ ማለት ነዉ::ዉሻ ለማባረሪያ:::

እረ ህዝቡ ጠመንጃም አይፈልግ :: ዱላ ብቻ ነዉ የሚፈልገዉ:: ለዉሻ ማባረሪያ::እናማ አቶ ገዱ ብሩን ወደ ህዝቡ ማስገቢያ መንገድ ፈልጉ::ሌላዉን ለህዝቡ ተዉት::

ወይም እንደ ገዱ በዬ አደባባዩ ከመንፈቅፈቅ ይልቅ ልብህ ያረረ በስህተተ ግን የወያኔ ሞፈር ቀንበር ልትሸከም ብአዴን ዉስጥ የገባህ የአባቶችህ ልጅ (የአባቶችህ ልጅ የሚለዉን ረግጠህ እና አስምረህ ልብህ ዉስጥ ከትበዉ) ካለህ ብሩ ወደ ህዝብ የሚደርስበትን መንገድ ፈልግ:: ስራዉን ህዝብ ይሰራዋል:: ብር ካለ ! ደግሞ ዉሻ ለማባረር:: ህዝቤን የቸገርዉ ብር ነዉ::

ይሄ ምክር እንግዲህ አቶ ገዱ የወያኔን ድራማ እየተወኑ ላይሆን ይችላል የሚለዉን ቀጭን ታሳቢ መዘን ወስደን እንደ አዎንታ ተቀብለን መሆኑ ነዉ::ወፍራሙ እዉነታ ግን አቶ ገዱ እዉነት የሰዉ ልብ ነዉ ወይስ የወያኔ ልብ ያላቸዉ የሚለዉ ጉዳይ ጥቅጥቅ ጫካ መሆኑ ነዉ::የማይታይ : የማይታወቅ እና ያልተደረሰበት ለማለት::

ለማንኛዉም በአማራ ተጋድሎ ዉስጥ የምትንቀለቀሉ ወጣቶች እንደ አባቶቻችሁ ቀኙንም ግራዉንም ብቻ ሳይሆን በፊትም በኋላም የመሸገዉን የጠላት ቀበሮ እና ተኩላ ጠልቃችሁ ማዬትን እንዳትረሱ:: ምናልባት ገዱ ከተኩላዎቹ አንዱ ከሆን ለቅሶዉ በወያኔ ተጽፎ የተሰጠዉ ድራማ ሊሆን ይቻላል::የወገን ልብ ካለዉ ግን ከላይ በተባለዉ ምክር ፈትኑት::

ለቅሶዉን እና መንፈቅፈቁን ተወዉ::ለቅሶዉን እናቶቻችን ለተጋድሎዉ ስንሰዋ ያለቅሱታል በሉት:: የአማራ እናት ጀግና ወላድ ብቻ ሳትሆን ጥሩ አልቃሽ እና አስለቃሽም ነች:: ያዉም መሪሪ ለቅሶ:: የሚያልቁ ልጆቿን የሚታደግላት ገዱን እንጂ ልጆቿን ከወያኔ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ እያስፈጀ የሚንፈቀፈቅን ገዱን እንደ ኩሩ ሴትነቷም ትጸዬፈዋለች::እረ በጣም አድርጋ !!

“ገደያ እወዳለሁ” ብላ የምትዘፍነዋ የአማራ ጉብልም ገዱ አለቀሰ ቢሏት “ቡፍ” ማለቷ አይቀርም:: ይሄን ሁሉ ስልጣን እጁ አርጎ ይጠቀምበት እንጅ ለማለት ነዉ:: ደግሞ ወንድ ልጅ የምን ለቅሶ ነዉ ስትል መሆኑ ነዉ:: ወገን ከሆንክ ጠላትን በጥርስህም ቢሆን መዘልዘል ወይም ማስዘልዘል ነዉ እንጅ የምን መንፈቅፈቅ ነዉ ስትል በገዱ ለቅሶ “ቡፍ” ማለቷ አይቀርም::

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.