ሰበር ዜና – ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲን ለማዳከም የጀመረውን እንቅስቃሴ ቀጥሏል

ፍኖተ ነፃነት

1466201_717380598346877_8775056603559492066_nኢህአዴግ አንድነት ፓርቲን ለማዳከም የጀመረውን እንቅስቃሴ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በራስ ሆቴል ከተለዩ ዞኖች አባላትን ፓርቲው መግለጫ እንደሚሰጥ በማስመሰል አስጠርቶ፤ ተልዕኮ ባላቸው ግለሰቦች መግለጫ አሰጥቷል፡፡

በመግለጫው ሳይ እንዲገኙ የተጠሩት የዞን አመራሮች የኢህአዴግ ሴራ እንዳለበት በመረዳታቸው በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ በፓርቲው ጽ/ቤት በመገኘት ያጋለጡት አቶ ግርማ ታረቀኝ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ የምዕራብ አርሲ የአንድነት ሰብሳቢ እና አቶ ታደሰ ወርቁ በኦሮሚያ ክልል የአርሲ ዞን የአንድነት ሰብሳቢ ሲሆኑ እኛ መግለጫ ይሰጣል ተብለን ነው በራስ ሆቴል የተገኘነው ነገር ግን ያየነው ነገር በጣም አስገርሞናል በቦታውም በመገኘት የተደረገውን ድርጊት ተቃውመናል፡፡

አባላት ወደፊትም ለእንደዚህ አይነት የተሳሳተ ዓላማ ባላቸው ኃይሎች እንዳይታለሉ ከፓርቲው ጽ/ቤት በሚደርሳቸው ጥሪ መሰረት ብቻ በሚጠሩበት ቦታ እንዲገኙ በማለት ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.