መንግስት ራሱ በፈጠረው ስጋት ህዝብም ሰጋ ተሸበረ!!!!  [ከአስገደ ገብረስላሴ]

17  /.1  /2009 ዓ ም መቀለ

Woyaneስርአቱ ራሱ ነጻነት ነጥቆ  ህዝብን በመፍራት  ተመልሶ በህዝብ ላይ ስጋት በመፍጠር  ዜጎች ነጻነት አግኝተው እች የተባረከች ተፈጥሮ ያደላት ለም ሀገራቸው   በነጻነት ተራምደው  ረግጧትና ተዝናንተው  እንዳይ ኖርባት ይኸው ስርአቱ ራሱ አሸባሪ ሆኖ ህዝብ ተሸብሮ መብቱ ነጻነቱ አጥቶ  ተሸማቅቆ እንዲኖር እያደረጉ ይገኛሉ  ።

ይህ ሀሳባ ላስነሳ ካደረገኝ   ምክንያት የኢትዮጱያ ህዝቦች አብዛኞቹ እምነቶች በፈለገት የእምነት በታ ስርአተ ጸሎት አድርገው  አሁን ካለው ስርአት በተሻለ  ያለስጋት ጸሎት አድርገው ይለያዩ ነበር  ።ይህ ስል ግን የጃንሆይ አንዱን እምነት የበላይነት ሌሎች እምነቶች  ዝቅ ማድረግ ወይ ጭራሹን  እምነቶች መከልከል  ።ኃላም ፈሽሽታዊ  ደርግ ጭራሹን ሁሉም እምነቶች  ጸረ አብዮት በማለት   ለመዝጋት  ሞክሮ ነበር  ። የእምነት መእመናን ግን ይፈጠርባቸው የነበረ ተጽእናኖ ወደጎን በመተው  በእምነታቸው በመጽናት አማኒያን በፈለጉት የእምነት ቦታ በመስበክ መስዋእትነት ይከፍሉ ነበር  ህዘቡም አይሰጋም ነበር ።  በወቅቱ  የእምነት ቦታዎች በተወሰነ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ለዘውዳዊው ስርአት  የማምለክ ጉዳይ ቢኖርም ። የሀይማኖት መድረኮች  እንደ  አሁን ያለው  ስርአት  የእምነት  ቦታዎች  የፕረዝዳንቶች ፡ የምኒስቴሮ ች ፡ ከንቲባዎች ፡ወረዳዎች ባለስልጣናት ፡ የፖለቲኮኞች ማጥመቂያ አልነበሩም ።
በአሁኑ  ጊዜ ያለው ስርአትስ  ?ይሀስርአት ከኃላ ታሪኩ ስንመለከተው በተለይ ደግሞ በስልሳዎች የነበሩ ፖለቲኮኞች  እነ ህወሀትና በአዴን   ፡ ኢህአፓ  ሌሎችም  ከደርግ የባሱ በአበዮታዊ ዲምክራሲ  የተጠመቁ  ጭራሹን የሀይማኖት እምነት አልነበራቸውም ። እንዳውም ቤተክርስትያን ለሚስሙ የኦርቶዶክስ    ወይ ሰአታቸውን ጠብቀው ለሚሰግዱ ሙስሊሞች  ታጋዮች  ይናቃሉ  በፓለቲካ  አይታመኑም ነበር ።
ይህ ስርአት ስልጣን ከያዘም ባህርዩ ቀይሮ የሁሉም  የሀይማኖት መብቶች እናከብራለን በማለት በህገመንግስት  አጽድቀው ለገዜው የሀይማኖት መብት  ለቀቅ ማለት ጀምረው ነበር ።
የሀይማኖት መብቶች ለፖለቲካ ፍጆታቸው ለቀቅ አድርገውት ቢኖሩም  በተዘዋዋሪና በቀጥታ ግን  የሀይማኖት መድረኮች ወይ  በአላት የስርአታቸውና የፖለቲካ አላማዎች ማጥመቅያና ለማሳካት  ከማድረግና ለመሳሪያነት   ከዘውዳዊው ስርአት በላይ ተጠቅመውበታል ።እንዳውም አብዛኛው ጊዜ ከሀይማኖት  መሪዎች  በፊት ቀድመው የፓለቲካ ቃለ ቡራኬ  በመስጠት ህገመንግስት እየናዱ መጥቷል ።
የነዚህ ሰዎች ከእምነቶች  ነጻነት በላይ መሆናቸው  ተጨበጭ መረጋገጫ በዛሬው 17 / 1 /2009 ዓ ም በአዲ ግራት  በተከበረው የመስቀል በአል ኢትዮጱያ ፓትሪያርክ ወይ ጳጳስ  የመስቀል ቃለ ቡራኬ ከመስጠታቸው በፊት  የክልል ትግራይ  መንግስት አባይ ወልዱ መድረኩ በመቆጣጠር  ደስ የማይልና አንድነት የማያንጸባርቅ በመላው የሀገራችን ህዝቦች ስጋት የሚፈጥር የጭቆና ቡራኬ መስጠታቸው ነው ።
እኔ የሚገርም ግን በሀገራችን ያሉ የሀይማኖት አባቶች የእምነት ነጻነት መድረኮች  በፖለቲኮኞች፡ አምባገነኖችች ሲነጠቁ  በአድር ባይነትና ስጋት እምነታቸው እንዲረገጥ አሳልፈው መስጠታቸው ነው።
ይህስርአት መቸ የሀይማኖት መድረኮች ለፖለቲካው አለማ ማሳካት ታሳቢ በማድረግ  ብቻ አይደለም ስህተት የሚፈጽመው ያለው ።
ዋናው ችግሩ ከፖለቲካ መስመሩ ፡ከፖሊሱ ፡ ከመንግስታዊው አወቃቀሩ ስህተት የመነጩና ለዜጎች ሁሉም አይነት መብቶችና ነጻነት  በመንጠቁ ፡ሁ በዝህች አገር የሚገኙ ዜጎች  በእኩልነት መኖር ተስኖዋቸው  ፡በደስታ በሀዘን ወይ በእምነት ነጻነት ቦታዎች ፡ በመዝናኛ ማእከላት  ሰክነውና ተረጋግተው እንዳያከብሩ  ዜጎች በእምነታቸው በባህላቸው ለመራመድ በለመቻላቸው ፡ ስርአቱ የዜጎች ጥያቄ ተገቢ ፍትሀዊ መልስ ባለመስጠቱ  ህዝብ ቂም በመያዙ ።
መንግስት ወይስርአቱ ከህዝብ ጋር ከፖለቲኮኞች ዝቅ ጎንበስ ብሎ የህዝብ ተገዥነት ባህል በመያዝ  በመታረቅ ሰላም በመፍጠር   በህዝብ በመተማመን በአሉ ነጻ ሆኖ እንደማክበር ፈንታ  ። የዘንድሮ የጥምቀት በአል በቡዙ ቦታዎች ህዝቡ በእምነት  ቦታው በነጻነት  ለማክበር ስርአቱ በፈጠረው የማሸበር ዘመቻ ህዝቡም  ተሸብሮና ሰግቶ  ወይ ተከልክሎ ። ወይ ህዝቡ በባአሉ ከተሰባሰበ ለተቃውሞ ሰልፍ ይመቻል በሚል የመንግስት  ስጋት በመፈጠሩ የመስቀል የሀይማኖት በአል እጅጉን ቀዝቅዞና ስጋትን አንጃቡቦበት ነው የዋለው ።
ለዚሁ ቅዝቃዜና ስጋት ተጨባጭ ማስረጃ  ፡በአዲስ አበባ ፡ በመስቀል አደባባይ የተከበረው እጅግ እጅግ ጥቂት አማኒያን ነው የተሳተፉ  ። መቀሌ ጮምዓም ስጋት ስለነበረ  አመርቂ ካለመሆኑም በስርአቱ ከባድ አፈና  ነበረው  ።   እንደዚሁም  በዛሬው ቀን በመቀሌ ሰውሒ ንጉስ  በ5 ሰአት የተከበረው የመስቀል በአል  ትላንትና በጮምአዓ  ታሪካዊው የመስቀል በአል  አከባበር ባጋጠመው የስርአቱ  እንቅፋት ምክንያት ቅሬታ ስለተሰማው  ቡዙ ህዝብ አልተሳተፈም ።በጎንደር  ፡ በጎጃም እንደዚሁ በርዶና ቀዝቅዞ  በስጋት ነው የተከበረው። የመስቀልና ፡ ጥምቀት በአል በትግራይ ፡በጎንደር ገጃም፡ አዲስ አበባ ነበር በድምቀት  የሚከበረው የነበረው።
በትግራየ በአዲግራት ሁሉም በለስልጣናት ተገኝተው በአባይ ወልዱ ቃለ  የተባረከ ኃላም በሀገራችን ጳጳስ ሰበካ የተደረገበት የመስቀል  በአል ለቡዙ ጊዜ ዝግጅት የተደረገበት  ከስጋት የተነሳ  ፡ ስፍር ቁጥር የሌለው የጸጥታ ሀይሎች አጅበውት በስጋት የተከበረ የመስቀል በአል ነው ።
ሀገራችን ከዚህ ሁሉ ይሆናል   ፡ይሆናል ወይ በትግርኛ ቋንቋ  ምናለባች ሊደረግ ይወናል ከሚል ስጋት  መቸ ትላቀቅ ይሆናል  ????????????????
በኔ እምነት ስጋት ሊጠፋ ከሆነ ስርአቱ  ሁሉም ሀላፊነት ፡ነጻነት  ፡መብት ፡እኩል ተጠቃሚነት ፡ የሀሳባ ነጻነት ፡  የህዝብ  ነጻ ተሳትፎ በሀላፍነት  ለዜጎች ከሰጠ መፍትሄ ይገኛል ። ካለበለዚያ ብቻው ቤት ዘግቶ ባሉት ለውሸት ተዘጋጅተውጆራችን በውሼተ ዳታ የሚያደነቁሩን  የሚዱያ ቅምጦች አገር አይቀየርም ።
ከአስገደ ገብረስላሴ ፡
17 / 1 / 2009 /ዓ ም  መቀለ ፡፡፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.