ህውሓት ሃያ አምስት አመት ሙሉ የሳበው ካርድ አልቆበታል [ናትናኤል አስመላሽ]

የህውሓት የመጨረሻ ካርድ !!!

TPLF (1)የቀሩት ሁለት ካርዶች ብቻ ናቸው። አንደኛው በትግሉ ጊዜ ሲጠቀምበት የነበረው አማራ እና ኦሮሞ ነው ጠላትህ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ዓረና የአማራ የኦሮሞ ተላላኪ ነው ከአማራ እና ከኦሮሞ ጋር ሆኖ ሊያጠፋቹ ነው የሚል ነው። ህውሓት አሁን መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ አመኔታ ተነግፈዋል(አጥታለች)፣ ይህ ብቻም አይደለም የህውሓት አባላት በህውሓት ላይ ተስፋ ቆርጠው አማራጭ ፓርቲ ፍለጋ ላይ ናቸው።
.
ህውሓት በየገጠሩ እና ከተማው አማራ እና ኦሮሞ ተባብረው ሊያጠፍዋቹ ነው ተነሱ ዓረናም ተባባሪ ነው በማለት ቀን ከለሊት እየቀሰቀሰች ነው። የዚህ ሁሉ ምንጭ የህውሓት የስልጣን ጥም እና የህውሓት መጨረሻችን ምን ይሆን ከሚል ፍራቻ ነው። ህውሓት ከትግራይ ውጭ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ውስጥ ለውስጥ በማስፈራራት እና ተጠንቀቁ በማለት የስልጣን ማራዘምያ ዘዴም ከፍታለች። ለምሳሌ በሃረህ ለሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በተለይ የትግራይ መታወቅያ ያለባቸው በማስፈራራት ላይ ትገኛለች።
.
የህውሓት መጨረሻ ልክ የሳዳም እና የጋዳፊ መጨረሻ እንደሚሆን አጠያያቂ አይደለም !ይህንን የምታውቅ የትግራይ ወጣት ከህውሓት ቦሃላ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመተባባር በአንድነት እንደሚኖር አውቀህ በየከተማው እና በየገጠሩ ላለው የትግራይ ህዝብ በማስረዳት አዲስትዋን ኢትዮጲያ ለመገምባት ታሪካዊ ግዳጅህን ተወጣ። የትግራይ ህዝብ እንደ ማንኛው የኢትዮጲያ ህዝብ ከህውሓት በፊት የተፈጠረ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ከህውሓት አልተጠቀመም አዎ የህውሃት ባለስልጣናት እና ቤተሰቦቻቸው ግን ከትግሉ ተጠቅመዋል፣ ስለሆነም ከህውሓት ቦሃላ የትግራይ ህዝብ እንደማንኛው ጭቁን ህዝብ ከህውሃት የጭቆና ቀንበር ወጥቶ አብሮ እንደሚኖር ምንም ጥርጥር የለውም ፣ ስለሆነም የትግራይ ወጣት ሆይ የትግራይ ህዝብ ከህውሓት ቦሃላ ከሁሉም ህዝቦች ጋር አብሮ እንደሚኖር በማወቅ በማስረዳት እና መከታ በመሆን ታሪካዊ ግዳጅህን ተወጣ።
.
ዓረና ትግራይ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ተላላኪዎች ሳይሆን የትግራይ ህዝብ አማራጭ ፓርቲ መሆኑን ታውቃለህ፣ የትግራይ ህዝብ ብቸኛ ጠላት ህውሓት ነው። አዎ ትናንትም ዛሬም ነገም የትግራይ ህዝብ ብቸኛው ጠላት ህውሓት ነው!!! የትግራይ ህዝብ ሆይ በከፈልከው ደም እና አጥንት ለዓረና የመታገል እና የማታገል መብት የምትሰጠው አንተ የትግራይ ህዝብ እንጂ ህውሓት አይደለም ! ህውሓት ሃያ አምስት አመት ሙሉ በስምህ ነግደዋል፣ዘርፈዋል፣ገድለዋል አሁን የትግራይ ህዝብ ልክ እንደ ሌላው ህዝብ ለውጥ ትፈልጋለህ፣ የለውጡ መሪ ደግሞ አንተ ነህ።
.
ህዝቦች በታሪክ ተጣልተው አያቁም አምባገነኖች ግን አዎ ህውሓቶች ግን አዎ።የትግራይ ህዝብ የወደፊት እጣ ከሌሎች ህዝቦች እንጂ ከህውሓት ጋር አለመሆኑን የተገነዘብከው የህውሓት ካድሬም በርታ፣ ጊዜው አሁን ነው ዓረና ማለት ሰላም ፍቅር አንድነት መከባበር ማለት ነው። የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ከሚያፋቅር ዓረና ጎን ተሰልፈህ የትግራይን ህዝብ መከራ ስደት ወዘተን ለማስቆም ታገል።የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ከትግራይ ህዝብ የወጡ የህውሓት አምባገነኖች እንጂ ከትግራይ ህዝቦች ጋር ለአመታት የኖሩ የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች አይደሉም።አዎ “ትናንትም ዛሬም ነገም ” የትግራይ ህዝብ ብቸኛው ጠላት ህውሓት ነው!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.