ጎጃም መተከል በሚገኘው 23/45ኛው ከ30 በላይ ወታደሮች የታጠቁትን ዘመናዊ መሳሪያ ይዘው ተጋድሎውን ተቀላቀሉ

Amhara - satenaw 2ጃም መተከል በሚገኘው 23/45ኛው ወታደራዊ ካምፕ ይኖሩ የነበሩ ከ30 በላይ ወታደሮች የታጠቁትን ዘመናዊ መሳሪያ ይዘው ህዝባዊ ተጋድሎውን ለመቀላቀል ጫካ ገብተዋል

የመተከሉ 23/45ኛው ወታደራዊ ካምፕ ማለት በአማራ ተጋድሎ ወቅት ወጣቶች የተገደሉበት፤ አካለ ጎደሎ የሆኑበትና በስቃይ ርሃብና ጥም ውስጥ ደንጋይ እንዲፈልጡ ሲደረግብት የነበረ አካባቢ ነው። ወታደሮች ጫካ የገቡት ሌሊት ላይ የመሳሪያ መጋዘን በመስበር ከውስጥ የነበረውን በትንሹ 10 መትረጌየስና መሰል ዘመናዊ መሳሪያዎችን በመያዝ ነው።

በዚህ የተነሳም መተከል ከፍተኛ የሆነ ፍለጋ ተጀምሯል።ፓትሮል በየጫውካ ተጀምሯል። የወያኔ ደህንነቶችና ጀሌዎች እስከ ምሽቱ 2:30 ድረስ በግልገል በለስ ዞን አስተዳደር አዳራሽ ስብሰባ ላይ ነበሩ። ከወታደሮቹ በተጨማሪ በአማራ እና ኦሮሞ ላይ ወያኔ እየወሰደው ባለው ግድያ ሲበሳጩ ከነበሩ ወጣቶች መካከል ጥቂቶቹ ዛሬ ህዝባዊ ተጋድሎውን ተቀላቅለዋል።

በሌላ በኩል እዚያው ጎጃም ሸርቆሌ አካባቢ ህዝብ ሊገድሉ የሄዱ 16 የወያኔ ወታደሮች ላይ ህዝቡ ራስን የመከላከል እርምጃ ወስዶባቸዋል። ሸርቆሌ አካባቢ የ12ኛ ክፍለ ጦር መገኛ ነው።

ይህ ጎጃም መተከል የሆነው ለሌሎች አካባቢ ወታደሮችም ትልቅ ትርጉም አለው። ዛሬ ላይ ወታደር ሆኖ ከህዝብ ጎን ለመቆም ብቸኛው ምርጫ የኢትዮጵያን ጫካዎች መቀላቀል ወይም የውስጥ አርበኛ መሆን ነው።

#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!

#የአማራ_ተጋድሎ፡ጎጃም

 

ጎንደርና ጎጃም እየተካሄደ ያለውን የአማራ ተጋድሎ ተከትሎ ከወር በላይ በግፍ ብርሸለቆ ታሰረው የነበሩት በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ወጣቶች ዛሬ ተፈተዋል። ወጣቶቻችን ከብርሸለቆ ሲወጡ ተጋድሎውን አጠናክረው ለመቀጠል ቃለ መሀላ ፈጥመዋል። የአማራ ተጋድሎ የወያኔ ግብዓተ መሬት እስኪፈጸም ድረስ በአማራ ትውልድ ብርታትና ጥንካሬ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

 #የአማራ_ተጋድሎ፡ ብርሸለቆ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.