ሰበር ዜና ….በአዲስ አበባ ዙሪያ ከፍተኛ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ ነው

1awከትላንት ማለዳ አንስቶ በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ አከባቢዎች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል፡፡
አዲስ አበባ አስኮ አዲስ ሰፈር አከባቢ ትላናት አመሻሽ ላይ ተቃውሞ ተከስቷል፡፡ ከአጎራባች የኦሮሚያ ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ወደ አስኮ አዲስ ሰፈር አቅንተው መንገዶችን በድንጋይ ዘግተው ነበር፡፡ በዚህ እንቅስቃሴም በአከባቢው ያሉ ሱቆችና ሆቴሎች ተዘግተዋል፡፡ ነዋሪዎችን መፈክሮችን በማስመት በአከባቢው ያለው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም አድርገዋል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ በስፍራው የደረሰው የፌደራል ፖሊስ መንገዶችን አስከፍቶ እስከ አሁን ድረስ በስፍራው ይገኛል፡፡
*
ከዛሬ ማለዳ አንስቶ ከታ፣ ቡራዩ እና ቡራዩ ማርያም አከባቢዎች ምንም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም፡፡ መንገዶች በድንጋይ ተዘግተዋል፡፡ በአከባቢው ቁጥሩ በርከት ያሉ የታጠቁ ኃይሎች በመኪናዎች እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡
*
በሱሉልታ እና ጫንጮ ታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው፡፡ በከተማው ምንም አይነት የትራንስፖርት አገልግሎት አይታይም፡፡ የመንግስት ካድሬዎች ታክሲዎችን ወደ ስራ እንዲገቡ ያደረጉት ጥረት ሊሳካላቸው አልቻለም፡፡ በዚህም የመንግስት መኪኖች ነዋሪዎችን እንዲያጓጉዙ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የግለሰብ መኪኖችን እያስገደዱ ተሳፋሪዎችን በማስጫን ላይ ይገኛሉ፡፡
*
በፉሪ ተቃውሞ ተቀስቅሷል፡፡ ፉሪ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ስትሆን መገኛዋም ከጀሞ ኮንዶሚኒያም አቅራቢያ ነው፡፡ የፉሪ ነዋሪዎች ከረፋድ አንስቶ መንገዶችን በድንጋይ ዘግተው ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ ቁጥሩ በርከት ያለ የአከባቢው ነዋሪ ተቃውሞውን በመቀላቀል ላይ ይገኛል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.