መዲናችን አዲስ ዛሬ ፦ [ዳንዔል ሺበሽ]

ዛሬ መስከ 25ቀን፡ 2009 ዓም ከስልሳ በላይ መኪኖች ጤናቸው ታውኳል፡፡ የድንጋይ ናዳ እንዳስተናገዱ ሰማሁ፡፡ ከባለመኪኖቹና ከነጂዎቹ፡፡ የተወሰነውን በዓይኔም ተመለከትሁ፡፡ ተሽከርካሪዎች የሚሄዱበት መንገድ መዝጋት የህጋዊነት/የተፈቀደ ሥራ ይመስላል ፡፡ ነገሩ ሰበብ በኢሬቻ በዓል ከተፈፀመው እልቅት ጋር የተያያዘ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ የሁሉም እጅ ያለበት ይመስላል፡፡ የሃይማኖት፣ የብሄረሰብ፣ የሹሜት ወዘተ ድንበር/አጥርም ሳይጣስ አይቀርም፡፡ እስቲ ማን ይከልክል፡፡ ጄሞ፣ ሰበታ፣ አለምገና፣ ወለቴ፣ ካራ፣ አየር ጤና፣ አሻዋ ሜዳ፤ ወልሶ ወዘተ በከፊል ዳመናማ፡ ጭጋጋማ ነበር፡፡

በወታደራዊ መኪኖች ታጥረዋል፡፡ አሁንም ሕዝቡ በሥጋት ውስጥ ያለ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም መንገዶች ሁሉ በከፊል ጭር ብለዋላ፡፡ የሞባይል ኢንተርኔት መስመሮች ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል፡፡ ወደ ጅማና ሆሳዕና መውጫ በሮች ለአብዘኛው አውቶብሶች፣ አውቶሞብሎችና ለታክሲዎች ዝግ ናቸው፡፡ የዘጋው ግን መንግሥት ሳይሆን ሁኔታው ነው፡፡ መንገደኞች በየመንገዱ ዳር ተኮልኩሏል፡፡ እንቅስቃሰዎች ሁሉ ዘርዛራ ናቸው፡፡ ቪዲዮና ፎቶዎችን አፕሎድ ያላደረኩት በኢንተርነት ችግር ነው፡፡

ቸር ያሰማን!

14610993_224860514595701_4903220276892369388_n

14494796_224859367929149_5136601750683098995_n

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.