ዝቡን የሚጠቅም ትግል በዲያስፖራው በኩል ጠቃሚ ስራ ስለ መስራት [በብርሃኑ መልአክህ]

TPLF (1)ገዥው የህውሃት ስርአትን አከካሪውን በሚመታ መልኩ በውጭው አለም ጠቃሚ ስራ መስራት ይቻላል።የገዥው ስርአት በባህርይው ራሱን በዘር አማክሎ ሎሎችን በማፈን፣በመርገጥና በጅምላ በመግደል(በመጨፍጨፍ) ንብረት ማካበትና መርገጥ ዋና ባህርይውና መልኩ ነው።አንድ ክፍተት ግን በግሌ ይታየኛል….

ይህንን ሁሉ ግፍ በማን አለብኝነት የሚያካሂዱ ሰዎች አንድ ቀን የህዝብ ሃይል ቢያሸንፍ ውጭው ሃገር ሄጀ የተለያየ ቢዝነስ ገዝቸ(ከፍቸ)ልጆቸንሽጥሩ ትምህርት ቤት አስተምራለሁ።እኔንና ቤተሰቤን ጥሩ ህይወት ማኖር እችላለሁ ብለው ስለሚያስቡም ጭምር ነው። ይህንን አስከፊ ስርአት የሚያራምዱት፣የሚደግፉት።በማን አለብኝነት ካለምንም ይሉኝታ ይህንን ህዝቡ ላይ የሚተኩስ ስርአት የሚያራምዱት፣የሚደግፉት።
ዛሬም በተለይም ባደጉት አገራት ራሳቸውና ቤተሰባቸው ተንሰራፍተው ይኖራሉ።ሃገር ዘርፈው ፣.የሰው ህይወት አጥፍተው፣አገር በትነው…ከስደተኛው ጋር እየተጋፉ አብረው አሉ።

ውጭ አገር ያለው ዲያስፖራ ተረባርቦና ተረዳድቶ መረጃ ከማቀበልና አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር ቢያደርግ እነዚህን ወንጀለኞች ለፍርድ ማቅረብና እስር ቤት መወርወር ይቻላል።

በዚህም  ከስርአቱ ጋር የመቆየት(የመቆራኘት)ባህርያቸውንና ምክንያታቸውን ያሳሳዋል ብየ አምናለሁ።
በዚህም ስራ አገር ቤት ያለው የስርአቱ አራማጅም ይሁን ተጠቃሚ የወደፊቱ እጣ ፋንታው ስለሚጠፋበት ስርአቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች ባነሰ ጊዜና መስዋእትነት የመሸነፍ፣ የህዝብን ተቃውሞ የመቀበልና ስልጣን ላይ የመውረድ እድሉን ይሰፋል።

ምልክታቸው…የህዝብ መረጃ፣ያላቸው ንብረትና የሚኖሩበት የመኖርያ ፍቃድ ያገኙበት ምክንያትና የመሳሰሉት በቀላሉ እነሱኑ ለይቶ ሊያወጠቸው ይችላል።በዚህና በሌላም ምክንያት ባሉበት አገር ሁሉ ላይ ስደተኛው ተረባርቦና ተጋግዞ ባንድ ላይ ተነስቶ ቢከሰሱና ለፍርድ ቢቀርቡ

ዘርፈው ያመጡት ብዙ ገንዘብ ተወርሶ ከሳሽ ማ/ሰቡ በተስማማበት መልኩ አገር ውስጥ ያለውን ትግል ለመርዳትና የተሻሻለ ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲመጣ የሚሰራበት ፖለቲካ ላይ ማዋል ይቻላል።
#AmaharaResistance
#Oromoprotest
#Ethiopia

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.