ወስጥ መስመሮቻችን እና አጭር ምላሻቸው ፪ [አቤ ቶላ ፈይሳ]

ለሲሳይ አጌና ፣ መሳይ መኮንን ፣ ደረጀ ሃብተ ውልድ፣አበበ ቶላ እና ሌሎችም ጋዜጠኞች፥-

Abebe Tolla Feyisa
Abebe Tolla Feyisa

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሕወሃት መንግስት ቁጥጥር ሲል ከዋሉበት ሰዓት ጀምሮ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ምን እያሉ ይጠሯቸው እንደነበር ይታወቃል። አቶ አንዳርጋቸው ሰው አልገደሉም ፣ አልሰረቁም ፣ ሕዝብ አይጠላቸውም ፤ ይሁን እንጂ ሚዲያው “ሳይፈረድባቸው” እንደ ወንጀለኛ ፣ ክብራቸውን ዝቅ በማድረግ ከ’ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ውጭ’ ሲገልጿቸው ሰምተናል።
“ኢሳት የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጀሮ ነው” አዎ ነው! ታዲያ የህዝብ ሚዲያ ጋዜጠኞች ፣ የምናከብራሁ እናንተ ሕዝቡን ልትመስሉ ይገባል ፤ በርግጥ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት መገለጫ መሆኑን ባምንም ማለት ነው.. ህዝቡ እንዲህ አያምንምና ። እንዲህ ነው ነገሩ:- የተለያዩ የህዋሃት መንግስት ባለስልጣናትን ፣ሰራዊቱንም ስትገልጹ አንዳንዴ አክብሮት ትጨምራላችሁ (አንቱታ)
ምሳሌ ፥ ፩) የ”ኢትዮጵያ መንግስት” ወይም “መንግስት” ብላችሁ ትጠራላችሁ የኢትዮጵያ መንግስት የሚባል አለ ወይ?
፪) መከላከያ ፣ማስታውቂያ ፣ ትምህርት ፣ ጠቅላይ ሚሩ “እንደተናገሩት…” ፣ “እንዳሉት…” ፣ “አስጠንቅቀዋል…”.. ትላላችሁ እንዴው ለነዚህ “አንቱታ” ቀርቶ እንደ “ሰው”ስ መቆጠር ነበረባቸው?

ለማጠቃለል በኢትዮጵያዊ ባህል “አንቱ” የሚባል ሰው በማህበረሰቡ ያለው ዋጋ ከፍ ያለ እንጂ ፤ ሰው ገዳይ፣ ሌባ፣ እምነት የሌለው ሰው በጭራሽ አንቱ አይባልም። መንግስት ማለት… ብየ ትርጉም ለናንተ መናገር አልፈልግም “መንግስት…” ብላችሁ ስትጠሩት ፣ የ”ኢትዮጵያ መከ ሰራዊት…” ስትሉ በጣም በጣም…!… ያው!!.. ገባችሁ እና አደራ “አንቱታው”ና “መንግስታው” ይታሰብበት ።
በተረፈ የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቃች ሁ ፤ ያሰባችሁት ሞልቶላችሁ ባገራችን መሬት ላይ ለመስራት ያብቃችሁ።

***** ወዳጄ በበኩሌ የሚሉትን እረዳለሁ፤ እንዳሉትም እነርሱ የተከበሩ የነጻነት ታጋዮችን ሲይዙም ሆነ ሳይዙ ለከት በሌለው አንደበታቸው ሲዘረጥጧቸው አይተናል፤ ቢሆንም ግን በነርሱ ብልግና ልክ ለመውረድ ይከብዳል! አንድ ግዜ ቁልቁለቱን ከወረድን ደግሞ ለመመለስ ዳገት ነው! እና እንርሱው እንደወረዱ ይውረዱት እኛ ተከትለናቸው ባንወርድ እመርጣለሁ!