* ብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራ አልፋና ኦሜጋ በክብር ይዘከራሉ ![ነቢዩ ሲራክ]

የጀግናው አብራሪ ጀኔራል የመጨረሻ ሽኝት :
==============================

14492617_10211081275213734_3665752110631022197_nበእሳት ተፈትነው ፣ ህይወታቸውን ለሀገራቸው ክብር የሰጡት ጀግና የብርጋዴር ጀኔራል ለገሰ ተፈራ መረዶ በእርግጥም በሀዘን ላይ ላለን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያንንከመርዶም የከበደ መርዶ ሆነ ፣ የገዘፈ የተጋድሎ ታሪካቸው በመላ ሀገሪቱ ሲነገር በቅርብ የማያውቃቸውና በዝና የሚያውቃቸው ሁሉም የሀገሬ ሰው በነቂስ አዝኗል 🙁

ባለ ንስር አይኑ ብርጋዴር ጀኔራል ለገሰን ተሰማ ማን ነበሩ ?
=====================================

14601104_1266827650015981_7740646148113489087_nጀኔራል ለገሰ ተፈራ አባት አቶ ተፈራ ወልደ ስላሴና ከእናታቸው ከወ/ሮ ተናኛ ተክለ ወልድ ይባላሉ ፣ ጀኔራል ለገሰ ተፈራ ውልደታቸው አዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ሾላ ተብሎ በሚጠራው ቦታ እንደሆነ ዝክረ ታሪካቸው ያስረዳል ። ህፃን ለገሰ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በተለመደው የባህል የቄስ ትምህርትን የተማሩ ሲሆን ከዚህ ም በኋላ ቤተሰቦቻቸው ጋር ቅርበት ባላቸው ወዳጅ በነበሩት ጀኔራል አቢይ እርዳታ ኮተቤ ደጃዝማች ወንድ ይራድ ትምህርት ቤት በማስገባት ባለ ብሩህ አዕምሮውን ለገሰን ከልጆቻቸው ሳይለዩ ፍፁም በሆነ ፍቅር እንዳሳደጓቸው ይነገራል። ሐረር አካዳሚ እና አየር ሃይልም ውስጥ ለለገሰ እንዲገቡ የተመረጠላቸው በግርማዊ ጃንሆይ አማች በጀኔራል አቢይ አበበ አማካኝነት ሲሆን ወቅቱም በ1956 ዓም እንደ ነበር ዝክረ ታሪካቸው ያስረዳል !

ለገሰ የተቀላቀሉት የሐረር አካዳሚ በልዩ ባለሙያዎች የተዋቀረና የተደራጀ ብቸኛ የላቀ ወታደራዊ መቅሰሚያ ማዕከል መሆኑ ይነገራል ። ማዕከሉ እንደ እንግሊዙ ” ሳንድኽረስት ሮያል አካዳሚና” እንደ አሜሪ ካኑ ስመጥር “ዌስት ፖይንት ” ወታደራዊ አካዳሚ የጠለቀ የውጊያ ስልት፣ የአመራር እና የአስተዳደር ችሎታ፣ የአካል ብቃት በኮሌጅ ደረጃ የሚሰጡ የቀለም ትምህርቶችን፣ የወታደራዊ ሳይንስ ስነ ምግባር በማስተማር ልዩና አይነተኛ የሆኑ መኮንኖችን ከአካዳሚው ይፈጠሩ እንደነበርም ከተጻፉ ድርሳናትና በስልጠናው ካለፉ መኮንኖች በሰፊው ይጠቀሳል ። ለገሰ በሐረር አካዳሚ ስልጠና ላይ በወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር አየር ሃይል ለበረራ የሚቀበላቸው እጩ መኮንኖች በቂ የሆነ የወታደራዊ ስልጠና ያገኙ መሆን አለባቸው የሚል መመሪያ አወጣ ። ይህን መመሪያ ተከትሎ የአየር ሃይል ትምህርት ክፍል ሐረር የጦር አካዳሚ እየሄደ ሲመለምል የያኔው ተራ መኮንን ብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራ የኢትዮጵያ አየር ሃይል የሚፈልገውን መስፈርት አሟልተው ከተመረጡት መኮነንኖች መካከል አንዱ ሆኑ ። የአየር ሃይል የበረራ ት/ቤት ተቀላ ቅለው በቀጣይ አመታትም የበረራ ትምህርታቸውን ጨርሰው ክንፋቸ ውን አገኙ ፣ ለገሰም ጀት አብራሪ እና የበረራ አስተማሪ ሆነው ተመረቁ !

ጀኔራል ለገሰ ተፈራ በሀገር ውስጥ ካገኙት የበረራ ትምህርት በተ ጨማሪ ህይዎታቸው መጨረሻ ወዳረፈችበት ሀገረ አሜሪካ ተጉዘው ከፍ ያለ ወታደራዊና የበረራ ትምህርት ቀስመዋል። በተለይም በአሪዞና የአየር ሃይል ማሰልጠኛ ተቋም ከበረራ ጋር የተያያዘ መሳሪያ አጠቃቀ ምን አጥንተዋል ። በወታደራዊ ትምህርት የላቁት ለገሰ ራሳቸውን ጠብቀው የሚመገቡ በመሆናቸው ሽንቅጥ ያሉ ደልዳላ አብራሪ እንደ ነበሩ ይነገራል ። ጀኔራል ለገሰንና የየሚያውቋቸው ትከሻው እና ደረቱ ሰፊ የአየር ኃይል ደልዳላው መኮንን እያሉ ይጠሯቸው ነበር ። ለገሰ ራሳቸውን ከመጠበቅ ባከፈ በትምህርታቸው ምጡቅ ከሚባሉት ምስጉ ን ተማሪዎች መካከል አንዱ እንደነበሩ የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ ! ለገሰ በወታደራዊ የላቀ ትምህርት ብቻ ሳይሆን በሙዚቃ ፣ በስፓርት እና በሌሎችም እንቅስቃሴዎች ተሰጥዎ የተካኑ ነበሩ ።

የ ጀኔራል ለገሰ ዘመን ተሻጋሪ ገድል …
========================

ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የግዛት ዘመን ጀምሮ እስከ ደርግ አገዛዝ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ጉልህ እንቅስቃሴን በማደረግ በቀዳሚነት ከሚጠሩት ጀግኖች መካከል ብርጋዴር ጀኔራል ለገሰ ተፈራ በፈጸሙት ገድል ከቀሩት ለየት ያደርጋቸዋል ። ከፈጸሟቸው አን ጸባራቂ ገድሎች መካከል በብዙዎች ህሊና የማይጠፋው በፕሬዚደ ንት መሐመድ ዚያድባሬ የምትገዛው ሶማሊያ ኢትዮጵያ የወረረችበት ወቅት ነበር ። ጃንሆይን አሽቀንጥሮ የጣለውን አብዮት ገና የለጋ እድሜ እያለ ሀገር በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምና ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ በወደቀች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ከውስጥና ከውጭ ችግሮች ፈጠው መጡ ፣ በተለይም በሰሜን የመገንጠል ጥያቄ የሚያቀነቅኑት የለኮ ሱት ጦርነት ፣ በመካከልና በቀረው የሀገራችን ክፍል ደግሞ በተለያዩ የፖለቲካ ደርጅቶች ሽኩቻ ደርቶ አለመረጋጋት ይስተዋል ነበር ። ወቅቱም ወርሃ ሃምሌ 1969 ዓም ነበር ።

በዚህ ወቅት ነበር የሶማሌው ፕሬዚደንት መሀመድ ዚያድባሬ አለመ ረጋጋትና ውጥረቱን እንደ ድክመት በመቁጠር በውጭ ጠላቶቻችን ” አይዞሽ ” ባይነት ሶማሊያ ኢትዮጵያን ወረረች … ሶማልያ አውጥታና አውርዳ እጅግ ብርቱ የጦር መሰናዶ አድርጋ በዘመተችበት ዘመቻ የተደ ራጀ የአየር ኃይልና የምድር ጦር ስለመኖሯ እንጅ ከኢትዮጵያ አንጻር የሚጠብቃትን ምላሽ ያሰበችው አልነበረም ። እናም ያላሰበችው ፈተና ገጠማት ፣ ባለ ንስር አይኖቹ ጀግና የአየር ኃይል አብራሪዎች ከሰማይ ፣ አነጣጥሮ ተኳሾቹና ቁጡ አንበሶቹ የምድር ጦር ጀግኖች በአጭር ታጥቀው እስከ አፍንጫዋ የታጠቀችውን ሶማሊያን ገጠሟት ፣ ቆፍጣ ኖቹ እንደ አንበሳ እያጓሩ እንደ ነበር እየተፈነጠሩ የሶማሊያን ወራሪ ልክ ልኳን ሰጧት ፣ ሶማሊያ የሃፍረት ማቅ ለብሳና ዋጋዋን አግኝታ ፣ አከርካ ሪዋ ተሰብሮ ወደ መጣችበት ተባረረች ! የሶማሌን ወራሪ አከርካሪ ይሰብሩ ከነበሩት ጀግኖች መካከል ደግሞ በአየር ላይ ዘመቻው የብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራና የጓዶቻቸው ውሎ ፍጹም ወደር ያልተገኘላቸው ነበር . ..

በወቅቱ በብዛትና ጥራት ከፍ የበላይነት ይዛ የተሰለፈችው ሶማሊያ ብትሆንም ፣ በምጡቅ ልጆቿ ተጋድሎ የነበረው እንደልነበረ በተደረገ በት አገርን ከወራሪ የመታደግ ተጋድሎ የጀግናው አየር ሃይል ዘጠነኛው ስኳድሮ ተዋጊ ባልደረባ የነበሩት ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ እና ጥቂት ጓዶቻቸው ሰማዩን ተሚቆጣጠሩ ፣ የማይያዙ የማይጨበጡ ተዋጊ ጄት አብራሪዎች ነበሩ ። የብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ የዘጠነኛው ስኳድሮ ተዋጊ ባልደረባጓዶቻቸው በሶማሊያው ጦርነት በፈጸሙት ተጋድሎ እሰከ ድሬድዋ ዘልቆ የገባውን እብሪተኛ የሶማሌ ጦር ዶግ አመድ ማድ ረግ ችለው ነበር ። በተለይ ጀኔራሉ ለገሰ ከዘጠነኛው ስኳድሮ ተዋጊ ባልደረቦቻቸው ጋር በቅንጅት ተዋግተው ወራሪው የሶማሌ አየር ኃይል ጀት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት አደርሰው ጠላት እንዲያፈገፍግ አድርገዋል ። ብ/ ጀኔራል ለገሰ በዚህ የጦር ውሏቸው እስከ አምስት የሚደርሱ ጀቶችን ያወደሙበት የጦር አውድማ ታሪክ ድንቅ ከተባሉት መካከል ይጠቀሳል …

ዘጠነኛው ስኳድሮ ተዋጊ ባልደረባ አብራሪው ብ/ጀኔራል ለገሰ በተከታታይ ድብደባ የተሰጣቸውን ኢላማን በማደባየት ላይ እንዳሉ በአንዱ ቀን በጠላት ኢላማ ውስጥ ወደቁ ፣ ጠላትን ያደባዩባት ጓዳ ቸው ያች የሚወዷት ጀት ተመታች ፣ በታጠሩና በጨነቀው ሰአት ጀቶ ችን እርስ በእርስ በማጋጨት የሚያወድሙት አሻግረው በሚሳየል የሚ ያደባዩት ጀግና ጀታቸው ተመታ ስትወድቅ እርሳቸው በዣንጥላ በጠላት መሬት አረፉ ! ጀግናው በጠላት እጅ ወደቁ ፣ የጀኔራል ለገሰን ጀት አል መው መትተው ፣ ጀኔራሉን በምርኮ የያዙ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለስ ልጣናት ጮቤ ረገጡ ፣ እናም ከተያዙበት ቀን ጀምሮ ለ11 ዓመታት የጦር ምርኮኛ ሆነው በሶማሊያ ወህኒ ለእናት እትዮጵያ ፍዳን የተቀበሉ ጀግና ቢኖሩ ባለ አንጸባራቂ ድሉ ብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራ ናቸው !

የመንግስት ለውጥ መምጣቱን ተከትሎና ከህመም እክል ጋር ወደ ምድረ አሜሪካ ያቀኑት ጀግናው ጀኔራል በቀድሞው የአየር ኃይልና በመላ አለም የሚገኙ አድናቂ አፍቃሪዎቻቸው ለምንወዳት ሀገራችን ለከፈሉት ከባድ መሰዋዕትነት ተደጋጋሚ ምስጋናና የክብር ሽልማት የተሰጣቸው ጀግና ነበሩ ! አኩሪ ገድልን የፈጸሙት ብ/ጀኔራል ለገሰ ከወጣትነት እስከ ጎልማሳነት እድሜ የእናት ኢትዮጵያን የአየር ክልል ሳያስደፍሩ ካቆዩን የቁርጥ ቀን ልጆች ጋር ሀገራችን ከነክብሯ አስረክ በውናል ፣ በተከፈለው ከባድ መስዋዕት ልክ ሃገርና ህዝብ ውለታ ካልከፈልናቸው ባለውለታዎቻችን አጋፋሪው የጦር ገበሬ ከሀገራቸው ርቀው በስደት እስከ ወዲያኛው አሸልቧል !

የጀግናችን የመጨረሻ ስንብትና ሽኝት ሀገር በክብሯ ሆና ፣ ኢትዮጵያ የወራሪን ጦር አከርካሪ ለሰበረ ጀግናዋ ነገሪት ጎስማና ለክብራቸው መድፍ ተኩሳ የምትከውንበት ጊዜው ዛሬ ባይሆንም ጀግናችን አዘክ ረን እያለቀስን ሳይሆን እያመሰገንን እንሰነባበት ዘንድ ግድ ሆኗል … !

ክበር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን ፣ ብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራ አልፋና ኦሜጋ ከትውልድ ትውልድ በክብር ይዘከራሉ !

ነፍስ ይማር !

ነቢዩ ሲራክ

መስከረም 27 ቀን 2009 ዓም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.