የሕዝብ ጥያቄ ካልተመለሰ አመጹ አይቆምም – የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉብዬ

blue_party_ethiopia101370869814-1የሰማያዊ ፓርቲ ትላንት መስከረም 28 ቀን ጠቅላላ ጉብዬ አድርጎ በኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ቦታ ለሁለት አመት በወህኒ ሲሰቃይ የነበረዉን በፓርቲው አባላት አካባቢ ብቻ ሳይሆን በአንድነት የለዉጥ ሃይሉ ዘንድ ተቀባይነት ያለውን የሺዋስ አሰፋን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።

ጠቅላላ ጉቤው የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ በመግለጫው በአማራው ክልል እና በኦሮሚያ የተነሳው ተቃዉሞ ምክንያቱ የዉጭ ሃይሎች ሳይሆን ላለፉት 25 አመታት በሕዝቡ ትከሻ ላይ የተጫነ የግፍ ቀንበር እንደሆነ አስቀምጧል። ሕዝቡ “እኔ ከሌለሁ ሀገር ትበታተናለች” የሚለው የህወሃት/ኢሒአዴግ ሟርት እንደማይቀበል የገለጸው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ለሕዝብ ጥይቄ ተገቢው ምላሽ ካልተገኘ ህዝባዊ አመጹ በጭራሽ እንደማይቆም አስጠንቅቋል።

ገዢው ፓርቲ ሰላማዊ ተቃዉሞ ባነሱ ዜጎች ላይ መተኮሱንና መግደሉን፣ ማሰሩንና ማፈናቀሉን በአስቸኳይ እንዲያቆምና የመከላከያ ሰራዊት ተግባር የሀገርን ዳር ድንበርና ሉዐላዊነት መጠበቅ መሆኑን ተገንዝቦ አገዛዙ በአስቸኳይ ወደ ጦር ካምፑ እንዲመለስ፤ እስከ አሁን የተገደሉና የተጎዱ፣ የተፈናቀሉና የተንገላቱ ወገኖቻችን ጉዳይ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ። ለዚህ ጥፋት ትእዛዝ የሰጡ ባለስልጣናት ለሕግ እንዲቀርቡ፤ ከሕዝብ ጋር በመወያየት በአስቸኳይ ስልጣኑን ለሕዝብ የሚያስረክብበትን መንገድ እንዲያመቻች የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉብዬ ባወጣው የአቋም መገልጫ ጠይቋል።

ፓርቲው  በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያገባኛል ከሚሉ ማናቸዉም ኢትዮጵያዉይን ወገኖች ጋር ተቀራረቦ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ ስለሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይም አዎንታዊ መፍትሄ የሚያስገኝ ዉይይት እንዲጀመር ጥሪውን አቅርቧል።

በኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አመራር የሰማያዊ ፓርቲ በርካታ አዎንታዊ ውጤቶች ያስመዘገብ ድርጅት ሲሆን፣ በብዙዎች ዘንድ ከሚወቀስበትና ከሚተችበት አንዱና ትልቁ ምክንያት የተናጥል ትግል የማድረግ ዝንባሌዉና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት አለመቻሉ ነበር። አዲሱ አመራር ፣ የፓርቲውን ጥንካሬ ጠብቆ፣ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ሶሊዳሪቲ በመፍጠር በመታገሉ ዙሪያ ወደ ኋላ የሚጎተት ሳይሆን በቀዳሚነትና በአዝማችነት የሚንቀሳቀስ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉብዬውን ያደረገው በመላው የኢትዮጵያ አንድነትድ ድርጅት (መኢ.አድ) ጽ/ቤት ሲሆን ይሄም በሰማያዊና በመኢአድ መካከልም ከወዲሁ መግባባቱ እንደተፈጠረ  የሚያሳይ ነው።

ሙሉው መግለጫ እንሆ

 

14600972_1222880537753202_5240264295403672810_n

14517450_1222880567753199_8500517059258935502_n

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.