ለመሞት እያጣጣረ ያለውን የወያኔ ሰው በላ ስርአት ተጨማሪ ጥፋት ከማድረሱ በፊት ተባብረን ወደግብአተ መሬቱ እናደርሰው ዘንድ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥሪያችንን እናቀርባለን

ጃዋር ሞሃመድ

jawar-mohamedወያኔ ከኦሮሞ ከአማራና ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች የተነሳበትን ከፍተኛ ተቃውሞ ማስቆም ባለመቻሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጎ ታጣቂዎቹን ለመጠነ ሰፊ ግድያና አፈና አሰማርቷል። ይህን የወያኔ ሴራ ለማክሸፍና ለመመከት ሁሉም ወገን በአንድ ልብ ሊነሳ ይገባል። በሁሉም አካባቢ የሚገኙ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለመጨረሻው የሞትና የሽረት ትግል ራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል። በአገሪቱ አምባገነናዊ ሥርአት ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዶ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት የሚስተናገዱበት ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመመስረት በጋራ የምንነሳበት ወቅት ላይ ደርሰናል። በመሆኑም ለመሞት እያጣጣረ ያለውን የወያኔ ሰው በላ ስርአት ተጨማሪ ጥፋት ከማድረሱ በፊት ተባብረን ወደግብአተ መሬቱ እናደርሰው ዘንድ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ሞት ለወያኔ!!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.