ከህወሃት የጨለማ ዘመን ቦኋላ፡ የነጻነት ጸሓይ ትወለዳለች [ከሙሉቀን ገበየው]

ላለፉት 25 አመታት ኢትዮጲያችን  በጨለማ ነገስታት  ዘራፊዎችና የሰው አጋንንቶች  ስትገዛ ቆይታለች። የፍጻሜው ዘመን ሲደርስም የጨለማው አገዛዛቸው ይባሱኑ ብሶበታል።

freedom-ethiopia-satenaw-newsየጥቂቶቹ ምርጥ ስብስብ የሆነው ጸረ-ዲሞክራሳዊው ሕወሃት፡የኢትዮጲያውያንን ለነጻነት የሚያደርጉትን  ትግል ለማፈን የሚጠቀምበት የማታለያ ዘዴው ሁሉ እያልቀበት ነው። አዲሱ ትውልድም ነቅቶ ተጠንቅቆ እየታገለው ነው። እድሜውን ለማራዘምና የአዲሱን ትውልድ ትግል ለማፈን የቀረችውን የመጨርሻ የሆነውን ዘዴ፡ የአስቸካይ ግዜ መንግስት  ( Emergency State) ሰሞኑን ደንግጎ የስቃይ አበሳውና የግድያ ሱሱን ቢቀጥልም የራሱን የመጨርሻ ዘመን ከማፋጠን ሌላ የሚፈይደው ነገር የለም።

ሰሞኑን ከፕሮፓጋንዳ መስሪያ ቤቱ በእጅ የሚዳሰሱ ቅጥፍቶችን እየነዛ ይገኛል። ፓርላማ ከሚለው የእንቅልፍ ምክር ቤትም፡ የማታለያ ተስፋዎችን እየመገበን ይገኛል። መቼም ቢሆን ህዝቡ የወያኔን ቅጥፈትና የሃሰት ተስፋ መምገብን በድንብ ለምዶታል።

በ1997  ቀጣፊው ህወሃት የአውሮፓ ሉእኳንን  በእጅ በእግራቸው ገብቶ  ከቅንጅትና ከህብረት ፓርቲዎች ጋ አስማሙኝ፤ ከጸሃይ በታች ላለ ነገር ሁሉ እደራደራለሁ ብሎ አዝናግቶ፤ በትንሽ ቀናት ውስጥ የቅንጅት መሪዎችን ሁሉ ሰብስቦ እስር ጣላቸው። ከዚያ ቧሃላማ እንደ ቆሰልች ነበር ሆኖ ለአስራ አንድ አመት ዘለቀው።  የነበሩትን ጋዜጦች፣ ተቀዋሚ ፓርቲዎች፣  የሰውን መብትና አገር አስተዳደር  በማስተማር  ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶችን ሁሉ አጥፍቶ፤ በጠፈጠፋቸው የሃሰት ተቀዋሚ ፓርቲዎች ተከቦ፡ ዙፋኑ ላይ ፊጥ ብሎ ከረመ።   ለመሐተም መምቻነት የሚጠቀምበትን ፓርላማ ተጠቆሞ  ሁሉን ቀርፍዶ የሚጋዛበትን የጸረ-ሽብርተኝነት ህግ አውጆ  ሁሉን ነገር ተቆጣጠረ።

ወገኖቼ፣ በተለይ አዲሱ ትውልድ ከዚህ ትልቅ ትምህርት ተማር። ወያኔ የሚቅባጥራቸ የውሸት ተስፋዎች ሁሉ ጊዜ ለመግዣ ነው። ከዚያ ወደያ  ለለመደው አስከፊ አገዛዝና የጨለማ ዘመን ውስጥ ሊከትህ ነው።

ስለነጻነትህ እርግጠኛ የምትሆነው ህወሃት ስልጣኑን ሲለቅ ብቻ ነው።

ወገኖቼ ኢትዮጲያውያን፤ ህወሓት በአሁኑ ግዜ ቆስሎ በሙት አልጋ ላይ ሆኖ እያጣጣረ ነው። አስቸካይ ግዜ መንግስት ብሎ በአወጀው አየር (ኦክሲጅን) እየታገዘ ነው። ያለችውም አየር  እያለቀቸበት ነው። አልጋው ላይ እያጣጠርም  ለእርቅና ንግግር የሰላሚዊ ሽግግር አሻፈረኝ ብሎአል። የስልጣን ጥሙ  አሳውሮትና አሳብዶት የኢትዮጵያውያን ግፍ፣ በደልና የነጻነት አምሮት አልታይ ብሎታል።

ኢትዮጲያን ሆይ፤  ይህን እውንታ አውቀን የጸረ-ህወሃት ትግሉን አፋፍመን መቀጠል አለበን። ህወሃት፡ ገድል አፋፍ ላይ ስላለ   ዘረ፣ ሃይማኖት፣ ጾታ፣እድሜ፣የአካል ብቃት፣ ሃብት፣ የትምሀርት ደርጃ ሳንል ተባብርን መገፈተርና ፍጻሜውን ማድረስ  አለብን።

የመንግስት ሰራትኛ ሆይ፤ ለመብትህ ለነጻነትህ ተነስ። የስራ አድማ አድርግህ የወያኔን አከርካሪ አጥንት አሽመደምድው።

ተማሪዎችና መምህራኖች።  ወያኔ  ለነፈጋችሁ የሰበአዊ   መብትና የእኩል ዜግነት ተነሱ። እናንተን አግልሎ  የተለየ ጥቅማጥቅሙን  “ለምርጦቹ ና ለደጋፊዎች” አድርጎታል።

ዲፕሎማት ሆይ።  ከህወሃት  ሚሲዮኖቹ አገልጋይንት ውጡና ህዝባችሁን ተቀላቀሉ። የወያኔ ወንጀልንና የክፋት አድራጎት  ለአለም  አስታውቁ ፤ አጋልጡ።

ነጋዴዎች ሆይ፤  እናንተን ከውድድር ሜዳ አስወጥቶ በጉልበቱ ተመክቶ በዘራፊ ካንፓንዎቹ (እንድ ኤፈርት ያሉ) እየተጠቀመ የአገሪቱን ንግድ ሁሉ ተቆጣጥሮ  አስችግሮትኋልና ለመብታችሁ ተነሱ።

የፖሊስ ሰራዊት ሆይ፡ አንተን እየተጠቀመ ወንድምህን  እንድታስር፣ በሃሰት እንድተከስ ፣ እንዲሁም እንድትገድል የሚያደርገህን ይህን ግፍኛ ህወሃት እንቢ በለው።

የአገር መከላከያ ሰርዊት ሆይ።  ያነተ ድርሻ አገር ሊወር የመጣን የውጭ ወራሪን ሰራዎት መመከት እንጂ ወንድምህን ግደል ሲልህ አይሆንም በለው።  እንደ እንሰሳ ልንዳህ የሚለወን የ ህወሃት ጂኔራሎችና የበላይ ሹሞች ላይ ጠምንጃህን አዙር እንጂ ወገነህን አተንካ። ሰከን በል።

የሃይማኖት አባቶች ና መሪዎች ሆይ፤  ስለ እውነት ቁሙ። ስለ ፈጣሪ ‘በጎች’ ቁሙ። የሚደርሰውን በድል ይቁም በሉ። ለሐይማኖት ተከታይ ልጆቻችሁ እግዚሃቤር የሰጣቸውን መብት ሲነፈጉ፣ ሲጨፈጨፉ አይሆንም በሉ።በከፋፋዩ፣ ባርመኔው፣በገዳዩ  ህወሃት ላይ ተነሱ።

ገበሬ ዎች ሆይ፤ መሬታችሁን ነጥቆ  ለራሱ ባደርገው ህወሃት ላይ ተነሱ። የተሻለ ገንዝብ ሲያይ ለውጭ ዚጋ መሬታችሁን ሽጦ በምሬታቹህ ላይ ‘ባርይ’ እንድትሆኑ በሚያደርጋችሁ ወያኔ ላይ ተነሱ። በእግዚሃቤር ጸጋ በላባችሁ የምታመርቱብትን መሬት ስትሉ ወያኔን በቃ በሉት።

ጋዜጠኞች፣ ጸሃፊያን፣ የሚዲያ ሰውች ሆይ፤ ስለ ህዝባችሁ፣ ስል ሃገራችሁ ስትሉ አገራችንን  የውስጥ ቅኝ ግዛት በያዛት ህወሃት ላይ ተነሱ። እራሳችሁንና አካባቢያችሁን እንዳትገልጹ  መብታችሁን በነፍጋችሁ ወያኔ ላይ ተነሱ።

ሙሁራኖች ሆይ፤  በስቃይ ላይ ያለውን ወገናችሁን አግዙት። መንገዱን፣ ህወሃትን ማፈርሻ ስልቱን ለህዝባችሁ አስተመሩ።ዘዴወን፣ መፍቴውን የተሻለ አገር መገንቢያ ሂደቱን ጠቁሙት።

ተቀዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ሆይ፤ በመካከላችሁ ያለውን ልዩነት አጥቡ ና በጸረ-ወያኔ ትግሉ ተባበሩ። በህወሃት የማታለያ ድራማ አትከፋፈሉ። ስለ ህዝባችሁና አገራችሁ ስትሉ ተነሱ። ወገናችሁን ምሩት፤ መንግዱን አሳዩት።

ከሁሉም ጎሳ የተወለድን ኢትዮጲውያን ሆይ፤ ኢትዮጲያ አገራችን የለቅሶና የዋይታ የሞት አገር ሆናለች። እናቾት ያለቅሳሉ፡ ወጣቶች የፊት ተስፋቸውን ተነፈጉ። የህወሃትን አስከፊ ወረራና አገዛዝ እንድጥንቱ አባቶቻችን ተባብርን እንመክተው። እግዚሃቤር የሰጠንን ነጻነታችንን  እናስከብር። በህወሃት ላይ ተነሱ!

በርግጥ በህወሃት አገዛዝ ጨለማ ውስጥ ነን ግና አዲሱ ትውልድ በለኮሰው የነጻነት ችቦ ብርሃን እያየን ነው።

እነሆ ከህወሃት የጨለማ አገዛዝ ዘመን ፍጻሜ ላይ ነን፡ የነጻነት ጸሓይም ትወለዳልች።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.