በሰሜን ግጎንደር በርካታ የሕወሃት ታጣቂዎች እየሞቱ ነው – ሠበር ዜና

gonder-343-satenaw-news

ሕወሃት በአገሪቷ እየተባባሰ የመታዉን ቀዉስ መቆጣጠር ካለመቻሉ የተነሳ የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል። አዋጁ ችግሮችን የበለጠ የሚያወሳስብና አገሪቷን ወደ ከፋ ደረጃ ሊወስድ እንንደሚችል የሃይማኖት አባቶችን ጨመሮ በርጋታ ዜጎች ከተለያዩ ማእዘናት በመናገር ገዢው ፓርቲ ለብሄራዊ እርቅ እንዲዘጋጅና የአገሪቷ ችግሮችን በሰላምና በዉይይት እንዲፈቱ ጥሪ ኡቀረቡ  ሆኖም። በኢሕሕአዴግ ዉስጥም ያሉ አንዳንድ ወገኖችም ኢሕሕአዴግ ከሃይል እርምጃ ተቆጥቦ የሕዝቡን ጥያቄ እንዲመለስ ግፊት እይደረጉ ነው። በተለይም ከብአዴን አካብአብኢ። የብዴን ም/ሊቀመንነበር  እና የአማራው ክልል አስተዳዳሪ አቶ ገዱ አንዳርጋችው “ችግሮችን በመከላክላያ፣ በፖሊስ፣ በደህንንነት ሃይል መፍታት አይቻልም። ህዝቡን አልብሮ፣ ሕዝቡን ማነጋገርና ሕዝቡን ምዳመጥ ነው ብችኛው መፍትሄ”  ሲሊም በዓደባባይ መናገራቸው የሚታወሰ ነው።

አዋጁ ከወጣ ጀምሮ ችግሮኢች የበለጠ ትባባሱ እንጂ የቀነሰ ነገር የለም። በጂማ፣ በደብረ ማርቆስ ተማሪዎች አንምርም ብለዋል። በባህር ዳር በአስደናቂኦ ሁኔታ የሥራ ማቆም አድማ እየተደረገ ነው። በሰሜን ጎንደር፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመታከክ በዚያ  አካባቢ ያለውን ማህበረሰብ ትጥቅ ለማስፈታት የተደረጉ ሙከራዎች ወደ ተለየ አቅጣጫ እየሄዱ ነው። ክዚህ ጋር በተገናኘ በርካታ የአገዝዙ ታጣቂዎች ሕይወታቸውን እያጡ እንደሆኑ ዘግባዎች ያሳያሉ።፡በዚህ ጉዳይ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ምንጮቹን ገልጾ የሚከተለውን ዘግቧል፡

#የአማራ_ተጋድሎ፡ ሰበር ዜና

በታችና ምዕራብ አርማጭሆ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 በላይ የወያኔ ጦር አባላት ተገድለዋል።

ከትናንት ጀምሮ በታችና ምዕራብ አርማጭሆ የተለያዩ አካባቢዎች የዐማራውን መሣሪያ መቀማት በሚል የወያኔ ጦር በዐማራው ገበሬ ላይ ይፋ ጦርነት ገጥሟል፡፡ በታች አርማጭሆ ዶጋው አካባቢና በምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ አካባቢ ከ50 በላይ የወያኔ ወታደሮች ተገድለዋል፡፡

አበራ ጎባው እና ደጀኔ ማሩ የተባሉ አርበኞችን ቤት በድንገት በመክበብ ለመግደል ሙከራ ያደረገ ቢሆንም በአካባቢው ተሰልፎ የነበረው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ መውደሙን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ አንድ አርበኛ ከዶጋው አካባቢ ጉዳዩን አስመልክተን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹የዛሬው ከበድ ያለ ጦርነት ነበር፤ 8፡00 አካባቢ መጥተው የደጀኔ ማሩን ቤት ከበው ለማፈን ባደረጉት ሙከራ የወያኔ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ አመድ ሆነዋል›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የሞቱ የጠላት ወታደሮችን በተመለከተ ደግሞ ‹‹ኧረ የሚሞተውን ወታደር በተመለከተማ ስንቱን ቆጥረነው! በየጫካው አይደል ተፈንድሶ ተፈንድሶ የምታገኘው! እንዴው ገምት ካልከኝ አሳንሼ ቁጥሩን ከ50 ይበልጣል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በጎንደርና በጎጃም የዐማራ አካባቢዎች በተወሰነ መልኩ ሰላማዊ የሆነ ቢመስልም ወያኔ የገበሬውን መሣሪያ እቀማለሁ በማለቱ ምክንያት እንደገና ሰላሙ ደፍርሷል፡፡ በሰሜን ጎንደር የአርማጭሆ፣ የጠገዴና የወልቃይት አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ አለመኖሩን ነው ምንጭቻችን የሚገልጹት፡፡

የመሣሪያ ትጥቅን ማስፈታት በተመለከተ በወያኔ መንግሥት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በዋናነት የአርማጭሆና የወገራ አካባቢዎችን ቁጥር አንድ አድርጎ ፈርጇቸዋል፡፡
(ዝርዝር መረጃዎችን በየጊዜው እየተከታተልን ማቅረባችን ይቀጥላል)

የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል/

© Muluken Tesfaw

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.