1 ሺህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን እስር ቤት አመለጡ

አዲስ አድማስ

– የወህኒ ቤቱ ጠባቂዎች እስረኞቹ እንዲያመልጡ ትብብር አድርገውላችዋል

african_refugees_protest  በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ገብተዋል በሚል በደቡባዊ የመን በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ታስረው የነበሩ 1 ሺህ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ባለፈው ረቡዕ ሌሊት አምልጠው መጥፋታቸውን አንድ የአገሪቱ የደህንነት ሃላፊ ማስታወቃቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
በህገወጥ መንገድ ወደ የመን ገብተዋል በሚል ሻባዋ በተባለቺው የአገሪቱ ግዛት ውስጥ ታስረው ከነበሩትና ወደ አገራቸው ሊመለሱ ከተዘጋጁት 1 ሺህ 400 ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል አንድ ሺህ የሚሆኑት ባለፈው ረቡዕ ሌሊት እስር ቤቱን ሰብረው በመውጣት መጥፋታቸውን ዘገባው ገልጧል፡፡
የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ስደተኞቹ እንዲያመልጡ ትብብር እንዳደረጉላቸው ተረጋግጧል ያለው ዘገባው፤ ስደተኞቹ በተቀናበረ መንገድ ካመለጡ በኋላም በተዘጋጀላቸው መኪና በቡድን በቡድን እየሆኑ በአቅራቢያ ወደሚገኙት ማሪብ እና ባይዳ የተሰኙ ግዛቶች መሄዳቸውን አስታውቋል፡፡ የየመን መንግስት ባለፈው ወር ብቻ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ገብተዋል በሚል ከ220 በላይ አፍሪካውያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ አገራቸው እንደመለሰ ያስታወሰው ዘገባው፤ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ጠቁሟል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.