በሰሜን አሜሪካና ካናዳ የሚንገኝ የወላይታ ተወላጆች:  በወቅታዊ የሀገራችን አሳሳቢ ጉዳዮችን አስመልክተን የተሰጠ መግለጫ

ቀን ጥቅምት 6, 2008     ኦክቶበር 16, 2016

welyta-2-satenaw-newsእናት አገራችን ኢትዬጵያ የበርካታ ህዝቦች መኖርያ የሆነች ጠንካራ ሃይማኖቶች፤ ጥንታዊ ቅርሶችና፤የበለጸገ ታሪክ ያላት፤ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት ናት። በኢትዮጵያችን ከሚኖሩ ህዝቦች አንዱ የሆነዉ የወላይታ ህዝብ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲሁም ለህዝቦች የጋራ መኖር ከፍተኛ አስተዋኦ ሲያደርግ የቆየ በደቡብ የሃገራችን ክፍል ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ህዝቦች አንዱ ነው። ከታሪክ እንደምንረዳው ወላይታ የሚለዉ የብሄረሰብ መጠርያ በወላይትኛ ቋንቋ “ወላሄታ” ወይም በአማርኛ “የተቀላቀለ” ከሚለዉ ቃል የተገኘ ሲሆን ይህም የወላይታ ህዝብ አንድ ዘዉግ ወይም የዘር ግንድ ሳይሆን ከኦሮሞ፤ ከአማራ፤ ከጋሞ፤ ከዳዉሮ፤ ከትግራይ፤ ከሃድያ፤ ከሲዳማ፤ ከአፋር፤ ከሶማሌና፤ ከተለያዩ አካባቢዎች በንግድ፤ በጦርነት፤ በጋብቻ፤ በስደት፤ ወዘተ የመጡ ሰዎች አካባቢዉን በለምነቱና ለኑሮ አመቺ በመሆኑ መርጠዉ ቀደም ሲል በስፍራዉ ይኖሩ ከነበሩ ሰዎች (natives) ጋር ተዋህደዉና ተዋልደዉ በአንድ ወላይትኛ ቋንቋ ተጠቅመው ጠንካራ ባህል ገንብተው የራሳቸዉን ንጉስ ተጠቅመው ቤተ መንግስት፤ የጦር ሃይል፤ የፍርድ ስርዓት፤ የመገበያያ ገንዝብ ፈጥረው ለብዙ ዘመናት የኖሩበት አካባቢ ነዉ።

በጥንታዊት በኢትዬጵያ አንዱን ንጉስ ሌላውን ንጉስ ለማስገበር አንደኛው መንገድ ጦርነት በመሆኑ በወቅቱ አፄ ምኒሊክ ማዕከላዊ መንግሥት ለመመስረት በነበራቸው ህልምና ምኞት ለማዕከላዊ መንግሥት  በሰላም አንገብርም ያሉትን በጦርነት ማስገበራቸው ይታወቃል ። በሄሆኑም የወላይታን ህዝብ ለማስገበር ጦርነት ከከፈቱ በኋላ በወቅቱ የወላይታ ንጉስ በነበሩት ንጉሥ ጦና የሚመራ የወላይታ ጦር 6 ጊዜ የሚኒሊክን ጦር አሸንፎ አባረረ። በዚህ ሽንፈት የተናደዱት አፄ ሚኒሊክ ራሳቸው ጦራቸዉን አጠናክረው በራስ አሉላ አባነጋ አዝማችነት ለ 7ኛ ግዜ ከወላይታ ህዝብ ጋር ተዋግተዉ በማሸነፍ ነጉስ ጦናን ማርከዉ የወላይታን ህዝብ ለማእከላዊ መንግስት አስገብረዋል። ጦርነቱ በህዝቡ ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ ከመሆኑ በላይ ሃብትና ንብረቱን ዘርፈዉ በአፄ ሚኒሊክ ፈቃድ የጦር ምርኮኞችንና ጉልበት ያላቸዉን ማንኛዉንም የወላይታ ተወላጆች ሠራዊታቸው የዘረፈዉን ንብረት አሸክመው እንዲወስዷቸው ተደረገ። በዚህም ሁኔታ በርካታ ወላይታዎች በመላዉ ኢትዮጵያ እንዲብትኑ ተደርጓል።ለመጥቀስም ያክል አዲስ አበባ ሲቆረቆር ከነበረዉ ነዋሪ ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የወላይታ ተወላጆች ነበሩ ። በደሴና አንዳንድ የኢትዮጵያ ከተሞችም የወላይታ ሰፈር እየተባሉ የሚጠሩት በጦርነቱ ተማርከዉ የተወሰዱት የወላይታ ተወላጆች ይኖሩበት የነበሩባቸዉ ሠፈሮች መጠርያዎች ናቸዉ።

አፄ ምኒሊክ ንጉስ ጦናን ማርከዉ ከወሰዱ ብኋላ የክርስትናን ሀይማኖት እንዲቀበሉ በማድረግ በመጥመቅና የክርስትና ስም በመስጠት ከእሳችዉ በፊት የወላይታ ነጉስ የነበሩት አማዶ ያገዱትን  የክርስትና እምነት ወደ ወላይታ እንዲገባየልዑላን ቤተሰብ የነበረችዉን “ሸዋንግዬ” የተባለችዉን ሴት ለንጉስ ጦና በመዳር የወላይታ ባላባት እንዲሆኑ መልሰዉ ልከዋቸዋል። የወላይታ ህዝብም ንጉሥ ጦናን ከተቀበለ በኋላ እንደሚስት ሆና አንድ ላይ የተላክችዉን ሴት “ሸንገቴ” ብለዉ ይጠሯት ነበር። የወላይታ ህዝብም የጣልያንን ወረራ ለመመከት በአድዋ ጦርነትንና  በግንባር ቀደምትነት በአዝማችነትና ዘማችነት ተዋግቷል ፣ የወላይታ ህዝብ በተለያዩ ወቅቶች ታሪካዊ ጠላቶቻችን ሃገራችንን ሲወሩ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ተዋድቋል። በቅርቡ ኢሃዴግ ደርግን አሸንፎ የኢትዮጵያ ሰራዊትን ሲበትን በተካሄደዉ የቀድሞ ሠራዊት ምዝገባ የት እንደገቡ ያልታወቁትንና በጦርነቱ የተሰዉትን ሳይጨምር በቀይ መስቀል የተመዘገቡት ከተራ ወታደር እስከ ከፍተኛ መኮንን 75ሺህ የወላይታ ልጆች በመከላከያ ሠራዊትነት የኢትዮጰያን አንድነትና ዳር ድንበር ሲያስክበሩ ቆይተዋል። በቅርቡም ህወአት/ በኢሃዴግና በሻቢያ መካከል በተካሄደዉ ዉጤት አልባ የባድሜ ጦርነት ከ 10ሺህ በላይ የወላይታ ልጆች ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር በመሆን ትዋግተዋል።

የዛሬ ሃምሳ በዓመት ገደማ ለለም መሬትና ለተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከጎንደር ፣ ጎጃም ፣ ከሸዋና ወሎ አካባቢዎች የመጡ ወገኖቻችን ወላይታ ውስጥ በአባያ ኃይቅ ዳርቻ አበላ በምትባል ለም አካባቢ ሰፍረው እዝያው ወልደው ፣ ተጋብተውና ከብረው ሃብትም አፍርተው ቋንቃውንም ለምደውና የራሳቸውንም ነዋሪውን አስለምደው እስከዛሬም ተባዝተው መኖራቸውና እንደዚሁም በሥራ ዝውውር የመጡ በርካታዎች ሁሉ ህዝቡንና አገሩንም በመውደድ ቤታቸው ማድረጋቸው የወላይታ ህዝብ ለኢትዬጵያዊነት ትስስርና አብሮነት ተምሳሌት  ስለመሆኑ ጥሩ ማሳያ ነው።

ዛሬም ታሪኩን አስከብሮ  ለዓመታት የተነዛውን የዘረኝነት አባዜ በመዋጋት ከሁሉም ወገኖቹ ጋር በትስስርና በፍቅርእንደሚቀጥል ሙሉ እምነታችንን ነው።

ከላይ ያስቀመጥነዉ የወላይታ ህዝብ ታሪክ የመጥፎም ሆነ የጥሩ የኢትዮጵያ ታሪክ አንዱ አካል መሆኑንና ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር የአክሱም ሀዉልት ለወላይታ ምኑ ነው ብለዉ የተናገሩት ለወላይታ ህዝብ ከፍተኛ ስድብ መሆኑን ለመጥቀስም ጭምር ነው።

፩  በወያኔ አኢሃዴግ የሚመራው በወላይታው የኢሃዴግ ክንፍ “ወህዴድ” በወላይታ ህዝብ ላይ ያደረሰው ግፍና በደል

1ኛ) 1985 በአረካ ገበያ ላይ ተኩስ በመክፈትና የእጅ ቦንብ በመወርወር ከ 100 በላይ ንጹሃን ዜጎች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ አካለ ስንኩል ሆነዋል። ይህም ሆኖ ወያኔ ወንጀለኞችንና ገዳዮችን ፈጥኖ ከአካባቢው እንዲሰወሩ በማድረግ ለሞቱትም ሆን ለቆሰሉ ተጠያቂ ሳይኖር በዋዛ ቀርቷል፤

2ኛ) በ 1991 ወጋጎዳ የተባለ በ 4 ቋንቋዎች የተዳቀለ አዲስ ቋንቋ በመፍጠር በሰላም ይማር የነበረዉን ተማሪና ወላጅ በማሸበር ከአጎራባች ጋሞና ጎፋ ህዝቦች ጋር ከማጋጨቱም በላይ በከፍተኛ የመንግስት ወጪ መጽሃፍ በማሳተም ህዝቡ በግድ አዲስ ቋንቋ እንዲማር ጫና በመፍጠሩ የወላይታ ህዝብ እምቢ በማለትና የዞን መስተዳድር ደረጃ ለመጠየቅ ሰልፍ በመውጣቱ የአጋዚ ጦር ታዞ የወላይታ አውራጃ ዋና ከተማ የሆነችዉን ሶዶ አፍንጫው በታጠቀ ሰራዊት በመክበብ የወላይታን ህዝብ ጨፍጭፏል፤ መምህራንና ሠራተኞች ከስራቸዉ አፈናቅሏል። ጉዳዩን እንዲከታተሉ በህዝብ የተመረጡትን ሽማግሌዎች በደህንነት በማደን ከቤት ንብረታቸዉ አፈናቅሏል። የጉዳዪ ጠንሳሾች ናቸዉ ያላቸዉን አስሮ ከፍተኛ ቶርቸር በማድረግና በማሰቃየት በሽተኛ ሆነዉ እንዲሞቱ አድርጓል። የዞን ጥያቄ አቀራቢና የወላይታ ነጻነት ታጋይ አቶ ሰለሞን ሴታ ሲሆን በእስር ተሰቃይቶ ሞቷል። 12 ግለሰቦችም በአጋዚ ወታደሮች ጥይት ተገድለዋል። በርካታ ግለሰቦችም አካለ ስንኩል ሆነዋል። የዚህ ወንጀል ፈጻሚዎችና መመሪያ አስተላላፊዎች እስከ ዛሬ ድረስ በወላይታ ህዝብ ተወካይ ነን በማለት በወያኔ የስልጣን ኮርቻ ላይ ተቆናጠው ይገኛሉ።

3ኛ) በ 1997 ምርጫ ሰፊዉ የወላይታ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችን በከፍተኛ ድምጽ ከመረጠ በኋላ በሶዶ በቦዲቲ፤ በሁምቦ፤ በባዴሳ ፤ በጋሱባ ፤ በአረካ ፤ በባሌ ከተማና በአንዳንድ ቀበሌዎች የአሸናፊዎች ስምና የቆጠራ ዉጤት ከተለጠፈ በኋላ በወቅቱ የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከአቶ መለስና በረከት ስምኦን በተሰጣቸዉ ትዕዛዝ በሌሊት በመላዉ ወላይታ ካድሬዎችን ከፍተኛ አበል ከፍለዉ በመንግስት ተሽከርካሪ በማሰማራት የወላይታ ህዝብ ድምጽ እንዲሰረቅና ኮሮጆ ተገልብጦ ኢህአዴግ እንዳሸነፈ ተደርጎ በህዝቡ ያልተመረጡ ግለሰቦች ሥልጣን በሌብነት እንዲይዙ ተደርጓል።  እነዚህ የዉሸት ባለስልጣኖች የወላይታ ህዝብ በጥቂቱም ቢሆን ብሶቱን እንዳይተነፍስ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ቢሮዎች በማሸግ አመረሮችን በማሰር የኑሮ ዋስትናቸዉን በማሳጣት ንብረታቸዉን በመቀማት እየተከታተሉ በማሳደድ አጥፍተዉ ለብቻቸዉ የወላይታን ፖለቲካ ጠቀልለዉ ይዘዋል።

  • በአሁኑሰአትወላይታዉስጥየኢህአዴግአባልወይምጆሮጠቢያልሆነግለሰብተምሮሥራአያገኝም፤ነግዶወደፊትእንዳይወጣይደረጋል፤አርሶበነጻነትእንዳይኖርበካድሬዎችጫናይደርስበታል።
  • ወላይታከፍተኛየህዝብብዛትያለበትናየመሬትጥበትያለበትመሆኑእየታውቀየገበሬዉይዞታለከተማመስፋፋትእየተባለአለበቂካሳክፍያይወሰዳል።በገጠርደግሞታዳጊማዘጋጃቤትእየተባለየገበሬዉመሬትይነጠቃል።የመሬትነጠቃዉንየተቃወሙግለሰቦችይታሰራሉይደበደባሉይባረራሉ።
  • የአርሶአደሩንመሬትበGPS እየለኩከአቅምበላይየሆነግብርበመጫንመክፈልካልቻለመሬቱንይነጥቃሉ።
  • ለገበሬዉበኮታማዳበሪያበማደልበአንድኩንታልክ 1 ሺህእስክ 2 ሺህበመተመንመክፈልካልቻለከብቱንነጥቀዉወደገበያበመዉሰድሸጠዉገንዘቡንለማዳበርያክፍያያዉላሉ።
  • በከተማዉነጋዴላይከአቀምበላይየሆነግብርበመጫንነግዶእንዳይበላያፈናቅላሉ፤ግብሩምእጅግየተጋነነነዉብሎየተናገረነጋዴየንግድፈቃዱተቀምቶቤቱይታሸጋል።
  • የከተማመሬትበከፍተኛዋጋበሊዝዝስለሚሸጥየመንግስትሠራተኞችምሆንአነስተኛኑሮያለዉዜጋየቤትባለቤትመሆንአቅቶአቸዋል።
  • በሌላዉየኢትዮጵያእንደሚፈጸመዉሁሉየወላይታህዝብበኑሮዉድነት፤በመኖርያቤትችግር፤በዉሃናበመብራትእጦት፤በመሬትዘረፋናንጥቅያ፤በኢህአዴግ“ወህዴድ”የፖለቲካጫናበድሮጉልተኛሥርዓትከደረሰበትጭቆናበላይወያኔበመደባቸዉየራሱንቋንቋበሚናገሩሆዳሞችታፍኖይገኛል።በሌላበኩልየወያኔጆሮጠቢዋችመዋቅርዘርግተዉህዝብንናመንግስትንበመዝረፍሰባዊመብቱንረግጠውናአፍነውይገዛሉ።

፪ በመላዉ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለዉ የህዝብ ንቅናቄና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምንስቴር ምላሽ በተመለከተ

አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከወላይታ ህዝብ ከመልካም ቤተሰብ የተወለዱ፤ በጥሩ ሥነምግባር ያድጉ፡ ከፍተኛ የቀለም ትምህርት የቀሰሙና ወጣት ሲቪል ፖለቲከኛ በመሆናቸው ህወሃት በጠቀላይ ሚኒስትርነት ሲመድባቸዉ ኢትዮጵያዉያን ወደተሻለ ዴሞክራሲ፤ የጋራ መግባባት ያለዉ የሰከነ ፖለቲካ፤ የህግ የበላይነት ያሰፍናሉ፤ የሰዉን ሰብአዊ መብት ያስከብራሉ፤ የህዝብን እምባ የሚያብስ ፖለቲካ ሥርዓት ያመጣሉ የሚል ተስፋ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደጣለባቸዉ እኛም የወላይታ ተወላጆች አንዳዶቻችን በግል ጓደኝነት ሌሎቻችን በአካባቢ ልጅነትና በትምህርትና በስራ አጋጣሚ ስለምናዉቃቸዉ ተደስተን ነበር። ሆኖም ቤተ መንግስት እንደገቡ ሙሉ በሙሉ ለህወሃት እጃችዉን ሰጥተዉ ህሊናቸውን ሸጠዉ የሟቹን ጠ/ሚኒስትር ራዕይ አሳካለሁ ማለት ጀመሩ።

የመጀመሪያዉ 2 የስልጣን ዘመን የዉከልና ነዉና ይሻሻላል በሚል ሲጠበቁ የመለስ ራዕይ የሚሉትን እንደ እግዚአብሄር ቃል ሙጭጭ አድርገዉ በመያዝ የመለስን የምርጫ ማጭበርበር፤ የተቃዋሚ ፓርቲ አፈና እስርና ግድያ፤ የጋዜጠኞች እስርና ስደት ደረጃዉን ከፍ አደረጉት። ኮሮጆ እየሰረቁም ቢሆን በመለስ ዜናዊ 10% ከዚያም አንድ ለእናቱ በሚል የሚታወቀዉን የፓርላማ ወንበር ጨፍልቀዉ ፓርላማዉን 100% ተቆጣጠሩት። በአረካ ከእርሳቸዉ ጋር የተወዳደሩትን እዉቁን ነጋዴ በካድሬዎቻቸዉ አማካኝነት የተቃዋሚ ደጋፊዎች የምረጡኝ ዘመቻቸውን በነፃነት እንዳያካሂድ በማዋከብና በማስፈራራት አሰናክለው ምንም ህፍረት ሳይሰማቸዉ 100 ለ 0 አሸነፍኩ አሉ። የህወሃትን የከፋፍለህ ግዛ ተልኮ ለመፈጸም በደቡብ የወላይታን ብሄረሰብ ከሲዳማ ጋር ለማጋጨት ከብላቴ ወንዝ ማዶ የነበረዉን የሲዳማ መሬት ብላቴን አሻግረዉ የወላይታ መሬት ለሲዳማ እንዲሰጥ በማድረግ ሁከት እንዲፈጠር አመቻችተዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉት የኦሮሚያ ህዝቦች፤ የመብት ጥያቄ ባነሱ የዓማራ ህዝቦች እንዲሁም በኮንሶ፤ በቁጫ፤ በአርባ ምንጭ፤ በቤኒሻንጉል፤ በጋምቤላና በቴፒ ወዘተ የተነሱትን የተነሱትን ጥያቄዎች የጥይት ምላሽ እንዲሰጥ የዉጭ ወራሪ ሃይል ባልተነሳበት ሁኔታ የመከላከያ ሠራዊት እርምጃ እንዲውስድ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

የመሬት ባለቤትነት ቢረጋገጥ ገበሬዉ መሬቱን ሸጦ ወደ ከተማ ይፈልሳል የሚለዉን የህወሃት ፕሮፓጋንዳ ፍጽም መሠረት የሌለው መሆኑን እየጠቆምን ለመረጃም ያህል  በደርግ ዘመን መሰረታዊ የተማሪው ጥያቄ የነበረው የመሬት  ላራሹ ምላሽ በማግኘቱ ሠፊው ህዝብ ከመሬት ጭሰኝነት ተላቆ የመሬት በለቤትነት በሚገባ ተረጋግጦ ነበር ። ታድያ   ህወአት /ኢህአደግን የምናሳስበው የኢትዬጵያ አርሶ አደር መሬቱን ያለማል ለልጅ ልጅ ያወርሳል ፣ ህይወቱና የኑሮ ዋስትናው መሆኑን በማወቅ ይንከባከባል እንጁ በቀላሉ አይሸጥም ለምሳሌም ወላይታን ብንመለከት ሄምቤቾ ፤ የአድማንቾ ፤ የወይቦ ቀበሌ ገበሬዎች መሬታቸዉን ሸጠዉ አረካ ወርደዉ ነበር? የኦፋ ሴሬ፤ የዋጃ ቄሮ ፤የኮካቴና ሌሎችም አካባቢ  የሚኖረውረው  ገበሬ  መሬቱን ሸጦ ሶዶ ከተማ ወርዶ ነበር ? ገበሬዉ ቢቸገር እንኳን ዘመዱን ወይም ቅርብ ጓደኛዉን ፈልጎ ለአንድ ወይም ሁለት ዓመት ኮንትራት ይሰጣል ። የወላይታ ቀበሌዎችን እንደምሳሌ  አነሳን እንጂ የትም ቦታ ገበሬዉ የኑሮ ዋስትና የሆነዉን መሬት በቀላሉ አይሸጥም። ይህ እኛ እናዉቅልሃልን የሚሉ የህወሃት ፖለቲከኞች የኢትዮጵያን መሬት ተቀራምተዉ ለዘመድ አዝማድ በማከፋፈል በአቋራጭ ለመክበር ያወጡት ዘዴና አርሶ አደሩን አሳንሶ ማየት ነዉ። ከዛሬ 45 ዓመት በፊት  የወላይታ ተወላጅ የነበረዉ በወቅቱ ከቀዳማዊ ኃይለሥላስሴ ዩንበርስቲ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ የነበረው ጀግናዉ ሰለሞን ዋዳ ከዩንበርሲትው በሰርቢስ አገልግሎት ወይላታ ተመድቦ በዚሁ ህይወቱን የሰዋዉ መሬት ላራሹ የሚል መፈክር አንግቦ ነዉ። በታሪክ አጋጣሚ ከወላይታ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት በተቃራኑው የኢትዬጵያ ህዝብ እስትንፋሱና መሰረታዊ ጥያቄው የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ መሆኑን በመረዳት ከሰፊው ህዝብ ጎን መቆም ተስኗቸዋል ።

የኢትዮጵያ ህዝብ አንኳር ጥያቄ የአንድ ብሄር የበላይነት ይቁም ሲሆን እርስዎ ግን የብሄር የበላይነት የለም ይሞግታሉ ! በማሳያነትም በአጭሩ ቢገለጽ  የመከላከያ ኢንጂኔሪንግን የሰዉ ሀይል ብንወስድ ከዘበኛ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ባለስልጣን ቢመለከቱ  ከትግራይ አንድም ሰዉ የቀረ አይመስልም። የደህንነት መስርያ ቤትንና ማዕከላዊ ምርመራን ገራፊዉ፤ አሳሪዉ፤ አዛዡ ሲቪል ልብስ ለብሰዉ በየመንገዱ ዜጎችን አፍኖ ወዳልታወቀ ስፍራ ወሳጁ ከእርስዎ አጃቢዎች ጀምሮ እስኪ አስተውሉ! የኢትዬጵያ አየር መንገድ 80% ሠራተኞችስ? ቴሌኮም ፣ የኢትዬጵያ ቴለብዥንና ራድዬስ ?

በሌላ በኩል በየፕሮጀክቶች ተቋራጭ የሆኑት፤ ዕቃ አቅራቢዎችና የመጓጓዣ ከባድ መኪና በለ ንብረቶች በሙሉ የአንድ ብሄር ተወላጆች አይደለምን? ለምሳሌ የወይጦ ስኳር ፋብሪካን እናንሳ አንድ የትግራይ ተወላጅ ግለሰብ እስከ 100 ከባድ መኪና ወይም ሎው ቤድ አለዉ። ይህ ከየት እንደመጣ ያጣራ ከፍል አለን?  ከጀቡቲ ወደብ መሃል አገር የኮንስትራክሽን ዕቃ የሚያመላልሱ የማን ተሽከርካሪዎች የማናቸው? አዲስ አበባ ካሉት ከፍተኛ ፎቆች አብዛኛዎቹ የህውሃት በለሥልጣንና ዘመድ አዝማዶቻቸው እንዲሁም በጋብቻና በአምቻ የተገናኙ ግለሰቦች ሀብት መሆናችው አይታወቅምን? ይህ ነው ይህች ሃገር የማን ናት አስብሎ የዜጎች እኩልነት የለም የሚያሰኘን። ከዚህም በላይ ኢህአዴግ እራሱ በየጊዜዉ በሚያካሂደዉ የምክር ቤትም ሆነ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባዎች ስለመልካም አስተዳደር እጦት ስለ ኪራይ ሰብሳቢነት ያነሳል ብልሹ አሰራረም እንዳለ በየመግለጫዎ በተደጋጋሚ ያስቀምጣል።

ኪራይ ሰብሳቢነት ችግር እንደሆነና ለመታገል አቅጣጫ ተቀምጧል ሲባል ቆይቷል። ሆኖም እየተሻሻለ ሳይሆን እየባስ ሄዷል። ኢሃዴግ ቁልፍ ችግር እንጂ ቁልፍ መፍትሄ ለኢትዬጵያ ህዝብ አልፈጠረም። ለህዝባችን ጥያቄ  ቁልፉ መፍትሄ 1ኛ) የመሬት ባለቤትነትና ንብረት ማፍራት 2ኛ) ነጻ ፕሬስ፤ 3ኛ) ነጻ ምርጫ፤ 4ኛ) የህግ የበላይነት፤ 5ኛ) በሰላማዊ ሰልፍም ሆን በተለያዩ መድረኮች ያለመሸማቀቅ ሃሳብን በነፃ መግለጽ  6ኛ) ከተቃዋሚ ፓለቲካ ድርጅቶች በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መነጋገርና ፖለቲካ ምህዳሩንም ማስፋት፤ 7ኛ) የመንግስ ባለስልጣናትና የፖልቲካ ድርጅት አመራርና አሰራርን መለየት፤ 8ኛ) በአገሪቱ መተማመንን ለመፍጠር ሁሉንም የፓለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት ሌሎችን ማሸማቀቅና ማሰርን ማቆም።

፫) ዉድ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ በሆነ መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኗን በመገንዘብ ካላይ ያስቀመጥናቸዉን ሁኔታዎች በጥልቀት አይተን የሚከተለዉን የአቋም መግለጫ አዉጥተናል።

1ኛ) ከአንደኛ  ደረጃ ጀምሮ በታሪክና በጂኦግራፊ ስንማር ወልቃይት ጠገዴ የጎንደር እንጂ የትግራይ ሆኖ ስለማያዉቅ ለበርካታ ግዜያት ከትግራይ ተወልደዉ የትግራይ ክፍለ ግዛት ገዠና አስተዳዳሪ የነበሩት ራስ መንገሻ ሰዩም በመሰከሩት መሰረት የወያኔ እንካ ሰላንተያ ቆሞ የአማራ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ እንዲያገኝ እንጠይቃለን፤

2ኛ) የወያኔ ሰራዊትና የደህንነት ኀይል በሰላማዊ መንገድ እምነቱን ለመግለጽና የእሬቻ በአልን ለማክበር በወጣዉ  ህዝብ ላይ ያደረሰዉን ጭፍጨፋ የሰዉ ዘር ማጥፋት ድርጊት በመሆኑ በጣም አዝነን እያለቀስን ይህን አረመኔያዊና ሴይጣናዊ ተግባር አጥብቀን እናወግዛለን፤

3ኛ) የወያኔ ሰራዊት በአማራ፤ በኦሮምያ፤ በጋምቤላ፤ በኮንሶና፤ ወዘተ የሚያፈሰዉ የንጹሃን ኢትዮጵያዉያን ደም የወላይታ ህዝብ ደም ስለሆነ ደርጊቱን እናወግዛለን፤

4ኛ) ሰሞኑንም በዲላና አካባቢው ብዙ ብሔረሰቦች በሰላምና በፍቅር ይኖሩ የነበሩት ሃያ አምስት ዓመታት ህዋአት ኢህአዲግ አገዛዝ በረጨው የዘረኝነት መርዝ ሳቢያ እርስ በርስ መጠቃቃታቸውንና በዚህም የንጽሐን ወገኖቻችን ህይወት  ማለፉና የአካልና የንብረት ውድመት መድረሱ እጅግም ልባችንን ነክቶታል ። አገዛዙም  የተቃጣበትን አገራዊ እምቢተኝነት ትኩረት ለማዛባት ሲል ራሱም ጭምር የለኮሰው መሆኑን በአሜሪካ ድምጽና ሌሎች መገናኛዎች ከሥፍራው ከተጠቂዎች አንደበት ስንሰማ በእጅጉ እያዘንን ድርጊቱን በጽኑ እናወግዛለን።

5ኛ) በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትርና የኢሃዴግ ሊቀመንበር የሆኑት የወላይታን፤ የሲዳማን፡ የጋሞን፤ የቁጫን፤ የኮንሶን ደም ያፈፈሱትን የመካላከያ ሠራዊት ሲያዙ ቆይተዉ ይህ ሳያንስ አሁን በመላ ኢትዮጵያ የተነሳውን የመብት ፣ የነጻነትና የህዝባዊ እምቢተኝነት ጥያቄ ለማዳፈን ጦር አዘዋል ፣ ይህንን ለማርገብ ያገባናል ከሚሉ ኃይሎች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ  ውይይት አገሪቱን ከእልቂት ማዳን ሲቻል ይባሱኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት በህወአት ወታደራዊ መዳፍና የደህንነት ኮማንድ ፓስቴ አፈናውን ለማስፋት መወሰኑ ስላሳሰበንና ስላሳዘነን በእጅግ እርምጃውን  በጽኑ እናወግዛለን፤ኣ።

6ኛ) ከወላይታ ህዝብ አብራክ ወጥተው ለህዝባቸዉ ጥቅም ሳይሆን ለሆዳቸዉና ለስልጣናቸው አድረው ሰፊዉን ሕዝየሚያተራምሱ ካድሬዎች ነገ በታሪክና በህዝብ ፊት ተጥያቂ ከመሆናችሁ በፊት እጃችሁን ከጥፋት መንገድ በአስቸኳይ እንድታነሱ እንጠይቃለን፤

7ኛ) ሰፊዉ የወላይታ ሕዝብ ትናንትናም ዛሬም ነገም ጅግና ነህ፤ ሃጤሮ አንቼ  የተባሉ የወላይታ ጀግ የመልከኛው ሥርዓት  አንገሽግሾት ህዝብን አንቼ ድርባ በምባለው ተቃውሞ  ዘመቻ ለወላይታ ሕዝብ መብትና ክብር ታግሎ እንድተሰዋ ሁሉ ንብረታችሁንና መሬታችሁን ለመቀማት ለሚመጣውና ለሚያፍናችሁ የወያኔ ካድሬ ጸጥ ብላችሁ እንዳትገዙና ለኦሮሞ፤ ለአማራና፤ ለኮንሶ ሕዝቦች የአጋርነት ድምጻችሁን እንድታሰሙ እንጠይቃለን። በህዝብ እገዛና ድጋፍ ተምራችሁ በተለያዩ የመንግስት ሥራ የተሰማራችሁ ወገኖች በኑሮ ዉድነት መከራችሁን እንድታዩና ልጆቻችሁን የማብላትና የማልበስ አቅም ያሳጣው በፕሮፓጋንዳ ሆዳችሁን እየሞላ ያለዉን የወያኔ ኢሃዴግ አገዛዝ ሕዝቡ እምቢ እንዲል የራሳችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ እንጠይቃለን፤

8ኛ) ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለዉን ጭፍጨፋ መልኩን ለማስቀየርና ሕዝባዊ ድጋፍ ያለው ለማስመሰል በየቦታው የሚጠራውን የድጋፍ ሰልፍ እንኳን ገደላችሁ ብሎ የሚወጣ የወላይታ ሰው አለመኖሩን በተግባር እንድታሳዩ እንጠይቃለን፤

9ኛ) አምባገነኑ ህወአት ኢህአደግ ሥርዓት በወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን መጠነ ሰፊ ሰቆቃ አስመልክቶ በአሁኑ ወቅት መላው ዓለም አገዛዙን በማውገዝ ላይ ይገኛል በዚህም ዓለም አቀፉ የሰባዊ መብት ድርጅቶች ፣ የተባበሩት መንግሥታት የአውሮጳ ህብረት ኃያላን መንግስታትን ጨምሮ አሜሪካና በሰሞኑ ኢትዬጵያን እግረመንገዳቸው የነበሩት የጀርመኗ ቻንስለር አንግላ ማርኬም አገዛዙን በመንቀፍ ለፓርላማው እንዲናገሩ የተጋበዙትን በአንድ ድርጅት ለተቀፈደደውየኢትዬጵያ ፓርላማ ንግግር አላደርግም በማለት ቅሬታቸውን ለማሳየት ውድቅ ማድረጋቸውን በጽኑ እንደግፋለን።

10ኛ) እኛም በአሜሪካና ካናዳ የምንኖር ( 69 ) ሰላሳ ዘጠኝ የምንሆን ኢትዮጵያዉያን የወላይታ ተወላጆች አገራችንችንን ከልባችን የምንወድ ከማንኛውም አፍራሽ ሃይል ጋር ግንኙነት ኖሮን ሳይሆን በአገር ቤት የሚገኘው ኢትዬጵያዊ ወገናችን ዛሬም በድጋሚ በአምባነኖችና ጨቋኞች መዳፍ ሥር በመውደቁና አፈናው ፣ ሰቆቃውና ግዲያው ህዝባችን ሊሸከመው ከሚችለው በላይ በመሆኑና ትዕግስታችንም በመሟጠጡ የወገናችን ሰቆቃ ሰቆቃችን መሆኑን በመገንዘብ የእዚአብሄር ቃል በመጽሃፍ ቅዱስ በተለያዩ ቦታዎች ለተጎዱ ጩሁ በየቦታዉ ድምጻችሁን አሰሙ ባለዉ መሰረት ድምጽን ለለታፈነው የኢትዬጵያ ሕዝብ አንደበት በመሆን ይህንን መግለጫ በጋራ አውጥተናል።

ኢትዬጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

በአሜሪካና በካናዳ የምንኖር የወላይታ ተወላጅ ኢትዬጵያዊያን!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.