አባይን ያላየ የምንጭ ውሃ ብርቁ ነው።(መስቀሉ አየለ)

dedebit-satenaw-news

ደደቢት ከሚባል ተፈጥሮ ከረገመው በረሃ ውስጥ ፈልተው እና የሰው ስጋ ለብሰው የመጡ እፉኝቶች ከሁለት አስርተ አመታት በላይ ዘርፈው አልጠግብ ያሉት የመሬት ወረራ ያስመረረው ህዝብ ከአሰር ወራት በፊት እንደ ቀላል በምስራቁና በምዕራቡ የሃገሪቱ ክፍል አካባቢ እንደቀላል መገዳደር ሲጀምር ማንም ነገሩ በዚህ ደረጃ ጠንክሮ ይዘልቃል የሚል ከየትኛውም ወገን በኩል ግምቱ አልነበረውም። ሁልጊዜም ህዝብ ግፍን የሚሸከመውን ያህል ቀን ቆጥሮ ለመነሳት ደግሞ ማን በምን ለምን በምንና እንዴት እንደሚጀምረው ባይታወቅም ድንገት እንደቀልድ የምትጫረው ክብሪት የአብዮቱ የመጀመሪያ ደዎል ልትሆን ትችላለች። በኛም አገር የሆነው ይኸው ነው። ነገሩ ከቀን ወደ ቀን እየገፋ ሳምንታትን አንድ ሁለት እያለ ማስቆጠር የጀመረው አስካሪሶቹ በመቶ ፐርሰንት ማሸነፋቸውን ባለገድል መሆናቸውን ካወጁና ይህንንም ባራክ አባማ እና አንዲት የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንቴር ነኝ የምትል ሳይኮፓት ሞሮን አዲስ አበባ ድረስ መጥተው ከመሰከሩላቸው ከጥቂት ወራት ቦሃላ መሆኑ ነው። ሆኖም ግን ሳምንትን ሳምንት እየወለደው ሁለት ወራት ሲሞላው ሳሞራ የኑስ የተባለ የአይምሮ ዘገምተኛ አንድ ደብዳቤ አስጽፎ ለሃይለማርያም ደሳለኝ ልኮለት ነበር።ይኸውም በአንድ ሳምንት ውስጥ የዚህን አመጽ ማስቆሚያ ፕላትፎርም ካላቀረብክ ሚሊተሪው መፈንቅለ መንግስት ለማድረግና ስርዓቱን እራሱ ለማስከበር ይገደዳል የሚል አይነት ይዘት ያለው ነበር። አመጹም ሳይቆም ጭራሽ በቅርጽ እና በይዘት እየሰፋና ህልቁ መሳፍርት ህይወት እያስከፈለ ጭምር እለት እለት ማደግ ጀመረ።

ቆይቶም አበበ ተክለሃይማኖት የተባለ የቀድሞ የወያኔ ሚኒሻ ወታደሩ እየመጣ ነዉ የሚል ማስፈራሪያ በሉት ማስጠንቀቂያ ጻፈ። ሆኖም ወያኔ ቱባ ቱባ የኦሮሞያ ባለስልጣናትን በሙሉ አባሮ ክልሉን በስምንት ቀጠኛ ከፍሎ ለስምንት ጀነራሎች ሰጠ። ይህ ክልል በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስር ሲዎድቅ ከሱማሌና ከቤንሻጉል ቀጥሎ ሶስተኛው ክልል መሆኑ ነው። ሆኖም ግን አሁንም ጠብ የሚል መፍትሔ ሊያመጣ አልቻለም። በዚህ መሃል በሰላማዊ ትግል ሲያልበው የከረመው ዘረኛ ቡድን ጭራሽ በነፍጥ ጭምር የታገዘው ህዝባዊ ተጋድሎ ከአማራ አገር ፈንድቶበት አረፈው። ይ ኽን ትግል ለየት የሚያደርገው ሊሞት ብቻ ሳይሆን ሊገድልም ጭምር የመጣ መሆኑ፣ እሳት የሚተፋ፣ ሞትን የናቀ፣ በአባቶቹ ቅኝት የሚናገርና በብሔራዊ ቁጭት የተቃጠለ አርበኛ ሆኖ መገለጡ ነው። ። አዎ፣ ከሁለት አስርተ አመታት በላይ ከኛ በላይ ባሩድ አሽታች ማነው በሚሉት ድውያን ላይ ቀሚስ ጭምር እያለበሰ እና የሴት ኮንጎ እያስጫማ አንበርክኮ ጭንቅላት ላይ ጥይት የሚቆጥር የሃይላንደር መረሬ ፋኖ ተሰማራ ብሎ፤በደርባርቅ ራስ ዳሸንና ሰሮቃ አካባቢ ፈነዳ። በቀናትም ውስጥ የአርባ ዓመቱን የወልቃይት ሰቆቃ በእሳተ ጋሞራ መንዝሮ መሃል ጎንደር ከተማ አምጥቶ ብሐራዊ አጀንዳ አደረገው። ይኽ ዛሬ አዲስ አበባን በቅርብ እርቀት ማፈንፈን የጀመረው ህዝባዊ ተጋድሎ ደም እያስከፈለና ሃሞትንም እያመረረ እለት እለት ማደጉ ለወንበሩ ጤና አልሰጥ በማለቱ በስቴት ኦፍ ኢመርጀንሲ ሽፋን ወታደሩ መንፈንቅለ መንግስቱን አካሂዶ የአገሪቱን ስልጣን ተረከበ። ዛሬ ሁላችንም ማወቅ ያለብን አንድ እውነት አገሪቱ ውስጥ ለይስሙላም ቢሆን የነበረው የሲቪል አስተዳደር ጨርሶ መፍረሱን ነው።

ይኽ መፈንቅለ መንግስት በተለምዶ ከሚታወቀው በተለየ ተኩስ አልባ በመሆኑ ማለትም የአገሪቱ መሪ ነው የሚባለው ጠቅላይ ሚንስትር በሉት ፕሬዝዳንት ሲገደሉም ሆነ ሲታሰሩ ወይንም አገር ለቀው ሲጠፉ አለማየታችን ግልበጣው ያልተፈጸመ ይመስለን ይሆንናል። እዚህ ላይ መሳሳት የሌለብን አንድ መፈንቅለ መንግስቱ ደም አፋሳሽ የሚሆነው የአገሪቱ የፖለቲካ ሃይል ይህ ነዉ የሚባል የራሱ የሆነ የሚያዘው ወታደራዊ ክንፍ ሲኖረው ነው። ለምሳሌ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ልክ በመለስ ግዜ እንደነበረው እና በህገመንግስቱ እንደተጻፈው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስቴር ብቻ ሳይሆን የጦር ሃልሎች ጠቅላይ አዛዥነቱንም ስልጣን ደርቦ ያዝ የነበረ ቢሆን ነው። ሃይለማሪያም ግን በዚህ አይታማም። ስለዚህ ለሳሞራ ወይንም ለጌታቸው መፈንቅለ መንግስቱን ለማከናወን የአንድ ወታደር ደም ማፈስ ሳያስፈልጋቸው በሁለት መስመር ደብዳቤ ማሳወቅ በቂያቸው ነበር ማለት ነው። የሆነውም ይኸው ነው። ሌላው አደገኛው ጭብጥ የሲቪክ አስተዳደሩን መፍረስ ተከትሎ የወጣው ባለ ሰላሳ አንድ አንቀጽ አዋጅ እና ለነፍሰ በላው አጋዚ የተሰጠው አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ መብት እንደ ቀይ ሽብር አይዲዮሎጅን ሳይሆን ይልቁንም ዘርን መሰረት ያደረገ የጀኖሳይድ አዋጅ መሆኑን ህዝባችን ልብ እንዲለው እና እራሱን ከመቸውም በላይ ለተጋድሎ እንዲያዘጋጅ ግድ ይለዋል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.