ጥብቅ ማሳሰቢያ . .  ህወሃት የሚመራዉ ወታደራዊ ጽንፍ ቡድን የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተንተርሶ በዉጭ ሐገራት በስደት የሚኖሩ ስደተኞች ላይ የሚመክር የመጀመሪያ ስብሰባዉን በደቡብ አፍሪካ ጠራ

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሚገኘዉ የህወሃታዊያን ኢንባሲ በፍሪ ስቴት እና አካባቢዉ የሚኖሩ ደጋፊዎቹን በ 22/10/2016 ቅዳሜ እለት ስብሰባ ጠርቷል። የዚህ ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር እንቅፋት የሆኑ ከአርበኞች ግንቦት 7 እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር ትስስር ያላቸዉ ግለሰቦችን በተመለከተ ለመምከር መሆኑን ከዉስጥ ያገኘነዉ መረጃ ያመላከተ ሲሆን ስብሰባዉን በማቀናጀትና ድጋፍ በመስጠት የህወሃት ተወካዮች እና አቶ ታመነ ወንዳሮ የተባሉ ( 0027743822700 ) የፍሪ ስቴት አካባቢ የህወሃት አባልና ተጠሪ በግንባር ቀደምትነት ይገኙበታል።

የስብሰባዉ ዋነኛ አላማ የሀወሃት ወታደራዊ ስርአት ያወጣዉን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በመደገፍ በደቡብ አፍሪካ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግና ሐገር በማበጣበት ከነጻነት ሐይሎች ጋር የሚያብሩ ግለሰቦችን የደቡብ አፍሪካ መንግስት አሳልፎ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ሲሆን መረጃዉ የደረሳቸው የነጻነት ታጋዮች  ይህንን እኩይ የወያኔ ተግባር በማኮላሸት በኩል የአስቸኳይ ግዜ እርምጃ እንዲወስዱ መልእክት አስተላልፈዋል ”

በተጨማሪ መረጃ ወያኔ ህወሃት በኡጋንዳ በኬንያ በታንዛኒያ በማፑቶና እንዲሁም በአዉሮፓና በአሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ተመሳሳይ ስብሰባዎችን ለማድረግ እንቅስቃሴ የጀመረ በመሆኑ በመላዉ አለም የምትኖሩ ወገኖች ይህንን ወንጀለኛና ገዳይ የኢትጵያና የኢትጵያዊያን ነቀርሳ ከስር መንግላችሁ እንድትጥሉ ጥሪያችን እናስተላልፋለን !

አንድነት ሐይል ነዉ !

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

ሊኡል ኣለመ

wp5070760f_06