ወገን እየሞተም ፥ወገን ደማችንን ይመልሳል !! [ህሊና ዘቀበሮ ፀረህወአታዊያን]

Amharaጎጃም ጃዊ ወረዳ የሚገደሉት ንፁሃን ዜጎች ቁጥር ጨምሯል ። በወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢ/ር አስራት መሪነት በከተማው የሠፈረው 120 የወያኔ ለቀን ሥራ ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢወች የመጡት ወገኖች በጃዊ ልዩ ስሙ አይማ እና ባንቡሉክ ከሚባሉ አካባቢወች ያልታወቀው የነፃነት ሃይል ወታደር ሰፍሮ ይገኝበታል በሚል ከዚህ ሃይል ጋር ትቀላቀላላችሁ በሚል ላለፉት 3 ቀናት ያገኙትን ሲደበድቡና ሲገሉ መቆየታቸውን የአይን እማኞች ይናገራሉ እስካሁን ከ20 በላይ የተገደሉ እንዳሉ ይነገራል ብዙወችምክፉኛ ቆሥለዋል ።

ለቀን ሥራ ከመጡት 5 የሠከላ ግሽ አባይ ጓደኛማቾች ውስጥተጎድቻለሁ አንዱን ተጎጂ አግኝቸ በስልክ አነጋግሬዋለሁ፦ ‘በጠዋት ወደ ሥራ እየተጓዝን ነበር ፤ትንሽ እንደተጓዝን ወታደሮች አስቆሙን አምስታችንም ቆምነ ከዳር ያለውን ጓዳችንን በጥይት ከፊታችን ደፉት እኛንም በሰደፍና በጫማ ደበደቡን ።እኔን ከሌሎች በበለጠ …የተወሰኑ ሰወች እረድተውን ወደ ጤና ጣቢያ አደረሱን ፤ከእኛም የከፋ በጥይትም የተደበደበ የቆሠለ ይሰቃያል ።ሽንቴን መሽናት ሥላልቻልኩ በላሥቲክ (ካታተር )ተደርጎልኝ መሽናት ቻልኩ።ከዛም በአፍና በአፍንጫየ ደም ይፈሥ ነበር እራሴን ሣትኩ ።

ማታ ስነቃ እራሴን ጃዊቻግኒ ሆስፒታል አገኘዋጋውን በጨለማ አምጠው እንደጣሉኝ አወቅኩ ፤ምንም የረዱኝ ነገር ስለሌለ በጠዋት ወጣሁ ግን ምንም ገንዘብ የለኝም ፤መታወቂያየንና ስልኬን ወስደውታል ።ቻግኒ መንገድ ላይ እራሴን ስቸ ደም በአፍፌ እየፈሰሰ ወያላወቹ ገንዘብ ወደ ሃያት ክሊኒክ ወሰዱኝ ። ዶ/ሩ ሳላመሰግነው አላልፍም እግዚአብሔር ዋጋውን ይክፈለው !በነፃ አክሞኝ ይሄው ለሀገሬ በቃሁ ÷ግን ብቻየን ጓደኞቸ ያሉበትን አላውቅም ‘ በጥልቅ የሀዘን ስሜን አሰባስበውበወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን እጂግ አሰቃቂ የወያኔ የዘር ማፅዳት ወንጀል ይዘረዝራል ።

ጃዊ ከተማ ፀጥ እረጭ ብላለች ለስራ ከተለዩ ስፍራወች የመጡ ወገኖች የሚያሞቋት ዛሬ ሁሉም የሉም። በአብዛኛው በትግሬው ነፃ አውጭ ዘራፊና ገዳይ ቡድን በሚደርሥበት ግፍና እንግልት የነፃነት ሃይሎችን ና ጫካ የገባውን የአማራ ገበሬ ተቀላቅሎ ታጥቋል።ከፊሉም ወደ መጣበት ተመልሷል ።የሚገኘው ወገኖቻችን በወያኔ አፉኝ ቡድን ለወታደሮች ቢገደሉም በአካባቢው ለሰሚ ግራ የሆነ ሃይል የት መጣ ሣይባል የወያኔን ወታደር መግቢያ መውጫ አሳጥቶ ጥቃት ፈፅሞ ይሰወራል ።

ወገኖቻችም እየተገደሉም የወገኖቻችንን ደም የሚመልስ ወገን አለ ።በወረዳው ሰፍሮ የወያኔ ወታደር ብዙው በመገደሉና ከፊሉም በመሰወር ከነፃነት ሃይሉ ጋር በመቀላቀሉ በቁጥር ተመናምኖ የድረሱልኝ ጩኸቱን ተጨማሪ ሃይል እንዲደርስለት የበላይ ሹሞቹን ይማፀናል ።
ድል ለጀግኖች የአማራ የነፃነት ፋኖወች !!

ህሊና ዘቀበሮ ፀረህወአታዊያን

# AmharaResistance #