ብዙ የሕወሃት ታጣቂዎች እየሞቱ ነው – #ግርማ_ካሳ

EPRDFብዙዎቻችን ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የተከሰቱ ቀዉሶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታና የሕዝብን ጥያቄእንዲያከብርም ለብሄራዊ እርቅና መግባባት ራሱን እንዲያዘጋጅ በተደጋጋሚ፣ ስንማጸን መቆየታችን ይታወሳል። ሆኖም ግን ሕግ መንግስቱን በመሻር፣ ፓርላማው መፍቀዱ በትክክል ሳይታወቅ፣ ሰላም በማስጠበቅ ስም በሕዝቡ ላይ የጅምላ እሥርና ግፍ ለመፈጸም አዋጅ አውጥቶ፣ ኮማንድ ፖስት የሚባል የሕወሃት ወታደራዊ አገዛዝ ተቋቁሟል።

ይህ ኮማንድ ፖስት ራካ ፣ ሲሪያ ካለው የአይሰስ ኮማንድ ፖስት በምንም አይለይም። አላማው ህዝብን ማሸበር ነውና። በአንዲት ትንሽ ከተማ ብቻ፣ በሰበታ በአንድ ቀን ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ ዜጎችን ነው ሕወሃቶች ያሰሩት። በየቦታው በጭካኔ ሕዝቡን እያሰቃዩት ሲሆን ፣ አገሪቷን ወደ ከፋ ደረጃ እየወሰዷት ነው።

ይህ ኮምናድ ፖስት የሚባለው የሕወሃት ወታደራዊ አገዛዝ፣ ህዝቡ በሰላም በሚኖርበት ቦታ ታጣቂዎቹን እያሰማራ ግፍ ሲፈርጽም ዝም መባል የለብትም። ለዚህ ነው በተለይም በአማራው ክልል የሚኖሩ እጅግ በጣም ብዙዎች ፣ “ቤታችን ቁጭ ብለን አንገደልም፣ እኛ እንደርሱ ሱሪ ታጥቀናል” ብለው የሸፈቱት። ይህ ሰላማዊ ህዝብን አማራው ወደ ማይፈለገው መስመር ገፋፉት።

በአሁኑ ጊዜ በተለይም በአማራው ክልል ጦርነት ነው ያለው። በርካታ የሕወሃት ታጣቂዎች እየሞቱ ሲሆን፣ ብዙዎች በተለይም የጎንደር ጎጃም ወሎና ሸዋ ተወላጆች የሆኑ መሳሪያዎቻቸው ይዘው ህዝቡን እየተቀላቀሉ ናቸው።

ለምሳሌ ጥቅምት 10 ቀን 2009 ዓ.ም በምዕራብ አርማጭሆ አቡጢር የገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታትና ለመግደል የሔደው የሕወሃት ጦር መደምሰሱን መረጃዎች ያሳያሉ። ሁለት ኦራል፣ አንድ ፒክ አፕ እንዲሁም አንድ ታንክ በመያዝ ነበር የሕወሃት ጦር የተንቀሳቀሰው።

ትላንት ጥቅምት 13 ቀን ደግሞ የ13 የአጋዚ ወታደሮች አስከሬን ወደ አዲስ ዘመን ተወስዷል። በዚህ ጉዳይ ላይ ጋዜጠኛ ሙሉቀን የሚከተለውን ዘግቧል፡

“በሊቦ ከምከም፣ በእብናትና በምስራቅ በለሳ ወረዳዎች የዐማራ ገበሬን ትጥቅ ለማስፈታት የተንቀሳቀሰው የአጋዚ ጦር በለስ አልቀናውም፤ ይልቁንም ብዙ አባላቶቹን ሕይወት አስገብሯል” ሲል የዘገበው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ” ሰሞኑን በርካታ የአጋዚ ጦር አባላት መገደላቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲዘግቡ የሰነበቱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ ሌሊቱን (ጥቅምት 13 ለ14 ሌሊት) በዐማራ ገበሬዎች የተገደሉ የተጨማሪ 13 የሠራዊቱ አባላት አስከሬን ሲጓጓዝ አድሯል፡፡ ከወያኔ ሠራዊት ጋር የነበረውን ተጋድሎ የተሳተፉ የጎበዝ አለቆች እንደሚሉት 13ቱ ተጨማሪ የወያኔ ጦር አባላት የተገደሉት በሊቦ ከምከም ወረዳ ሊቦና ማርታዲዮስ በሚባሉ ገደላማ ቀበሌዎች ነው፡፡ እንደ ጎበዝ አለቃዎቹ ከሆነ የመቶ አለቃ ማዕረግ የነበረው የኦፕሬሽኑ መሪ በከባድ ቆስሎ በአዲስ ዘመን ሆስፒታል እርዳታ ቢደረግለትም በሕይወት መቆየት አለመቻሉን ገልጸውልናል፡” ሲል ዘገባውን አጠቃሏል።

እነዚህ ሁለቱ እንደ ምሳሌ ተጠቀሱ እንጂ በተለያዩ ቦታዎች ብዙ የአገዛዙ ታጣቂዎች እንደ ቅጠል እየረገፉ ነው። አገሪቷ አዲስ አበባ ብቻ የሆነች ይመስል ምን እንደሌለ ሊታሰብ ይቻላል እንጂ የርስ በርስ ጦርነት ላይ ነው ያለነው። ለዚህም ተጠያቂው አንድ ሺህ በመቶ ሕወሃት ነው።

(በነገራችን ላይ በአማራው ክልል እየተደረገ ያለው ትንቅንቅ ከሕዝቡ በተወጣቱ የጎበዝ አለቆች የሚመራ እንጅ የሻእቢያ እጅ ያለበት ወይም ኤርትራ ያሉ ደርጅቶች ያሉበት እንዳልሆነ ህዝብ በግልጽ ሊያውቀው ይገባል። የአማራው ክልል ህዝብ እንኳን ይሄን ያወቃል፤ ግን ሌላው ማህበረሰብ ብዙ መወናበድ የለበትም)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.