የገርጂ ኤሌክትሪክ ማሰራጫ ጣቢያ ቃጠሎ ደረሰበት

በታምራት ጌታቸው

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የገርጂ ማሰራጫ ጣቢያ ትናንትና ከሰዓት በኋላ 10፡30 ላይ የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ የተቃጠለው የገርጂ ማሰራጫ ጣቢያ፣ ከመገናኛ በኡራኤል እስከ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ ያለውን አካባቢ የሚሸፍን መሆኑም ታወቋል፡፡

ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባለመታወቁ፣ የዕለቱ ተረኛ ሠራተኞችን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ በምርመራ ላይ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በተለይ በጥቅምት ወር መጨረሻ አካባቢ በተደጋጋሚ የኃይል ማቋረጥ ማጋጠሙም ይታወቃል፡፡ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና አገልግሎት ኃላፊዎች ጊዜያዊ ችግር ተፈጥሮበታል ወደተባለው የጣና በለስ የኃይል ማመንጫ መጓዛቸው ተነግሯል፡፡ የጣና ብልሽትም ሆነ በገርጂ ማሰራጫ ጣቢያ የደረሰውን አደጋ እንዲያብራሩ የመሥሪያ ቤቱን ኃላፊዎች ለማግኘት ቢሞከርም፣ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

 

20814a67b0d36ff959b0e51679ff2026_L
የገርጂ ኤሌክትሪክ ማሰራጫ ጣቢያ ቃጠሎ