ኢትዮጵያ አይናችን እያየ አትፈርስም! [አቤ ቶክቻው]

abe-tokochawይቺ ሚጢጢ የአቋም መግለጫ ናት ብላችሁ አስቡ… አንዳንድ እድሜ የተጫጫናቸው ስደት እና አሰልቺ ትግል የሃገራቸውን እና የህዝባቸውን ተጨባጭ ሁኔታ ያሰረሳቸው… ግለሰቦች እና ድርጅቶች ኢትዮጵያን አፍርሰን እኛ እንቆማለን ሲሉ እየሰማን ነው… (እስቲ ማሉልን… በሳቅ ነው የምታፈርሷት ወይስ በመረጃ ልትቆፍሯት ነው…!?)

እኛ የት ሄደን ነው ለመሆኑ ኢትዮጵያ የምትፈርሰው… ለዛች ሃገር አያቴ ኦቦ ፈይሳ ደሞ በዳኔ የተቋሰለላትን ያክል…. አባቴ ቶላ ፈይሳ ደሞ የደከመላትን ያክል… እኔ እና ሌሎች በርካታ ሚሊዮኖች ልንሰዋላት ዝግጁ መሆናችንን የማያውቅ ኦሮሞ ካለ እርሱ ኦሮሞ ሳይሆን ኦሮምኛ የሚችል ጥቁር ጣሊያን ነው።
ሃገራችንን እንወዳለን ስንል ህዝቦች በእኩልነት የሚኖሩበት አንዱ በአንዱ ላይ ያለ እውቀቱ የበላይ የማይሆንበትን ማነኛውም ዜጋ በእኩል አይን የሚታይበት ሃገር እንድትኖረን እንመኛለን ማለት ነው እንጂ ትልቋን ሃገር እያፈረስን ትንንሽ ጎጆዎችን እንቀልሳለን ማለት አይደለም!
እናም እላለሁ…. እኛ በቁም እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም!!!

© Abe Tokichaw
+++++++++++

Habtamu MAbdi
ኢትዮጵያ አትፈርስም !
የአያቴ የሳጅን አብዲ ቦሩ አፅም የለንደኑን ኮንፍረንስ ቢሰማ ከመካነ መቃብሩ ሆኖ እንደሚሸበር አልጠራጠርም ።

በኬንያ ጠረፍ አከባቢ የፋሺስት ጣልያን ጦር መፈናፈኛ አሳጥተውት ፤ ድንጋይ ተንተርሰው፤ ዱር ቤቴ ብለው የኖሩት ኢትዩጵያን ብለው ነበር።

በስተመጨረሻም ከእንግሊዝ ጦር ጋር በማበር በተደረገው ፍልምያ እንደልማዱ ወራሪውን የፋሺስት ጦር ሲፋለም በክብር ተሰውተዋል። ይህ ሁሉ የሆነው ኢትዮጵያን ብለው ነው።

እናም ዛሬ ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት ብለው ግለሰቦች ሲፎክሩ የዛ የጀግናው የኦሮሞ አያቴን መስዋዕት ከየት አድርስውት ነው ? በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ አባት አርብኞችና እናት አርበኞች የከፈሉት ዋጋ በዜሮ ተባዛ ማለት ነው ?

ሰከን ቢባል ይበጃል ። ካልሆነ ያው እኛም የልጅ ልጆቻቸው ለዚህች ሀገር ሲባል የመጨረሻዋን ፅዋ ለመቅመስ ዝግጁ ነን።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር !
++++++++++++++

Elias GebruGodana
በኢትዮጵያዊነት ላይ ድርድር የለም! ኢትዮጵያዊነት ሲነካ ..ያኔ ቀልድ የለም … ታጥቀን እንታገላለን! ይኸው ነው።
በዓለት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያ ነገ ትኖረናለች! በዘር-ፖለቲካ አሸዋ ላይ የተመሰረተችውን ኢትዮጵያማ፣ ላለፉት 25+ ዓመታት አይተናታል፤ እያየናትም እንገኛለን! ይህም በቅቶናል!
++++++++++++
Derese GKassa (Dr.)
So you think the art of valor and warfare is your monopoly??! Seriously? You gotta be kidding me!
Habtegiorgis DeeNagde, Abbiche Garba, Geresu Duki, Abebe Aregawi, Balcha Aba Nafso, Abdiisaa Agaa, Jaggama Kello, Tadesse Birru, Hailemariam Gemeda, and Demissie Bulto, Kassahun Chemeda.
These guys ARE valor! They are patriots!
Their love letters will arrive on your zip code pretty soon.
++++++++++++
እኔ ሙሉነህ ዮሃንስ ደግሞ ይህን ማሳረጊያ ጋበዝኳችሁ….
አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ
ላገር ፍቅር ናፍቆት ጥላሁን ገሰሰ!

https://youtu.be/6UwpkL37QIo

Comments are closed.