ሰበር ዜና …በአላፋና ጣቁሳ ደልጊ ከተማ 42 ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን ዛሬ አሳወቁ

October 26 , 2016

Bahir dar Policeበአላፋና ጣቁሳ ደልጊ ከተማ 42 ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን ዛሬ አሳወቁ። በማህበረሰቡ ዘንድ የተከበሩና ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች እንደሚገኙበት ጨምረው አስታውቀዋል። ከነዚህም መካከል አቶ ደመላሽ ብርሃኑ፣
አቶ ሙሉው አደም እና አቶ አበራ ሻረው እነደሚገኙበት ከስፍራው የደረሰን መረጃ ጠቁሟል።

በሌላ በኩል በአሁኑ ሰዓት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ፤አልደገፋችሁኝም ፤አውግዛችሁኛል ፤የጥላቻ ዘመቻ አድርጋችኋል፤ህብረተሰቡ እንዳይቀበለኝ አድርጋችኋል፤የሥራ ማቆም አድማ አካሄዳችኋል ወዘተ በማለት በበርካታ የአማራ ክልል ነዋሪዎች ላይ የጀምላ እስር፣ግድያና ዘረፋ እየተደረገ መሆኑን ከተለያዩ አካባቢዎች በየጊዜው መረጃዎች እየደረሱን ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.