ቪዲዮ …. መቼም ሰው እንደ ተማረው ትምህርትና እንደ አስተዳደጉ ነው የሚወጣው [ደረጀ ሓብተዎልድ]

በዚህ ቪዲዮ ላይ በተደጋጋሚ አወዛጋቢና የፈጠራ ታሪክ ሲናገሩ የሚደመጡት ዶክተር ገመቹ መገርሳ በደርግ ጊዜ በቀይ ሽብርና በነጭ ሽብር ከተገደሉት መካከል ሰማንያ በመቶው ኦሮሞዎች ናቸው በማለት ለ እነ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጋቢሳና ለነ ጃዋር መሀመድ ማብራሪያ ሢሰጡ ይታያሉ፦ ዶክተር ገመቹ መገርሳ የዛሬ አስራ አራትና አስራ አምስት ዓመት አካባቢ አቶ መለስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ተገኝቶ ለነበረው የዘፕሬስ ጋዜጣ ሪፖርተር በሰጡት ቃለ ምልልስ “ እዚህ ውስጥ ከተሰበሰበው መቶ ፕሮፌሰር ይልቅ የአንድ የመለስ ጭንቅላት ይበልጣል” ብለው በመናገራቸው ወይም መወድስ በማቅረባቸው የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት የተደረጉ ቢኾንም ፤ሥራቸውን በአግባቡ መሥራት ባለመቻላቸው ብዙም ሳይቆዩ እንዲወርዱ የተደረጉ ናቸው) እንዲሁም ምርጫ 97ትን ተከትሎ በተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን አባላት አባል የነበሩ ሲሆን፤ ” መንግስት የወሰደው የኃይል እርምጃ ተመጣጣኝ ነው” ካሉት የኮሚሽኑ አባላት መካከል አንዱ ናቸው። የሁለት ደቂቃ ቪዲዮ ነች፤ ስሟቸው ›(ቪዲዮ- ካሳ አንበሳው) እነ መላኩ ተፈራ ስለጨረሱት የጎንደር ሰው እንኳ እንዲህ የተጋነነ ውሸት አልተሠማም።

ቪዲዮ …. መቼም ሰው እንደ ተማረው ትምህርትና እንደ አስተዳደጉ ነው የሚወጣው  [ደረጀ ሓብተዎልድ]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.