ሰበር ዜና . . .   በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ የሚገኙ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ተገደሉ (በልኡል አለሜ)

34የ ላንግላታ ፖሊስ ስቴሽን ወይም ላንግላታ እየተባለ የሚጠራዉን አካባቢ የሚቆጣጠረዉ ፖሊስ ስቴሽን ኮምንደር እንደገለጸዉ በጆሐንስበርግ ሜይፌር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ የሚኖሩ ሶማሌዎች እና ኢትዮጵያዊያን የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች በፈጠሩት አለመግባባት የአካባቢዉ ሰላም ከመቃወሱ በላይ ግጭቱ ለ7 ሰዎች የሞት ምክንያት ሲሆን ለሁለት ግለሰቦች የመቁሰልና ለ5 ሰዎች የእስር እንዲሁም ለበርካቶች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ችግር ፈጥሯል።

በሶማሌ የአዉያ ብሔር  ግለሰቦች እና በኦሮሞ ኢትዮጵያዊያኖች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት ከተከሰተ ወዲህ የኦሮሞ ህብረተሰብ ለተገደሉ ሁለት የሶማሌ ልጆች 800.000 ሺ ራንድ ካሳ ከከፈሉ በሗላ አለመግባባቱ ይበርዳል ተብሎ ቢገመትም በትናንትናዉ እለት ሁለት ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸዉ አህመድ ጀማል እና ሐፊዝ የተባሉ የኦሮሞ ወታቶች ከረፋዱ ላይ በባለ 38 ሚሊ ሜትር ማካሮዝ ሽግጥ በሶማሌ ወጣቶች ከተገደሉ ወዲህ ችግሩ እንደና ያገረሸ ሲሆን ከግድያዉ በሗላ የበቀል እርምጃ ለመፈጸም የተንቀሳቀሱ 3 የኦሮሞ ወታቶች ከነታጠቁት መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፤፤

ፖሊስ ፈይሰል የተባለ ግለሰብን ጨምሮ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ከመግለጹ በላይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት አላቸዉ የተባሉ ሌሎች ግለሰቦችን ለመያዝ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታዉቋል

አንድ በሜፌር አካባቢ የሚኖር ግለሰብ እንደገለጸልን ከሆነ ” ሶማለዎቹ ሆን ብለዉ ከሗልህ ይመጡና በኦሮምኛ ሰላምታ ይሰጡሃል በኦሮምኛ መልስ ስትመልስ በጥይት ጀርባህን ብለው ይሄዳሉ በንግድ ቤታችን ዉስጥ በመሳሪያ የታገዘ ዘረፋ ይፈጽሙብናል መኖሪያ ቤታችን ይከበባል መንገድ ላይ ስትሄድ አስነዋሪ ስድብና ዛቻ ይደርስብናል ” ሲል ተናግሯል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያናገርናቸዉ የፖሊስ ኮማንደር እንደገለጹት በማንኛዉም መልኩ አደጋ ይፈጥራሉ ወይም አደጋ ፈጥረዉ የተሰወሩ ግለሰቦችን የተመለከተ ማንኛዉም ግለሰብ በነዚህ ስልኮች መረጃ እንዲሰጥ ኤጻጽቤኣል  Langlaagte – 011 473 6200 @@@@@@ Johannesburg Central – 011 497 7000   እነዚህ በፎቶዉ ላይ የምትመለከቷቸዉ ሶማሌያዉያኖች በግድያዉ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ሲሆኑ ግለሰቦቹን ለፖሊስ በመጠቆም ወንጀልን እንድንከላከል ጥሪ ተደርጓል።