ቅርሻትህን መልሰህ ,,,,,,,,, ግርማ ቢረጋ/ ስቶክሆልም

unity-ethiopia-satenaw-news-2ህዝብ እያወቀ የማያውቅበት ግዜ ያለፈበት ይመስላል ምክንያቱም ለሃያ አምስት ዓመታት በጫንቃው ተሸክሞ ከነገ ዛሬ ይማራሉ ወይም ማስተዋልን ያገኛሉ ብሎ እድል ሰጥቶ እሱ እየጠፋ ነገር ግን ገዢዎች ይማራሉ ብሎ ሁሉን ችሎ በደሉን እንደበደል ሳይሆን እንደ ፀጋ ተቀብሎን የሚኖር ህዝብ የለም እኔን ፈርተህና አከብረህ ኑር ለመኖርህም ዋስትናህ እኔ ነኝ ምን መብላትም ሆነ መናገር እንዳለብህ እኔ ነኝ የምፈቅድልህ በማለት ፍጡርን ከፍጡር በታች አሳንሰው የሚያዩ ውርጋጥ የበታችነት በዘር ማንዘራቸው ሰፍኖ እነሱ ኩንትሪ ለቅመውና ቁልቋል ልሰው በሚበሉበት ዘመን ነጭ ጤፍ ጋግሮ የሚበላ የነበረን የኢትዮጵያ ገበሬ ዛሬ ለስደቱና ለአሳ ነባሪ እራት መሆን እነሱ ምክንያቶች ሆነው መገኘትን እንደ ጀብዱ በመቁጠር በህይወቱ ላይ በመቀለድ ያሳለፉት ሁሉ ልክ ከማሰሰገባት ባለፈ ባገኘበት ሁሉ እየደቆሰና አሳሩን በማሳየት የጀመረውን የተጋድሎ ውጤት ጫፍ ለማድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አኮብኩቦ ይገኛል ።

በሌላ አቅጣጫ ደሞ ሁሌም ምሁር አዋቂ መስሎ የሚታያቸው ጥቂት በተቀደደላቸው ቀዳዳ መፍሰስ የሚፈልጉ ከዘረኝነትም ባለፈ እራሳቸው የራሳቸውን ማንነት ፈልገው ማግኘት ሲገባቸው አንድ ማንነቱን የረሳ መረን በተለፋደደ ቁጥር ማጨብጨብ የሚያበዙ ትውልዶችም ማየት ጀምረናል ።

እና ታዲያ ኢትዮጵያችን ምን ትሁን በድህነት አረንቋ ተደፍቃ ባሳደገች መፈራረስን መመኘቱ ታዲያ የዶክተርነት መገለጫ ነው? ጥቂቱን ለሃገሩና ለወገኑ ተቆርቋሪ ምሁር መጎንተል አይሁንብኝ እንጂ ይህን ቃል በአደባባይ ከማውጣት በላይ ምን ደደብነት አለ ለነገሩ ከለማበት የተጋባበት ሆነና አጨብጫቢው አብሮ ማላዘኑ ከመገረምም ባለፈ አዘቅቱ የትም ድረስ እንደማያስኬደው አለማወቁ አንዳንዴ ከሰውነት በወረደ ደረጃ ብዙ ሰዎች አብረው መቆጠራቸው ትንሸም ቢሆን ምን አይነት ዘመን ላይ እንደተደረሰም ለመገመት ያስቸግራል።

ማንም ምን አለ ወይም አመጣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሁሌም የሚያሳስባቸው ከተራው ገበሬ ጀምሮ እስከ ታላቁ ምሁር ድረስ ሃገራችን ያለችበት ሁኔታ አሳስቧቸው ግንባራቸውን በጥይት ከመገመስ ባለፈ ሃብት ንብረት ወይም ቤተሰብ ሳያሳሳቸው በረሃ በመውረድ ለመስዋዕትነት እራሳቸውን የዘጋጁትንም መመልከት ይቻላል ። ሁሌም ከአንደበት የሚወጣውን ማስተዋል ያሻል እንደኔ እንደኔ በማህበራዊ ሚዲያዎች ስክሪን ያየውት የሰውየውን ንግግር ሣይሆን ያን ሁሉ አልፎ የመጣውን አዛባ አዛባ የሚሸት ክርፋቱን ብቻ ነው ደግሞም ወደደም ጠላ ይህን ቅርሻቱን የሚውጥበት ቀን ሩቅ አይሆንም።

ድል ለታጋይ አርበኞቻችን!!!
ስቶክሆልም ኦክቶበር 2016

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.