«ህወሀት» ወይንስ የማታለያ ጭምብሉ «ኢህአዴግ»? [አቻምየለህ ታምሩ]

TPLF (1)የቀድሞ ባልደረባየና ወዳጄ አብርሀ ደስታ ተቃማዊዎችን በተደጋጋሚ «ወያኔ ወይንም ህወሀት አትበሉ» ፤ የልቁንም «ኢህአዴግ በሉ» በማለት እየመከረ ያለበት ያለው ሁኔታ ነው ያለው። ይህ ምናልባት ወያኔ ላይ ትኩረቱ ሲበረታ ወያኔ ከትግራይ በመሆኑ «ወያኔ ሲጠቃ ትግሬ ተጠቃ ማለት ነው፤ ይህ ማለት ደግሞ እኔም ተጠቃሁ ማለት ነው» ከሚል መንፈስ ካልሆነ በስተቀር «ኢህአዴግ» የሚባለው የዳቦ ስም ነፍሱ እንደሌለ፤ይልቁንም የአገራችን አገዛዝ ብቸኛ አልፋና ኦሜጋ የትግራይ ግፈኞች ማህበር የሆነው ወያኔ ብቻ እንደሆነ ለመገንዘብ በዚህ ህዝብ እንደቅጠል በጥይት በሚጨፈጨፍበት ወቅት ከህዝብ ወገን የሚቆሙ ህሊና ያላቸው የዘመናችን ዳዊት ወልደ ጊዮርጊሶችና ጎሹ ወልዴዎች አለመኖራቸውን መታዘብ ከበቂ በላይ ነው።

በዚያ ላይ አገዛዙ [በስልጣን ላይ ያለውን ነውረኛ ቡድን ማለቴ ነው] አራት መሰረታዊ ምርኩዞች ወይንም የኃይል ምንጮት ያሉት አካል ነው። እነዚህ መሰረታዊ የኃይል ምንጮች መከላከያ፣ ደህንነት፣ ኢኮኖሚውና የውጭ ጉዳይ ናቸው። የአንድ አገዛዝ ጥንካሬ እነዚህ የኃይል ምንጮች ላይ ባለው የቁጥጥር መጠን ይለካል።

መከላከያውና ደህንነቱ የወያኔ የግል ንብረት እንደሆነ አብርሀ ደስታ የሚስተው አይመስለኝም። ኢኮኖሚው የማን እንደሆነ አብርሀ ደስታ ራሱ የመረጀውን የኤፌርት ካምፓኒዎች ካፒታል ማየቱ በቂ ነው። የወያኔው አምበልና ለአባትነት የማይበቃው «አቦይ» የሚሉት ስብሀት ነጋ [ በትግርኛ አቦይ ማለት አባት ማለት ነው] በአፍሪካ ውስጥ ኤፌርትን የሚያህል ኩባንያ እንደሌለ ተናግሯል። ይህ ማለት አይደለም በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔን የሚያህል ሀብታም በአፍሪካ ውስጥ የለም ማለት ነው። ውጭ ጉዳዩ በማን እጅ እንዳለ ለማወቅ ሩቅ ሳንሄድ የቀድሞው የወያኔ ታጋይ ተስፋዬ አጽብሀ ያጠናውን መመልከት በቂ ነው። ተስፋየ አጽብሀ እንዳለው «በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ ወያኔ ዘመን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤቶች በአንድ ሰፈር ሰዎች ተይዘው አያውቅም»። ስለዚህ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ የወያኔ ኩባንያ ነው ማለት ነው።

እንግዲህ! የችግሮች ሁሉ ምንጭ የሆነውን፤ ከትግራይ የበቀለውንና በትንሹ አራቱን መሰረታዊ መንግስት የሚያደርጉ ምርኩዞችን ወይንም የኃይል ምንጮችን በብቸኛነት ተቆጣጥሮና ጠይፍሮ የያዘውን ወያኔን ትተን ኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን ላይ የሌለውን ኢህአዴግን የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ ማድረግ ማለት ከነውርም ያለፈ ወንጀል እንደመስራት ይቆጠራል።

ወያኔ ከትግራይ በመሆኑ «ወያኔ ሲጠቃ ትግሬ ተጠቃ ማለት ነው፤ ይህ ማለት ደግሞ እኔም ተጠቃሁ ማለት ነው» የሚል ከሆነ አንድ የወያኔ ተቃዋሚ ነኝ የሚል የተከዘ ማዶ ሰው፤ ወያኔን «ኢህአዴግ» በሚባለው የማታለያ ጭምብሉ ጥሩት ከሚለን ተባኖበታልና ለወያኔ ያለውን መቆርቆር በማታለያ ጭምብሉ ሳይሸፍን ማታለያ ጭምብሉን አውልቆ አሰላለፉን ቢያስተካክል ይቀለዋል እላለሁ። በግልጽ አፍጥጦ የሚታየውን እውነት በመፈላሰፍ ማሽሞንሞን አይቻልም!

በኢትዮጵያ ቤተ መንግስት በግፍ ዙፋኑ ላይ ያለው ከትግራይ የበቀለው ወያኔ የሚባለው ነውረኛ ቡድን ነው። እውነት ነው ማፍያ ቡድን ለመዝረፍና ለመግደል የማታለያ ጭምብል ያጠልቃል። ወያኔም እንደ ማፍያ ቡድንነቱ «ኢህአዴግ» የሚባል የማታለያ ጭምብል አጥልቋል። «ኢህአዴግ» የሚባለው የማታለያ ጭምብሉ ግን ወያኔን ኢህአዴግ አያደርገውም። በመሆኑም ወያኔ የማታለያ ጭምብል መልሰቡ ኢህአዴግ ያላደርገው ከነ ማታለያ ጭምብሉ መጠራት የለበትም።

ስለዚህ በመንግስትነት የተሰየመው ነውረኛ ቡድን የቅሚያ፣ የዘረፋና የግድያ ድርጅትነቱ ታውቆና «ኢህአዴግ» የሚለው የማታለያ ጭምብሉ መልቆ፤ በግዙ ዙፋኑ ላይ በተቀመጠበት ማዕረግ በሽፍትነቱ ተለይቶ፤ ተግባሩም የትግራይ ግፈኞች ክፉና ትዕቢተኛ ፍላጎታቸውን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ገደብ ለማስፈጸምና ለወንጀል ያቋቋሙት ፋሽስታዊ ቡድን እንደሆነ ታውቆ በእውነተኛ ስሙ ፋሽስት ወያኔ ተብሎ መጠራት አለበት።