ከባዱ ማስጠንቀቂያ ለአሜሪካ ዴሞክራሲ! [ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው]

አለምነህ ዋሴ አዋዜ ዜና……ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ 45ኛው ፕሬዚደንት ሆኖ ታወጅበቅድመ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት የአሜሪካ መንግሥት ንብረት የሆነውን ቪኦኤን ጨምሮ ሌሎች
የብዙኃን መገናኛዎችና አንዳንድ መንግሥታዊ ድርጅቶች በዶናልድ ትራምፕ ላይ ከሠሩበት አሳፋሪና ኢዲሞክራሲያዊ (ኢመስፍነ ሕዝባዊ) ሸፍጥ አኳያ
የአሜሪካ ምርጫ ቅድመ ሁኔታ ያለበትና ምንም ይሁን ምን ሕዝብ የፈለገውን ሰው ሊመርጥ የማይችልበት ምርጫ ነው ማለት ነው፣ አንድን ተመራጭ ሕዝብ ሊመርጠው የሚፈልገው ቢሆንም የአሜሪካ ዴሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) ሊያስተናግደው የማይፈለግ የተመራጭ ዓይነት እለ ማለት ነው፣ ሕዝብ ከመምረጡ በፊት ውሳኔው እንደ ዶናልድ ትራምፕ ያለውንየአሜሪካ ዲሞክራሲ ሊያስተናግደው የማይፈለገውን ዓይነት ሰው እንዳይሆን ጣልቃ ተገብቶ የማስቀየስ ሥራ  ይሠራል ማለት ነው ብየ ደምድሜ ነበር፡፡ በእርግጥ አሁንም ምርጫውን ካስፈጸመው አካል ውጭ በብዙኃን መገናኛዎቹና በአንዳንድ መንግሥታዊ አካላት ላይ የነበረኝ ቅሬታ አሁንም እንዳለ ነው፡፡ የብዙኃን መገናኛዎቹ ሚዛናዊ የሆኑ ለመምሰል ጥረት ቢያደርጉም ሸፍጠኛ ተግባራቸውን ግን በፍጹም መደበቅ አልቻሉም፡፡ ሸፍጠኛ ኢዲሞክራሲያዊ ተግባራቸውን ደብቀው ዓላማቸውን ማሳካት አይችሉም ነበርና፡፡

የብዙኃን መገናኛዎቹ ዶናልድ ትራምፕን በማጥላላት  ሂላሪ ክሊንተንን በማወደስ ሕዝብ ድምፁን ለ ወ/ሮ ሂላሪ እንዲሰጥ ግፊት በማድረግ ፣ ጫና በማሳደር ሥራ ላይ ተጠምደው ነበር፡፡ አቶ ትራምፕም ይሄንን የብዙኃን መገናኛውን ሸፍጥ በተደጋጋሚ ሲኮንንና ሲያወግዝ ሰንብቷል፡፡

ሲመስለኝ በዶላልድ ትራምፕ ላይ እንዲህ ዓይነት አቋም የተያዘበት ምክንያት በጽንፈኛ ውጭ ጉዳይ መርሖው ወይም መመሪያው (ፖሊሲው) ምክንያት “ሰውየው ቢመረጥ ሀገራችንን ለከፍተኛ ችግር ዳርጎ ለውድቀት ይዳርግብናል!” በሚል ሥጋት ነው ሊተባበሩበት የቻሉት፡፡ ይሁንና “ወሳኙ ሕዝብ ነው!” ከተባለ የፈለገ ነገር ቢሆን ውሳኔው ማንም ጣልቃ ሳይገባበት ለሕዝብ ሊተው ይገባ ነበር፡፡ ይሄኔ ነውና ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) አለ ሊባል የሚችለው፡፡ የአሜሪካ ሕዝብ አልታመነም፣ ተንቋል፣ ሥልጣኑን እንዳይጠቀም ለማድረግ ተጥሯል፣ እነኛ አካላት የፈለገውን የማድረግ መብቱ ሕዝብ እጅ ላይ መሆኑ አልተመቻቸውም፣ አሳስቧቸዋል፣ አስጨንቋቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ለአሜሪካ ዲሞክራሲ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው  “ይህች ጥሬ ካደረች!” እንዲሉ ይህ ኢዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብና ተግባር አሁኑኑ በእንጭጩ ካልተቀጨ ነገ ጎልብቶ የምርጫ ውጤት እስከመቀየር ሊደርስ እንደሚችል ያሠጋል፡፡

እውነቴን ነው የምላቹህ ቅድመ ምርጫ ከነበረው ሁኔታ አንጻር ትራምፕ ቢያሸንፍም ውጤቱ ተገልብጦ የሂለሪ አሸናፊነት ይታወጃል እንጅ ትራምፕን “አሸንፈሀል!” ብለው ያበስሩታል ብየ በፍጹም አልጠበኩም ነበረ፡፡ እንድጠረጥር ካደረጉኝ ነገሮች አንዱ ነገ ስለሚሆነው ነገር ማንም እርግጠኛ ሊሆን በማይችልበት ሁኔታ ዶናልድ ትራምፕን “የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነዎት ወይ?” ሲሉ መጠየቃቸው ነው፡፡ እንዲህ ብለው መጠየቃቸው “አንዳች ነገር ሊያደርጉ ካላሰቡ በስተቀር ይሄ ጥያቄ በፍጹም አሜሪካን ሀገር የሚጠየቅ ጥያቄ አይ

አልነበረም!” አሰኝቶኝ ነበር፡፡ ቆይ ትራምፕን ጠንቋይ ነው ብለው ካለሰቡ በስተቀር በአደባባይ ስንት አግባብ ያልሆነ ሥራ እየተሠራበት እያየ ምርጫው ነጻና ፍትሐዊ ሆኖ መጠናቀቅ አለመጠናቀቁን እንዴት አውቆ ነው ለዚህ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ የሚጠበቀው? እንዴትና ለምንስ ነው አስቀድመህ “አዎ በል!” የሚባለው? ይሄ በነጻ የማሰብ መብትን መንፈግ አይደለም ወይ? የአሜሪካ ምርጫ ፍጹም ነጻና ፍትሐዊ የመሆኑ ጉዳይ ማንንም የማያጠራጥርና የሚያስተማምን ከሆነ እንዴት እንዲህ ተብሎ ይጠየቃል?

እኔ ዶናልድ ትራምፕን ቢያደርገኝ “የእነኝህ አካላት ተግባርና የሰዎቹ አስተሳሰብ ፀረ ዲሞክራሲያዊ መብትና አስተሳሰብ እንደሆነ፣ ለአሜሪካ ሕዝብ ከፍተኛ ንቀት ስድብና መሠረታዊ የዲሞክራሲ መርሖ ጥሰት እንደሆነ፣ የእነኝህ አካላት ተግባርና አስተሳሰብ ፀረ ዲሞክራሲ በመሆኑ በእነኝህ አካላት እጅ ነጻና ፍትሐዊ የሆነ ምርጫ ሊደረግ አይችልምና ኡኡ የአሜሪካ ሕዝብ ሆይ! ይሄ ነገር ካልተስተካከለ በስተቀር ድምፅህ ዋጋ የለውም! የአሜሪካ ሕዝብ ለሉዓላዊ መብቱ መከበር ሲል የእነኝህ አካላትን ነውረኛና ኢዲሞክራሲያዊ ተግባር በማውገዝና በመቃወም ከጎኔ ቁም!” ስል አበክሬ እጠይቅ እጮህ ነበር፡፡ ትራምፕ ግን ያደረገው እንደተበደለና ከባድ ሥጋት እንደተጋረጠበት እያወቀና እየተናገረ ሐሜት ከማሰማት አላለፈም፡፡ መብቱን መጠየቅና ሕግ ይከበር! ከማለት ደረጃ ላይ ደርሶ ለሕዝብ አቤት! አላለም፡፡ ለካ የአሜሪካ ሕዝብ ሆየ የሰውየው መበደል አሳዝኖት የብዙኃን መገናኛውና የአንዳንድ መንግሥታዊ ተቋማት ቅሌት አብግኖት ኖሮ ድምፁን ለትራምፕ በመስጠት ትራምፕን ሊክሰው እነኛን አካላት ደግሞ አይቀጡ ቅጣት ሊቀጣ ቻለ!

ሌላው የገረመኝ ነገር ደግሞ የትራምፕን ስም የማጥፋት ዘመቻ ወቅት ትራምፕ “ታዋቂነቴን ተጠቅሜ የፈለኳቸውን ሴቶች ቸብ አደርጋለሁ፣ ሳብ እያደረኩ እስማቸዋለሁ!” ማለታቸውን በማራገብ “ሰውየው ጨዋነት ይጎላቸዋል ስለሆነም ለፕሬዘዳንትነት (ለርኡሰ ሥልጣንነት) አይመጥኑም!” በማለት ሰውየውን ለመጣል ያደረጉት ጥረት እጅግ ነበር የገረመኝ፡፡

ምክንያቱም አንደኛ ፖለቲከኞቻቸው (እምነተ አሥተዳደራውያኖቻቸው) እና የእምነት መሪዎቻቸው ግብረሰዶምን ፈጻሚና የዚህ ጸያፍ ተግባር ደጋፊ አቀንቃኞች ሲሆኑ፣ ግብረሰዶማዊነትን የሚያክል ወንጀል ሕጋዊ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማድረግ የመከላከል አቅም አተው ተደፍረው ወይም ተጭበርብረው በጨካኝና ወንጀለኛ ደፋሪዎቻቸው በመደፈር ወደዚህ ማጥ ውስጥ እንዲገቡ በተደረጉ የሥነልቦና ቀውስ ወይም ሕመም በሚያሰቃያቸው ሕፃናትና አዋቂ ዜጎቻቸው ቁስል ላይ እንጨት የሰደዱ ሲሆኑ፣ ይህን የመድፈር ወንጀልን የሚፈጽሙትን ለፍርድ ማቅረብ እንዲሁም ተደፍረው ወደዚህ ጸያፍ ተግባር እንዲገቡ የተደረጉትን የሥነ ልቡና ሕክምና በመስጠት ከዚህ ማጥ ውስጥ እንዲወጡ ማድረግ ሲኖርባቸው ተፈጥሯዊ ያልሆነንና ከአካላዊና ሥነልቡናዊ ጤና አኳያም እጅግ ጎጅ የሆነውን ፆታዊ ግንኙነት “ሰብአዊ መብት ነው!” ብለው ሕጋዊ በማድረግ አጥቂዎቹ ጥቃታቸውን በነጻነትና በሰፊው መፈጸም የሚችሉበትን ሁኔታ ሲፈጥሩ “ጨዋነት የጎደለው ተግባር ነው!” ሳይሉ በተገባ መንገድ ባይሆንም ተፈጥሯዊ የሆነውን ፆታዊ ግንኙነት የፈጸሙትን “ጨዋነት የጎደላቸው ናቸው! ለፕሬዚዳንትነት አይመጥኑም!” ብለው መኮነናቸው ሲሆን፡፡
ሌላው ተመራጮቹ በዚህ ደረጃ መመርመር መመዘን መፈተሽ ካለባቸው አሁን ማን ይሙትና ወ/ሮ ሂላሪ ያለ ክሊንተን ማንንም የማያውቁ ቢያንስ እንኳ አቶ ክሊንተን ከሞኒካ ጋር ቤተመንግሥት ውስጥ ከቀበጡ በኋላ እልህ ገፋፍቷቸው ያልወሰለቱ ሆነው ነው ሰውን “ጎነተልክ! ሳምክ!” እያሉ ሀገር ይያዝልኝ ሲሉ የሰነበቱት? ፈጽሞ የማይመስል ነገር ነው፡፡ ነው ወይስ የጨዋታው ሕግ “የፈለከውን አድርግ! ነገር ግን እንዳይታይ እንዳይሰማ አድርገህ ደብቅ!” የሚል ነው? ይሄ ከሆነ መለኪያው ጨዋነት ሳይሆን የመዋሸት የማስመሰል ችሎታ ነዋ?

1ለማንኛውም የአሜሪካ ሕዝብ ነጻ ዳኝነቱን ሰጥቶ ኩም ስላደረገልኝ ደስ ብሎኛል፡፡ እኔም በበኩሌ ለትራምፕ አሜሪካ ኗሪ የመምረጥ መብት ላላቸው ኢትዮጵያውያን ትራምፕን እንዲመርጡ

በማለት በመጽሐፈ ገጽ መዝገቤ (በፌስቡክ ገጽ አካውንቴ) ቅስቀሳ አድርጌ ነበር፡፡

እንግዲህ ቀጥተኛ ተናጋሪውና ማስመሰል የሚባል ነገር የማያውቀው አቶ ትራምፕ የአሜሪካ የዓለም ፖሊስ (ጸጥታ አስከባሪ) ነኝ ባይነቷ በታወሰው ጊዜ ብመረጥ “I will

lock African dictators in prison if I

become a President of USA” ብሎ ነበርና “ወያኔን ጨምሬ ጨካኝ አንባገነን የአፍሪካ ገዥዎችን እያንጋጋሁ ወሕኒ አጉራቸዋለሁ!” ብሎ አፍሪካን ጭር እንዳያደርግብን ንገሩልን? ይሄ ተገቢ አይደለም የሰው ሀገር ሉዓላዊነትን መድፈር ነውና! lol.

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.