በማግስቱ [አስፋ ጫቦ]

አስፋ ጫቦ Dallas Texas USA
donaldዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን ፕሬዚዳንት ሁኖ ትላንት ማታ ተመርጧል!! የህ እውነት ነው! ማሸነፍ አልነንበረበትም፤በዚያምክንያት ነው፤በዚህኛው ምክን  ያት ነውያሸነፈው፤እንዲህ፤እንዲያ ቢደርግ ኖሮ የሚሉ አዋቂዎችም፤ አዋቂች ነን ባዮችም፤ አለአዎቂዎችም፣የኔቢጤዎችም ለዘመናትይተቹታል፤ይተቹበታል። ያ “ጅብ ከሔደ ውሻ ጮኸ!” ነው የሚሆነው።
የዛሬ ስንትስ አመት የአሜሪካን ህዝብ ምንኛ ደንቆሮ ቢሆን ነው ጆርጅ ደብሊው ቡሽ የሚባል መሐይም ለፕሬዚዳንትነት የመረጠው?” የሚል ርእሰ አንቀጽ አንድ የእንግሊዝ ጋዜ ጽፎ ነበረ።  The Daily Mail ይመስለኛል።አንዱ አንሶ ሁለቴ ተመረጠ! ይኸው ዛሬ ቡሹ ያቀጣጠተለው ሰደደ እሳት መላውን መካከለኛ ምስርራቃ ያጋያል! ለአፍሪቃም ተርፏል! አልሸባብ የአልቄይዳ ግልገል ነውና! አሜሪካንና አውሮጳም እየተለበለቡ ነው። በሊቢያ በርሐ የተቀለቱን ኢትዮጵያውያን የዚያ ቃጠሎ ወጤት ናቸው!

ትራምፕ እንዴት፣ለምን አሸነፈ በሚባለው ላይ አሁንም ሙሉ ስራቸውም፣የግማሽ ጌዜ ስራቸውም፤ እንደኔ ያሉ ስራቸው ያልሆነውም ጭምር ለዘማናት የሚተቹት፤የሚተቹበት፤ጠጉር የሚሰነጥቁበት ይሆናል የሚል ግምት አለኝ። እንዴኔ እንደኔ ትርምፕ ያሸነፈው በሕዝብ አመጽ ነው።  አሜሪካን ሕዝብ አመጽ ነው።

ምን አይነት አመጽ ?  አመጹ የተቃዉሞ ድምጽ! Protest Vote “ የሚሉት ነው። ማንን ነው የሚቃወሙት? ። “ሥረ አቱ (The Establshmnet “ የሚሉትን ነው። ስርአቱ የሚሉት የአሚሪካንን ፈዴራል መንግስት  አሰራር፤ አሜሪካንን ለዘመናት እየተ ፈራረቁ በገዙት፤በነዱት የሬፑብሊካንና የዲሞችራቲክ ፓርቲዎች ላይ ነው። አጭሩ፣ ለመላው ሕዝብ 99  እጅ (99 Percent) ሳይሆን ለአንድ እጁ (1 Percent)የሚሠሩትን ማለት ነው

ይህ ተቃውሞ እንዴት ተገለጠ? ልብ የማለት፤የማስተዋል ወይም ለማስተዋል የመፈለግ ጉዳይ ይመስለኛል። የአሜሪካን  ሕዝብ ስለዶናልድ ትራርም የተነገርውን ጉዳ- ጉድ አል ሰማሁም፣ አላየሁም አላለም! መስማት አልፈልግምም አላለም! ማጋጣ፤ባለጌ፤ ቀጣፊ፤ ዛሬ የተናገረውን ነገ በጠራራ ፀሐይ የሚክድ መሆኑን፤ አጭበርባሪ መሆኑን፣ዘረኛ፤ሴት የሚንቅ ፤የሚዘልፍ፣ የሚያዋርድ መሆኑና ሌላ ሌላውንም አልሰማሁም አላየሁም አላለም! ስምቻለሁ አይቻለሁ ሆኖም እናነት ይሻላል!” ነው ያለው። ከእናነት ይሻላል የሚለውየስር አቱ ሰዎችና ድርጅቶች  (The Establishment)ከሚላቸው ነው። የዋሽንግቶን ወንበዴዎች The D.C Mafia ይሏቸዋል። በዚሁ መሠረት ሂለሪ ክልኒተን የዚህ የውንበዴው ቁንጮ መሆኗ ነው።

እንግዲህ አንድ ዋና ነገር ልብ ማለት ያለብን ይመስለኛል። ትራምፕ ያሸነፈው ክሊንትንና ደሞክርቶችን ብቻ አይደለም። የራሱን ፓርቲ ረፑብሊካኖችንም አሸንፏል!አለደገፉትም፤አለፈለጉትምና!ይህ” ሙያው ትችት Critic)የሆነውንም ነገድ አሸንፏል! ተንቢት ተናጋሪዎችንም(Pollisters) አሸነፏል! መገናኛ ማእከላትንም (Mass Media)አሸንፏል! የተነብየት፣ የተቹት አልሠመረምና!  በ አጭሩ ያላሸነፈው ክፍል የለም!

ያም ሁኖ ትርምፕ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል? አንዴታ!  አሁን የአሜሪካን መንግስት ልክ እንደወያኔ የአንድ ፓሪቲ መንግስት ነው። ምክር ቤቱንም(Congress) ተቆጣጥረዋልና! አሜሪካን መንግስት ዘላቂ ለውጥ የሚያመጣው ፕሬዚዳንቱ ወይም ምክርቤቱ(Congress) ሳይሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ(Supreme Court) ነው። አሁን 8 ዳኞች ብቻ ስለአሉ አንዱን ትራምፕ ይሠይማል! አንድ ሶስቱ በምርኩዝ ስለሚሔዱ በአራት አመት ውስጥ ሌላው ቢቀር ሶስት ዳኛ የመሠየም እድል አላው። ዳኞችአንዴ ከተሠየሙ  ሞት ብቻ ነው የሚገላግላቸው።  ስለዚህም ትራምፕ በአለም ላይ ለውጥ ማማምጣት መቻል አለመቻሉ የሚያነጋገር ቢሆንም አሜርካን ላይ ለውጥ ማምጣት መቻሉ ብዙም አይነጋገርም። ሁሉንምታውቁኛላችሁኮ !አርፋችህጭ ተቀመጡ!” ማለት ይችላል። ማንም ውለታ የሰራለት የለምና

ትራምፕበኢትዮጵያ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ሊኖር ይችላል? ይህ የሚያነጋግር ነው። እንደኔ እስከ ዛሬ ድረስ ኢትዮጵያ ላይ ለውጥ ያመጣ የአሜሪካን ፕሬዚዳንት ስለሌለ ትራም የተለየ የሚሆንበት ምክንያኛት አይኖረውም።እኔአይታየኝም! የአሜሪካን መንግስት ፤የማንኛውም መንግስት፣ መሠረታዊ መርሆ ለራሱ ሕዝብና መንግስት ብቻ ነው። ከጥቅሙ ጋር ሲገናኛኝ የተባበራል። ወይም የሚተባበር ይመስላል!!

በተለየ ኢትዮጵያን በሚመለከት ሁሌ የምታዘበውና የሚገርመኝም አለ። ብሩክ ኦባማ የወያኔ ደጋፊ ነው የሚል ጽሑፍ በድሕረ ገጾችም ላይ፤ስልፍ ላይ በሚያዙ መፍክሮችም ላይ አያለሁ። ምሁራን ነን የሚሉ፣የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሶርች ጭምር ስለኢትዮጵያ ሲጽፉ የ አሜሪካንን ሕገ መንግሰ ጠቅሰው “አሜሪካ የሰው ልጅ መብት የተከበረባት አገር” አድርገው ያቀርባሉ። አብዛኞዎቹ እንዲህ ባዮች፤ማለትም ጽሐፊዎቹ፣ እዚህ አሜሪካ ያሉ ፤በተለምዶ ዳያስፖራ ተበሎ የሚታወቁቱ ናቸው። በአይናቸውን የሚያይቱን ትተው  የሚያነቡትን ያምናሉ እንደማለት ይመስለኛል። ማን ይሙት አሜሪካ የራሱን ጥቁር በ አብዛኛው ከሰው ልጅ በታች አድርጎ የሚያኖር፤ በነጋ በጠባ በፖሊስ ጥይት የሚዘርር፤ ወህኒ ቤቶችን ሌላው የጥቁሮች መኖሪያ አገር ያደርገ ፤ እዚያ ከዉቂያኖስ ማዶ ላለች ኢትዮጵያ በተለየ ሊይስብ የችላል ማለት፤ ወይ ከንቱ ምኞት፤ ወይም እውነትን ማየት አለማቻል፤ ወይም አይቶም መቀበል አለመፈለግ ይመስለኛል።

አሜሪካ ከላይ በገለጽኩት ምክን ያት ኢትዮጵያን ተፈልጋለች። መካከለኛው ምስራቅ ላላት ጥቅም ማስከበሪያ ለጦር ሰፍርነት(Military Base) ብቻ ነው። ልክ ጁቡቲን የምትፈልገውን ያክል ማለት ነው። አንስተዉታል ሲሉ የሰማሁ መስለኝ እንጅ አሜሪካ አርባ ምንጭም የጦር ሰፈር ነበራት።

እዚህ ቦታው ስለአልሆነ አልገባበትም እንጅ በኃይለ ሥላሴ ጊዜ በአሜሪካና በኃይለ ሥላሴ ጊዜ የነበረው ግንኙነት ትንሽ ራሱን የቻለ ድራማ ነበር።   John Spencer, Ethiopia at Bay   በሚለው መጽሐፋቸው በኒክሰን ዘመን የኃይለ ሥላሴን ጉብኝት አስመልክተው የጻፉት የሚያሳፍር አይነት ባህርይ ያለው ነው።

አንድ የረሳሁትን ልጨምር! የኢትዮጵያ ህዝብ አመጽና የአሜሪካ ሕዝብ አመጽ የሚመሳሰልበት ነጥብ ያለው ይመስለኛል። ሁለቱም በሥልጣን ላይ ያለውን ሥረ አትአንፈልግምወግድልኝ!” ነው።           የአሜሪካው የተሳካ ይመስለኛል። ኢትዮጵያ በእንጥልጥል ቆየብኝ!

ሁሌ ስለ አሜሪካ ተምክሮዬ(Experience) እጽፋለህ እልና እዘነጋለህ። አሁን መጀመሬ የሚቀር አይመስለኝም!

የዚያ ሰው ይበለን! “መልካም የትርምፕ ዘመን “አይባል ነገር!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.