ሰሜን ጎንደር አምባጊዮርጊስ አካባቢ ልዩ ስሙ እንቃሽ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ለሶስተኛ ቀን ከባድ ውግያ የተካሄደ ነው ተባለ

ሙሉነህ ዮሃንስ
Amhara - satenaw 2ሰሜን ጎንደር አምባጊዮርጊስ አካባቢ ልዩ ስሙ እንቃሽ ተብሎ የሚጠራ የጀግና መፍለቂያ ላይ በገበሬው ሰራዊትና በአጋዚ መካከል የሚካሄደው በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ ከባድ ውጊያ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሏል።
በአጋዚ በኩል ከ80 በላይ እንደሞተና ብዙ እንደተማረከ ከቦታው አረጋግጠናል።ዲሽቃ፣ ብሬን፣ መትረጌስና ስናይፐር መሳሪያወች ተማርከዋል። ከገበሬው በኩልም እስካሁን ወደ 6 ጀግኖች ተሰውተዋል።
ወያኔ የተማረኩትን ወታደሮችና የቡድን መሳሪያወች መልሱልኝ በማለት የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች በመላክ የሸፍጥ ሽምግልና ቢጠይቅም ተዋጊው ህዝብ ዞር በሉ ብሎ አሳፍሮ መልሷቸዋል።
በውጊያ ያሉት ወገን በፍጥነት ከጎናችን በአካል ተሰልፎ እንዲያግዝ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል። ለሚያስፈልጋቸው የቁሳቁስ ድጋፍም አቅም ያለው ሁሉ ይረባረብበት ብለዋል። በተጨማሪም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በየአካባቢው የአጋዚን ሃይል እንዲታገልና ሃይሉን እንዲበትን የትግል አጋርነት ጠይቀዋል። ከቦታው እንዳጣራነው ከህዝባችን ጋር ውጊያ አንገጥምም በማለት እየከዳ የሚያመልጠው ወታደር ተበራክቷል።
በተመሳሳይ መልኩ በወልቃይት ቃፍቲያ ዱር ቤቴ ባሉ ወልቃይቶችና የትግሬ ሰራዊት መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ ነው። ወያኔ እዛም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ታውቋል።
ከእንቃሽና ከወልቃይት መልእክቱን ላደረሱኝ አመሰግናለሁ። እግዜር ሃይልና ብርታቱን አክሎ ይስጣቹህ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.