ጎሳን እና ሀይማኖትን እንደ እስትራቴጅ አጣምሮ የሚንቀሳቀሰዉ ጀዋር ማህመድ [ሸንቁጥ አየለ]

jawarጀዋር ኦርቶዶክስን ለማዋረድ አሁን በአትላንታ ያደረገዉ ስብሰባ ላይ አንድም የኦርቶዶክስ ተወካይ አልጋበዘም::በጀዋር እና ተከታዎቹ አንደበት የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የለም የሚል ትርክታቸዉን ቀጥለዋል:: የኦሮሞ ህዝብ ግን እስልምናንም ሆነ ክርስትናን እኩል በኩል የሚያመልክ ህዝብ ነዉ::

በ2007 ዓም (እንደ ፈረንጅ) ቆጠራ መሰረት ከኦሮሞ ህዝብ ዉስጥ 48 % (31 % ኦርቶዶክስ እና 7% ፕሮቴስታንት) ክርስቲያን ነዉ:: 47.6% የሚሆነዉ የኦሮሞ ህዝብ ደግሞ ሙስሊም ነዉ::ሆኖም ለጀዋር 48% የሚሆነዉ ክርስቲያን በተለይም 31% የሚሆነዉ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የለም::ፈጽሞ ኦሮሞም አይደለም::ጀዋር ዋና ግቡ አክራሪ እስላማዊ መንግስት መመስረት ነዉ::

አንዳንድ ክርስቲያኖች አሁንም ከጀዋር ጋር አብረዉ ይጨፍራሉ::በመጨረሻም በጀዋር ሜንጫ አንገታቸዉን ይመታሉ:: ደግማችሁ ጀዋርን አድምጡ::ሰሞሙኑን አትላንታ ላይ ያደረገዉን ስብሰባ ተከታተሉ::ከኢየሱስ ክርስቶስ ደም እና ፍቅር ይልቅ የጎሳ አጥንትና ደማችሁ ማርኳችሁ ከጀዋር ጋር እየጨፈራችሁ ያላችሁ ክርስቲያኖች በመጨረሻም የጀዋር ሜንጫ ያርፍባችኋል::

ይሄ ትንቢት አይደለም::ቀላል የፖለቲካ ስሌት ነዉ::አሁኑን ብትባንኑ ይሻላችኋል:: የኦሮሞን ህዝብ ትግል ለመበታተን ነፍጠኛ አማሮች የነደፉት ስልት ነዉ ብለዉ ብልጦቹ እነ ጀዋር እንደሚለፈልፉላችሁ እርግጥ ነዉ::ብዙዎቻችሁ የጀዋር ተከታይ ክርስቲያኖችም የጀዋር ዉሸት እዉነት እንደሚመስላችሁ ገሃድ ነዉ::

ይሄም ማለት እኔን እንደማትሰሙም ለእኔ በደንብ ግልጽ ነዉ::ከክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ይልቅ የጎሳችሁ ደም እና አጥንት ይበልጥ እያናወዛችሁ ነዉ እና የጀዋር ተከታይ ክርስቲያኖች ብዙ ቅር እንደሚላችሁ አዉቃለሁ::ቢሆንም እንደ አንድ ክርስቲያን ወንድማችሁ ይሄን መራራ እዉነት የማስገንዘብ ግዴታ አለብኝ:: ጀዋር ያቀደላችሁ አንድ ነገር ብቻ ነዉ::አክራሪ እስላማዊ መንግስት (ISS) ዋናዉ የጀዋር ተልእኮ እና አላማ ነዉ::

መላዉ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች መንገላጀጃችሁን ካላቆማችሁ ወዮላችሁ:: በክርስቶስ ሀይል ቆፍጠን ብላችሁ ብትቆሙ ይሻላችኋል:: ፍርሃታችሁን እና መንፈጭፈጫችሁን ከልባችሁ አዉጥታችሁ ጣሉት:: ለነገሩ እናንተም የጀዋር ሜንጫ ተመዞ እስክታዩት ድረስ አሁን ደማችሁ እንደ በረዶ የቀዘቀዘ እንደሆነ አዉቃለሁ::አሁን እንዲህ ፍርጥርጥ ተብሎ ስለጀዋር ስለተጻፈ እንኳን ብዙ ጥያቄ በህሊናችሁ እንደሚመላለስ እርግጠኛ ነኝ:: ቁም ነገሩ ግን አንድ ነዉ::ጠላት ጀዋር ክርስትናን በእግሩ ሊረግጥ በገሃድ እና በይፋ እየተንቀሳቀሰ ነዉና እዉነቱን ለመዋጥ ተዘጋጁ:: ቢመራችሁም ዋጡት::

ከጥቂት አመታት በፊት በራሱ በጀዋር አንደበት የተነገረዉን የጀዋርን የፖለቲካ ስትራቴጅ የሚያብራራዉን ይሄን ቪዲዮ በጥንቃቄ ተመልከቱት::

 

ጀዋር መሃመድ እንዳቀደዉ እቅድ ሙስሊምን የተናገረ አንድ ክርስቲያን ቢገኝ አንገቱን መባል አለበት::ጀዋር መሃመድ እንደሚተርከዉ ኦሮሞ በሙሉ ሙስሊም ነዉ::የኦሮሞ ክርስቲያን ህዝብ በርሱ አይን ኦሮሞ አይደለም::ስለሆነም በጀዋር ቲዎሪ መሰረት የኦሮሞ ሙስሊም የበላይነት ሲሰፍን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የበላይነት ይሰፍናል::በዚያም ጊዜ አንድ ክርስቲያን አንድን ሙስሊም ሀረር ላይ ወይም ጎንደር ላይ ቢናገረዉ በቆንጨራ አንገቱን ይመታል::ስለሆነም የኢትዮጵያ ሙስሊም ሁሉ የጀዋርን ትግል መደገፍ ያለበት ጀዋር የሚታገለዉ ለሙስሊም የበላይነት ስለሆነ ነዉ ብሎ በገሃድ ጀዋር ያብራራል::

በተለይም ጀዋር የተዋህዶን እምነት ሊያጣጥል ሲፈልግ በድፍረት ስለ አቡነ ጴጥሮስ ስም መለወጥ ይተርካል:: ሳያፍር በአንደበቱም አማራዎች የአቡነ ጰጥሮስን ስም የቀየሩት ኦሮሞ ስለሚጠሉ ነዉ ይላል:: የኦሮሞ ስም ቀይረዉም አቡነ ጴጥሮስ የሚል የክርስትና ስም አወጡላቸዉ ብሎ በባለጌና ደንቆሮ ልቦናዉ ይጽፋል::አክራሪ ተከታዎቹም አብረዉ ያጨበጭባሉ::ስለ ተዋህዶ የምልኩስና እና የጵጵስና ስም አወጣጥ ህግ አያዉቁም::ወይም ቢያዉቁም ሆን ብለዉ ህዝቡን እስካናከሰላቸዉ ድረስ ሁሉንም ሀሰት በህዝብ መሃል ያሰራጫሉ::

ጀዋር ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አጥር ዉስጥ ዘሎ ለመግባት አላፈረም::ማንን ፈርቶ? አንዳንድ ከንቱ ክርስቲያን ነን ባዮችም እንደ ጀዋር ሁሉ ከክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ይልቅ የጎሳ ደም እና አጥንት እየቆጠሩ የተዋህዶን ቤተክክርስቲያን ዉርደት በደስታ ያርገበግባሉ:: ክርስትና ሲዋረድም ምድረ ክርስቲያን ሰባኪ “ጀዋር እረፍ !” ማለት አልደፈረም:: እዉነታዉ አንድ ነዉ::እንደ ጀዋር አይነት ክፉ እና ባለጌ ሀሳብ ያላቸዉ ሀይሎች እስካሉ ድረስ ኢትዮጵያ መከራዋ ይቀጥላል:: ጀዋርን የሚያቆመዉ አንድ ነገር ብቻ ነዉ::ያም እርሱ በሀይል ሲመጣ በሀይል መመከት::እርሱ ለማዋረድ ሲመጣ እርሱን አዋርዶ መመለሰ::

በአጠቃላይ ጀዋር ለሙስሊም ኢትዮጵያዉያንም ሆነ ለክርስቲያን ኢትዮጵያዉያን ነቀርሳ ነዉ::ምክንያቱም ጀዋር ክርስቲያን በሙስሊም ሜንጫ አንገቱን አስመታለሁ ሲል የሚከሰተዉ ሀገራዊ ብጥብጥ ግልጽ ነዉ::እዚህ ታሪክ ማንሳት እና መተረክ አያስፈልግም::መላዉ መካከለኛዉ ምስራቅ የሚታመሰዉ በጀዋር አይነት ነዉረኛ እና አክራሪ ግለሰቦች ነዉ:: ሌላዉ ቀርቶ ሙስሊም እና ሙስሊም እንኳን ተስማምቶ እንዳይኖር በኢራቅ እና በመካከለኛዉ ምስራቅ አክራሪዎች እያጫረሱት ነዉ::እነጀዋር ደግሞ ጎሳን እና ሀይማኖትን አጣምረዉ የፖለቲካ ስትራቴጅ በመንደፍ ኢትዮጵያን የማይበርድ እሳት ዉስጥ ሊከቷት አስልተዉ እየተንቀሳቀሱ ነዉ::ለዚህ ግባቸዉም የኦሮሞን ህዝብ መያዣ አድርገዉ በመያዝ የኦሮሞ ተቆርቋሪ በመምሰል 48 % ክርስቲያን ኦሮሞዉን በ47% ሙስሊም ኦሮሞዉ ለማስዋጥ ብሎም በኦሮሞ ህዝብ መካከል የርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ አንዱን እምነት ዝቅ አንዱን እምንት ደግሞ ከፍ አድርገዉ እየሰበኩ ነዉ::

ጀዋር ማህመድ እርሱ እራሱ የሚከተለዉ እምነት ከመካከለኛዉ ምስራቅ የመጣ የሙስሊም እምነት ሆኖ ሳለ ክርስትናን ለማጣጣል ግን ከመካከለኛዉ ምስራቅ የመጣ የእስራኤል እምነት በህዝባችን ላይ አማራ ጫነበት ብሎ ያናፋል::ሌላዉ ቀርቶ የጀዋር መሃመድ ስም የአረብ ቃል እና ቋንቋን መዞ የተሰጠዉ ስም ሆኖ ሳለ ሌሎች ክርስቲያኖች ግን በአቡነ ጴጥሮስ ወይም በቅዱስ ጳዉሎስ ስም ሲጠሩ የኦሮሞን ህዝብ ባህል ክርስትና ነጠቀዉ: ኦሮሞ ቋንቋዉን እንዳይጠቀም እና በቋንቋዉ ስም እንዳያወጣ ክርስትና ጫና አድርጎበታል ብሎ ይናገራል::

በርሱ አባባል የመካከለኛዉ አረቦችን ባህል እና ቋንቋ ሁሉ የኦሮሞ አድርጎ ሲቀበል በተቃራኒዉ ግን የመካከለኛዉ ምስራቅ እስራኤሎችን ክርስትና ባህል እና ቋንቋ ግን ባዕድ ነዉ ሲል ይከሳል:: ጀዋር አመለካከቱ የተዛባ እና በጥላቻ የተወጠረ ሰዉ ነዉ::እርሱ እንደሚመስለዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ቂል ወይም ፈሪ መስሎታል:: ዝም ስለተባለ ግን ቀን በቀን የሚዋሸዉ ዉሸት ህዝባችንን ክፉኛ ስነልቦናዉን እየጎዳ ነዉ :: ብሎም ጀዋር ለሚያቅደዉ የርስ በርስ ጦርነት እያዘጋጀዉ ነዉ:: ጀዋር ቁም ሊባል ይገባል:: ክርስቲያኖች ሁሉ በጀዋር አካሄድ መናደዳችሁን መግለጽ አለባችሁ::በተለይም የኦሮሞ ክርስቲያኖች ጀዋር ያቀደዉን የተወሳሰበ ጎሳ እና ሀይማኖትን ያማከለ መርዛማ አካሄድ ቆርጣችሁ ካልጣላችሁ ጀዋር የሚያመጣዉ መዘዝ ብዙ መሆኑን እወቁት::

በተያያዥም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የጀዋር ክርስቲያንን በሜጫ አንገት አስቀላለሁ ፉከራ ጤናማ ያልሆነ መሆኑን አዉቃችሁ በገሃድ ልታወግዙት ይገባል እንጅ ጀዋርን ደግፋችሁ ልትቆም አይገባችሁም:: ጀዋር ገና ምኑንም ሳይዘዉ እንዲህ ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት አንዱን ከፍ ሌላዉን ዝቅ ለማድረግ ካቀደ ጀዋር የሚዘራዉ ፍሬ መራራ መሆኑን በደንብ መረዳት ይገባል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.