በቃፍታ ኹመራ የፀረ ሽምቅ ኃላፊው በ‹‹ከፋኝ›› ጦር ተገደለ፤ ይፋዊ የትጥቅ ትግል ተጀምሯል

ሙሉቀን ተስፋው

ሙሉቀን ተስፋዉ
ሙሉቀን ተስፋዉ

ከትናንት ኅዳር 7 ቀን ጀምሮ እስካ ዛሬ ድረስ በቆላ ቃፍታ ኹመራ እየተካሔዳ ባለው ጦርነት የከፋኝ ጦር በወያኔ አጋዚ ሠራዊት ላይ ድል መቀዳጀቱ ተሰማ፡፡ በርካታ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የወያኔ ሠራዊት አባላት የተገደሉ ሲሆን የጸረ ሽምቅ ኃላፊው ‹‹ጣዕመ›› የተባለው ወያኔም ትናንት በነበረው ውጊያ ተገድሏል፡፡ ጦርነቱ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ተጨማሪ የወያኔ ጦር በ41 ትናንሽና በ7 አውቶቡሶች በወልቃይት አዲረመጽ ወደ ዳንሻ እየሔዱ እንደሆነ ከቦታው የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በወያኔ የጭቆና አገዛዝ የተማረሩ የዐማራ ወጣቶች ራሳቸውን ‹‹ከፋኝ›› የሚል የትግል ስም በመጠቀም ይፋ የትጥቅ ትግል መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ ወጣቶቹ ሁሉም የዐማራ ወጣትና በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ያሉ የዐማራ ተወላጆች የትጥቅ ትግሉን በአጪር ጊዜ በመቀላቀል በሕዝባችን ላይ የወደቀውን ጭቆናና ጭፍጨፋ ልናስወገድ ይገባል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
(እየተካሔደ ስላለው ጦርነት ዝርዝር መረጃዎችን በየጊዜው የምናደርስ መሆኑን እንገልጻለን)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.