የጅብ ጥላ   የራስክን ቁስል ተንከባከብ እንጂ የሌላውን,,,,,,,,, ግርማ ቢረጋ

ethiopia-675-satenaw-news-1ኢትዮጵያ ማለት የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምሳሌ እና መከታ መሆንዋን ዓለም በሚመሰክርበት ዘመን ጥቂት የራሳቸው ቀፈት ካልሆነ በስተቀር የምስኪኑ ህዝብ ረሃብ ፣ስደትና እንግልት የማይሰማቸው እሱ ሳይማር ያስተማራቸውን ደሃ ገበሬ ሊያስቡለት ሲገባ ለሱ ሰደትና እንግልት እንዲሁም ሞት ምክንያት ከመሆን ባለፈ አሳደው ገዳይ እራሳቸው መሆናቸውን እያየን ነገር ግን ለሆዳቸው  ያውም በኩርማን እንጀራ ለሚታገስ ሆድ እራሳቸውን ሸጠው  ባሉ ዘረኛ የትግሬ ቡድን አፈ ቀላጤ ከመሆንክም ባለፈ በተግባር ለምታየው የወቅቱ የሃገራችን የወደፊት እጣ ተግተውና እራሳቸውን አሳልፈው ለመስጠት በሚተጉ ሰዎች ህሊና ውስጥ ጠባሳ ለመጣል መራወጥህ  ያንተን ማንነተ ያጋለጠ ቢሆንም ረሳህን መግዛት ሳተችል የሌላውን ቀላማጅ ጉዳይ በዚህ በትንሹ ጭንቅላትህ  ቦታ ሰጥተከው ማንሸራሸርህ ማንነትክን ፍንትው አድርጎታል። ኧረ አሁንስ ምን ዓይነት ፍጡር እንደሆንክም አልገባኝ አንዴ አፈር ሲሉህ  ገንፎ  ገንፎ ሲሉህ ግን እዳሪ ሆነህ ተገኘህሳ ። ሲጀመር እኮ እሱን ካልሆነ ሌላ ሰው ሲከበር ደስ የማይለው፣በማህበራዊ ሕይወታቸውም ሆነ ባስተሳሰባቸው ተሽለው  የተገኙ ሰዎችን በፀዳ አይምሮ ከመመልከት ባለፈ የሌለና ነገሮችን በመመንዘር  ሁሌም መጥፎ መጥፎውን ፈላጊ ሆኖ ከመገኘት ሌላ ምን አይነት ስንኩልነት ይገኛል ። በርግጥ ጥቂት ግራ የተጋቡ ሰዎችን በዙሪያህ ሰብስበህ ያውም አይደለም መጠጊያ እራሱ ማፈሪያ መሆንህም ያልገባቸው ከታሪክም ሆነ ከነባራዊው ዓለም ሊማሩ የማይቻላቸው ደናቁርታት በዙሪያው ደርድሮ ከመቀባጠር ባለፈ አንድም ነገር ለማይፈይዱ የሌሎችን ጥላ ተከትሎ የአለቆቹ የትግራይ ወያኔ አሽቃባጭ ከመሆን ባላለፈ ቆሻሻ ድረጊት ወስጥ ተዘፍቆ ትችት አይሉት እርምት አራሱ በማያውቀው አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆ ብዕር በመጨበጡ ብቻ አዋቂ መስሎ ለተሰማው ሰው ምን ሊነገረው እንደሚችል ግልፅ ነው ፣ ያው እንግዲህ አካፋን አካፋ ማለት ያስፈልጋል።

አርበኞች ግንቦት ሰባት አላማውን ከማንም ሸሽጎ እንዳልተጓዘ ማንም የሚያውቀው ሆኖ ሳለ የድርጅቱ ማንኛውም ወስጣዊ አሰራርና አካሄድ ለንተ በግልህ ሊነገርህ የምተፈልግና አንተ ወደ ድርጅቱ የመጠጋት አካሄድ ተፈላጊ መሆንህን አሳይቶ የሺዬ እባክህ ናልኝ ሊልህ የምትፈልግ ሞኝ መሆንህንማ ሳስበው ኣይ ፍጡር ያስብላል ።

ደግሞ እኮ ዘረኝነትን ለመስበክ የተከፈተ አፍ መልሶ ለመዝጋት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆን ልነግርህ እገደዳለው፣ ጥቂት ሳንቲም ለብዕር መግዣ  እየሰጡ ወደ ገደል የሚገፉህን ዞር ብለህ የምታይበት ህሊና ይሰጥህ ዘንድ ምኞቴ ነው።

ጀግኖቹ በበረሃ ስለሃገራቸው እየሰሩ ነው ስለዚህ ተወት አርጋቸው በቃ ፣ ለዚህም ደግሞ የትግሬ ወያኔው ቡድን እራሱ ካንተ ጋር ሆኖ እየመሰከረ ነው።

በቃ አታሽቃብጥ ይብቃህ ብዕርህን ወደ ቀድሞ ቦታህ መልሰው እሱ ይሻልሃል ፣ በሁለት ቢላ ለመቁረጥ አትሞክር አያዋጣህምና።

ስቶክሆልም

ኖቬምበር 2016

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.