ኮሎኔል ደመቀ አንድ ሰው አይደለም አሥር ሚሊዮኖች ሆኗል – #ግርማ_ካሳ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

ሕወሃቶች ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱን ወደ አዲስ አበባ ለመውሰድ ዝግጅታቸውን መጨረሳቸው የሚገልጹ አንዳንድ ዘገባዎችን እያነበብኩ ነው። ለኮሎኔል ደመቀ አጋርነት ለማሳየት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ የጎንደር እና አካባቢዋ ህዝብ፣ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ የባህር ዳር እና አካባቢዋ ህዝብ በነቂስ በመዉጣት አስደማሚ እና ታሪካዊ ሰለፎች ማድረጉ ይታወሳል።

ኮሎኔል ደመቀ ነፍስ አጥፍተሃል በሚል ክስ ቀርቦበት ምንም አይነት መረጃ ባለመቅረቡ ክሱ በፍርድ ቤት ዉድቅ መደረጉ ይታወሳል። ሆኖም ግን ህወሃቶች አዲስ ከስ መሰረቱ። “ሽብርተኛ ነው” የሚል።

ኮሎኔል ደመቀ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባል ናቸው። በአገሪቷ ሕግ መሰረት የሕዝቡን ጥያቄ ይዘው የሄዱት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው። ግን ሕወሃቶች ሕግን አክብሮ፣ ከሕዝብ ፊርማ አሰባስቦ፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉዳዮችን ማቅረቡን “ሽብርተኝነት” ይሉታል። ወንጀል የሚባለው ሕግን አለማክበር ነበር። በሕወሃቶች ትርጉም ግን ሕግን ማክበር ወንጀል የሆነበት ሁኔታ ነው ያለው።

በአሁኑ ወቅት በጎንደር እና በጎጃም ከፍተኛ ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነው። በተለያዩ ቦታዎች ጦርነቶች እያየን ነው።

ማንም ኢትዮጵያዊ አገር ወደ ጦርነት እንድትሄድ አይፈለግም። ማንም ጤነኛ የሆነ ሰው ሰላም እንዲኖር ይፈልጋል። ሰለም እንዲኖር ደግሞ የሕዝብ ጥያቄን ማክበር ያስፈለጋል። ከሕዝብ ጋር ያቃቃሩ ነገሮችን ማስተካከል ያስፈልጋል።

አንድ ከህዝብ ጋር ሊያስታርቅ ከሚችሉ ጉዳዪች መካከል እንደ ኮሎኔል ደመቀ ፣ እህት ንግስት ያሉ የትግል ምልክት የሆኑ ወገኖችን መፍታት ነው። እስረኞች መፍታት ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት በጣም የሚረዳ ጉዳይ ነው። በአንጻሩ ግን ኮሎኔል ደመቀን በማእከላዊ ቶርቸር ለማድረግ ወደ አዲስ መዉሰድ ግን ነገሮችን በጣም የሚያባብስ ነው የሚሆነው።

አገዛዙ ዉስጥ ጤነኛ ያልሆኑ፣ ድንጋይ ራስ፣ ደካማዎች፣ የጫካ የኋላ ቀር አስተሳሰብ የተጠናወጣቸውና ዲያብሎስ ራሱ በዉስጣቸው ሰፍሮ እንደ ኳስ የሚጫወትባቸው ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ። ሆኖም ግን ትንሽ ቢሆን ማመዛዘን የሚችሉ ሰዎች አይጠፉም ብዬ ስለማስብ፣ እነዚን ጥቂቶች ነገሮች እንዳይባባሱ የተቻላቸውን እንዲያደረጉ እመክራለሁ። አገር ጦርነት ውስጥ እየተዘፈቀች ነው። የሚያረጋጋ እንጅ የሚያባብስ፣ ወደ ሰላም የሚያመጣ እንጂ ወደ ጠብ የሚወስድ እርምጃዎች መዉሰድ አያስፈለግም።

“ኮሎኔል ደመቀ በአስቸኳይ ይፈታ” የተባለነት አስደማሚው የጎንደር ሰልፍ ለማስታወስ ያህል እንሆ ። ኮሎኔሉ አሁን አንድ ሰው ብቻ አይደለም። አሥር ሚሊዮኖች ነው።

ethiopia-satenaw-news

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.