ብአዲን ለእድሳት ዛሬ ተሰብስቧል! [ልያ ፋንታ]

gedu-satenaw-newsይህ ስብሰባ ትልቅ የውይይት ጦርነት የሚያስነሳ ይሆናል ተብሎም ተገምቷል። የአማራው ጄኔራል ገዱን መንካት የማይሞከር ነው የሚሉ እሳት የሚተፉ ወጣት ለውጥ ፈላጊ ካድሬዎች ተበራክተዋል። በህዋህት ትግራይ ቅኝ አንገዛም፣ ትግራይ ሰራዊቷን ከአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ታውጣ የሚል ጥያቄ በአዳራሹ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል አንዳንድ ሰዎች የብአዲንን አባላት በሙሉ ሲያወግዙ እዚህ ፌስ ቡክ አስተውላለሁ።
ሆኖም ከብአዲን አባላት ውስጥ ወያኔን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ለህዝባቸው ነጻነት የሚፋለሙ ጄግኖች መኖራቸውን ስንቶቻችሁ ታውቁ ይሆን?
ስም ቀይሮ የጄግና ፎቶ ፕሮፋይል አድርጎ ፌስቡክ ላይ መጻፍ ጄግንነት አይደለም።
በእርግጥ ለወያኔ ያደሩ የብአዲን አባላት መኖራቸው ባይካድም ለህዝብ የወገኑ ጄግና፣ ጄግና የሚሸቱ የብአዲን አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።

በመጨረሻም ብአዲን ለመታደስ ጊዜ ማባከኑን ትቶ ሆ ብሎ በአንድ አቋም በመጽናት በህዋህት በግፍ ከሚጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ ጎን እንዲቆም የአማራ ክልል ህዝብ ይፈልጋል።
ቼር ያሰማን
ልያ ፋንታ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.