ሰበር ዜና– በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ በተለያየ መልክ ያደራጁ የዐማራ ታጣቂዎች በአንድ ዕዝ ስር ሆነው በሁለት ግንባሮች ተደራጅተዋል

በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ በተለያየ መልክ ያደራጁ የዐማራ ታጣቂዎች እና የአርበኞች ግንቦት 7 በሙሉ በአንድ ዕዝ ስር ሆነው በሁለት ግንባሮች ተደራጁ በቤተ ክርስቲያን መሃላ ተደረገ።
በሰሜን ጎንደር የሚንቀሳቀሱ አጠቃላይ የነፃነት ኃይሎች በሙሉ በአንድ ዕዝ ስር ሆነው በሁለት ግንባሮች ተደራጅተዋል።እራሳቸውን በተለያየ መልክ ያደራጁ የዐማራ ታጣቂዎች እና የአርበኞች ግንቦት 7 ሁሉም በአንድነት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እና በአንድ ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው ዛሬ መሃላ አድርገዋል።በእዚህ መሰረት በሰሜን ጎንደር ያለው ኃይል ኢትዮጵያ በሚል እና በደቡብ ጎንደር ያለው ቴዎድሮስ በሚል ሁለት ግንባሮች መከፈታቸውን የአካባቢ ሚሊሻ በሙሉ ስራውን እየለቀቀ እየወጣ መሆኑን ኢሳት ራድዮ አሁን ምሽት ላይ ገልጧል።

 

የሁለት አለም ሰዎች ።  [በ ዘነበ ዘ ቂርቆስ]

ለመሆኑ ማነው የተማረው እኛ ነን እነርሱ ?
ከሃገሩ ይልቅ የቆመ ለራሱ
ማንስ ነው አዋቂው ፊደል የቆጠረው ?
ማንስ ነው ምሁሩ ላገሩ የበጀው ?
ማንስ ነው የተማረው ብዙ የተመራመረው ?
ማንስ ነው አገሩን ከጥፋት ያዳነው ?
ማንስ ነው መሃይም ፊደል ያልቆጠረው ?
ማነውስ መሪው ማነውስ ተመሪው ?
አዎ እኔስ ግራ ገባኝ እናንተው ንገሩኝ
ባዶ መሆኔን ሳውቅ በራሴው አፈርኩኝ።

ይህችን አጭር ግጥም የፃፍኩት የግጥም አዋቂ ሆኜ ሳይሆን እንደው በትላንትናው እለት በኢሳት ሬድዮ የአገሬ ገበሬውና የአርበኞች ግንቦት 7 ጦር በቤተ ክርስቲያን ተማምለው የአገራቸውን ሰንደቅዓላማ አንስተው በአንድ ወገን ዘመቻ ቴድሮስ በአንድ በኩል ዘመቻ ኢትዮጵያ ብለው ኢትዮጵያን እስከመጨረሻ ነፃ ለማውጣት ተንቀሳቀሱ ሲባል ሰምቼ በቃ በእውነት ነው የምላችሁ በራሴ አፈርኩ እዚህ ውጭ አገር ተቀምጠን እኛ ደግሞ አብረን ላንሰራ በፌስ ብክ ላይ መማማላችንን ሳይ አይ እውቀት አልኩኝ ። አዎ ወገኔ በውጭ ያለህ ሁለተኛ ምሁር ነኝ እንዳትለኝ ። አዎ የኛ አዋቂነት ታየ ደግሞ እኮ እሄንን ህዝብ እኮ ነው ካልመራነው የምንለው እንኳን ልንመራው ለመመራትም ብቁዎች አይደለንም ። እውነቴን ነው የምላችሁ ቀልዴን አይደለም እዚህ ያለነው ፕሮፋይላችን ላይ የመላእክትን የቅዱሳን የእመቤታችንንና የእግዚአብሔር ምስሎችን እንዲሁም ሙስሊሞችም በበኩላችን የቁራአኑን ጥቅስ የነቢዩ መሀሙድን ስም ይዘን ተማምለን በጋራ ከምንሰራ ይልቅ በጋራ ልንጣላ የቆረጥን ነን አንዳንዴም በፕሮፋይላችን ላይ ያለውን እረስተን የወረደ ስድቦችን የምንሰዳደብ ሰዎች መሆናችንን ሳስብ በእርግጥ ማነው የተማረው ነው ያልኩት ። በእውነት ነው የምለው ቢያንስ ቢያንስ ህሊና ካለን እሄን በታጋዮች ላይ የምናወራውን የዘቀጠ ወሬ እናቁም ባዶ እንደሆንን እንወቅ ። ለማንኛውም እኔ በበኩሌ እግዚአብሔር ይመስገን ብያለሁ አዋቂም እንዳልሆንኩ አውቄአለሁ ። እንዲህም ብዬ የአገሬን ጀግና አወድሼዋለሁ ፦

ዛሬ ግን ተመስገን አልኩኝ
ባገሬም ገበሬ በህዝቤ ኮራሁኝ
ማነው የተማረው ማነው ያልተማረው እሱንም አወኩት
ጥጋብ ያሰከረው ሰላም ከጠማውም እሱንም ለየሁት
ማነውስ መሪው ማነውስ ተመሪው ለይቼም አወቅኩት
ማነውስ ፈሪው ማነውስ ደፋሩ እሱንም አየሁት
ከዚያማ አልኩኝ የሁለት ዓለም ሰዎች ፍፁም ማንገናኝ
ለካስ ከውጭ ያለው የአዋቂ አላዋቂ መሆኑን አወኩኝ

ድል ለአርበኞቻችን
አፍረት ለወሬኞች

ዘነበ ዘ ቂርቆስ

 

amara-mili-456-satenaw-news

15056418_359264931092905_3631113216737228091_n amhara-tewagi-satenaw-news

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.