የወልቃይት ጉዳይ ውሳኔ ለትግራይ ክልል ተሰጠ

gedu-and-abayBBN News Wednesday, Nov. 23, 2016

ለአማራ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀስ ምክንያት የሆነው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የሚፈታው በትግራይ ክልል ባለስልጣናት ውሳኔ መሆኑ ተነገረ፡፡ ይህን ያሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሲሆኑ፣ በአማራ እና በትግራይ ክልል ያለው የወሰን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ለትግራይ ባለስልጣናት ተላልፎ መሰጠቱን ከርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡
‹‹ከወልቃይት ጋር የተያያዘው ጉዳይ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ተከትሎ የትግራይ ክልል የሚፈታው ይሆናል›› ሲሉ የገለጹት አቶ ገዱ፣ በወልቃይት ጠገዴ ወሰን አፈታት ጉዳይ ላይ ህዝባዊ ተሳትፎ ሊኖር እንደማይችል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ይልቁንም ጉዳዩ ለትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ብቻ በኃላፊነት የተሰጠ መሆኑን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያመለከቱት፡፡
ከትግራይ ክልል በተጨማሪ የወሰን ጥያቄውን በመፍታት ረገድ የአማራ ክልል ተሳታፊ ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ጉዳዩን የትግራይ መንግስት ብቻ እንዲፈታው መወሰኑ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላትን አላስደሰተም ተብሏል፡፡ ለወትሮዉ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚቀርበውን የበጀት ዓመት ዕቅድ እና ሌሎች በምክር ቤቱ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በሙሉ ድምጽ ያጸድቁ የነበሩት የምክር ቤቱ አባላት፣ በትላንቱ ስብሰባቸው ግን ሙሉ ድምጻቸውን አልሰጡም ተብሏል፡፡

welkeit

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.