አሥር ነጥቦች መልካም የአዕምሮ ጤና እንዲኖረን ወሳኝ ናቸው ሲል አስቀምጧቸዋል።

የአእምሮ ጤና ማጣት ማንኛውንም ሰው በማንኛውም የህይወት ጊዜ የሚያጠቃ ነው። ሰው በብዙ ምክንያት የተነሳ የአእምሮ ጤና ማጣት ሊያዳብር ይችላል። ከባድ የህይወት ገጠመኞች እንደ የቤተሰብ ችግር ወይም አስቸጋሪ የስራ አጋጣሚ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ የአእምሮ ጤና ማጣት ከኪሳራ፣ ሞት፣ አደጋዎች ወይም ሰዎች ከጦርነት ከሚያገኙት ልምድ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች በዘር የአእምሮ ጤና ማጣት የሚወረሱ ሲሆንና ጭንቀትም አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

ለአእምሮ ጤና ማጣት ያለው አመለካከት ከግዜ በሗላ እየተቀየረ መጥቷል። በዛሬው ጊዜ ብዛት ያላቸው የኖርዌይ ህዝቦች ለአእምሮ ጤና ማጣት ህመም ግልፅና ጥሩ አመለካከት አላቸው። ብዙዎችም የአእምሮ ጤና ማጣት ህመምተኛ ክትትልና እርዳታ ልክ እንደሌሎች የአካል ህመምተኞች በጤና ጥበቃ በኩል ማግኘት አለባቸው ይላሉ። ብዙዎች የአእምሮ ጤና ማጣት ህመምን መዳን ይቻላል ባይ ናቸው።

 አሥር ነጥቦች መልካም የአዕምሮ ጤና እንዲኖረን ወሳኝ ናቸው ሲል አስቀምጧቸዋል።

1. ስለሚሰማህ ስሜት የመናገር ልምድን አዳብር።
2. ለጓደኞችና ለቤተሰብ ጊዜ መስጠት የራስህን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አመለካከቶችን እንድታስተናግድና ለችግሮችህ መፍትሄ እንድታገኝ ይረዳልና ለእነሱ ጊዜ ይኑርህ።
3. በአግባቡ ተመገብ።
4. እረፍት ውሰድ። ይሄም በቀላሉ ከምንሰራው ማንኛውም ዓይነት ሥራ ለጥቂት ደቂቃዎች ዞር ማለትን ይጨምራል።
5. ማንነትህን ተቀበል። ሁላችንም የተለያየን ነን። ልዩነት ውበት ነው እንል የለ….
6. መደበኛ የአካል ብቃት ዕንቅስቃሴ አድርግ።
7. አልኮል የምትወስድ ከሆነ በልኩ ይሁን። በአልኮል የሰጠሙ ችግሮች ተመልሰው ይንሳፈፋሉና…..
8. እርዳታ ሲያስፈልግህ ከመጠየቅ ወደኋላ አትበል።
9. ስትሳተፍበት የሚያስደስጥን ወይም ጥሩ ነኝ ብለህ የምታስብበትን ነገር አድርግ። የራስ መተማመንን ለማምጣትና ለመጨመር ይረዳልና።
10. ለሌሎች መልካም ነገርን አድርግ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.