ቴምር ለጤና ፍቱን መድሐኒት መሆኑን ስንቶች እናውቅ ይሆን ? [ነቢዩ ሲራክ ]

የማለዳ ወግ … አስገራሚና አስደናቂው የቴምር ፋይዳ !
====================================

የጤና ነገር ሲነሳ የምግብ አጠቃቀምን መቆጣጠር ፣ ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ አብሮ መነሳቱ ባይቀርም … አመጋገብን በመምረጥ በአለማችን ቁጥር አንድ የተባሉት ገዳይ በሽታዎችን ማስቆም ባይቻል መከላከልና መቆጣጠር እንደማይገድ ይነገራል ። በአረቡ አለም ለጤን ነት ከሚመከሩት ምግቦች መካከል ቴምር መመገብ በቀዳሚነት ሲጠ ቀስ የግመል ወትትና የግመል ሽንት ለተለያዩ በሽታዎች ፍቱንነት በሰፊ ው ይነገርላቸዋል !15259455_10211611023097100_5945990565133438638_o

የዛሬ መረጃ ቅበላየ የሚያተኩረው ተምር ለጤና በሚሰጠስ ጠቀ ሜታ እንጅ በግለመል ወተትና ሽንት ዙሪያ አይደለም። ቴምር ሙስሊ ማን በጾም ጸሎት ፈጣሪያቸውን ሲማለዱ ውለው ጾማቸው ከመፍታ ታቸው አስቀድመው የሚመገቡት ሀይማኖታዊ ትውፊት ያለው ፍሬ ነው ! ነፍሰ ጥሩዋ መርዬም ምጧ እንዳይጣናባት ተጨንቃ ” ምነው ይህን ሳላይ ከዚህ በፊት በሞትኩ፣ ተረስቸም በቀረሁ “ብላ አማረረ ች ! … ፈጣሪም ከዘንባባው ግንድ ስር አስጠግቶ ካጽናናት በኋላ እንዲህ ማለቱ ይጠቀሳል “And shake the trunk of date-palm towards you, it will let fall fresh ripe-dates upon you.” የተምሩን ዛፍ ወዝውዥው ፣ የበሰሉ ትኩስ የተምር ፍሬዎች ይወርዱ ልሻል !” በማለት ተምር እንድትመገብ እንደመከራት በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በሱራተል መሬም ላይ በቁጥር ከ23 እስከ 25 በግልጽ መቀመጡን ሙስሊም ልሂቃን ይናገራሉ !

የቴምር ጠቀሜታ ለነፍሰ ጥሩዎች ምጥ እንዳይበረታ በቀን ቢያንስ 100 ግራም ቴምር ፍቱን ፈውስ የሚሰጥ በመሆኑ ለነፍሰ ጥሩዎች ይመከራል። ቴምር በአለማችን የብዙዎችን ህይዎት እየቀጠፈ ያለው የድንገተኛ የልብ ድካም Heart Attack ፣ ለደም ብዛት Hypertens ion, ስትሮክ Stroke ፣ ኮልስትሮል Cholesterol ፣ ደም ማነስ anemia ፣ ለነርቨ ዝውውር ፍቱን መድሐኒትና መከላከያ ቁጥር 1 ምግብ መሆኑን በጤና ዙሪያ መረጃ የሚያቀርቡ ድረ ገጾች የሚያሰራጯቸው መረጃዎች ያስረዳሉ !
.
ከላይ ለተጠቀሱት ህመሞች መከላከያ ፍቱን ምግብ የመሆኑ ሚስጥር ተምር በውስጡ በርካታ ጠቃሚ ማዕድንና ንጥረ ነገሮችን መያዙ እንደሆነ ነው ። ተምር በውስጡ ከያዘቸው መካከል በርከት ያለ አይረን ፣ ሴሌኒየም ማንጋኒዝ፣ ሰልፈር ፣ኮፐር ፣ ማግኒዚየም እና ቫይታሚን ቢ6 ንጥረ ነገሮች በውስጡ በመያዙ ነው ። ተምር በባዶ ሆድ የሚወሰድበት ዋናው ምክንያት በውስጡ ካለው ንጥረ ነገር አንጻር ቴምር ምግብ በሆዳችን እንዲዋሃድና አንጀትን የማለስለስ ባህሪ ስላለው ድርቀትን በመከላከል ነው በሚል አረቦች ይመሰክራሉ ።

ቴምሩን በውሃ ውስጥ በመዘፍዝፍ በማሳደር ፣ አለያም ከወተት ጋር በመፍጨት በጠዋት ላይ መመገንብ ለጤና ጠቃሚ ነው ። ለአጥንት ጤናማ እድገትና ጥንካሬና አለርጂክን በመከላከል ቴምርን የሚተካ ከል የለም ። የተመረጠ ቴምር የውስጥ ስሜትን በማነቃቃት
ያለው ጥቅምም ፍቱን ነው የሚሉ የሞከሩትም ጭምር ናቸው 🙂

እኔ ይህችን ታክል መረጃ ካቀበልኩ ሌሎቻችሁ የምታውቁትን መረጃ ጨምሩበት … 🙂

ቸር ይግጠመን !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 19 ቀን 2009 ዓም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.