ወደ አንቃሽ የተንቀሳቀሰው ጦር ሙሉ በሙሉ ወድሞ ውጊያው በድል ተጠናቋል [ሙሉቀን ተስፋው]

satenaw-news-amhara-m34ከትናንት ጀምሮ ሰሜን ጎንደር ወገራ የሔደው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡ ዛሬ ኅዳር 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ እንቃሽ ላይ ሌላ አዲስ ጥቃት መከፈቱን ገልጸን ነበር፡፡ እኩለ ሌሊት ላይ ውጊያው በገበሬዎች ተጋድሎ ድል አድራጊነት የተደመደመ ሲሆን እስካሁን አንድም ሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ፈለቀ አለበል የተባለ የአካባቢው ተወላጅና የመንግሥት ታጣቂ፣ ወታደሮችን እየመራ ሂዶ እንዲመለስ በዘመድ አዝማድ ቢጠየቅም ባለመስማቱ ሊገድሉ ከሔዱ ወታደሮች ጋር አብሮ ተገድሏል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም የወታደሮችም ሆነ የአቶ ፈለቀ አየለ አስከሬን እንዳልተነሳ ሰምተናል፡፡
የወያኔ ወታደሮች የገበሬዎችን መኖሪያና አዝመራ በከባድ መሣሪያ ያወደሙ ሲሆን በሰው ሕይወት ግን ምንም የደረሰ አደጋ የለም ተብሏል፡፡ የአቶ መለሠ፣ የአቶ ደጉ ባዜና የአቶ ያለው ባዜ ቤቶች ከተቃጠሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.