የጥንታዊት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አጭር ታሪክና ሥርዓት [ታሪኩ ዉብነህ ጌታነህ]

ክፍል ሁለት
 
መግቢያ
 
lalibela“ወርኢኩ ጽሑፍ በላዕሊሆሙ  እስመ ትውልድ ትኢብስ እስከ ትትነሣእ ትውልድ  ጻድቅ ወአበሳ ትትኃጉል ወኃጢአት ትትለሑስ እምዲበ ምድር ወኩሉ ሠናኢ ኢይመጽእ”

“ጽሑፉን አነበበኩ፤ ከትውልድ ትውልድ የሚሰራው ኃጢአት በሚነሳው መልካሙ ትውልድ አባሳችን ከምድረ ገጽ ላይ ይደመሰሳል፤” እያለ መጽሐፉ ይጮሃል፤ እዚህ ላይ ጥያቄው መቼ ነው ያ መልካም ትውልድ የሚመጣው ? እንዴትስ ነው ትውልድ መልካም መሆን የሚችለው? አጥፊ ትውልድ መልካም ትውልድን ሊፈጥር አይችልም፤ ማነው መልካሙን ትውልድ ሊያመጣልን የሚችለው? ሃገራችን በጦርነት፤ በመልካም አስተዳደር እጦት እየተሰቃየች ነው፤ በድህነትና በረሃብተኛነት በዋነኛነት ታዋቄ አገር ሆናለች፤ በጎሳ ልዩነት ሕዝብ በጅምላ እየተፈጀ ነው፤ ሕፃናት በጥይት እየተደበደቡ ነው፤ እስር ቤቶች የሰው ልጅ መሰቃያ ሲኦል ሆናለች፤ ይህ ሁሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምን አለች? ይህንን መነሻ በማድረግ የቤተክርስቲያኗን ታሪክ በአጭሩ ይቀርባል፤ ነገር ግን የታሪኩ ሂደት በቅጡ እንዲገባን ታሪኩን ስለክርስትና አነሳስና አመጣጥ እንጀምራለን።

ክርስቶስና ክርስትና

ከሁሉ አስቀድሞ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ክርስቶስና ክርስትና ምን ማለት እንደሁነ በደንብ ከተማረ በኋላ ወደ ነገረ መለኮት ገብቶ የክርስቶስን ባሕርይ ማለትም አምላክነቱንና ሰዉነቱን በቅጡ ማወቅ ይኖበታታል፤ ክርስቶስ ማለት በዕብራይስጥ ወይም በአረማያ “የሺዋ” ወይም “የሆሹዋ” ማለት ነው፤ ይህም ዕብራይስጦች “መሲአህ” ከሚሉት ጋር ተመሳሳይነት አለው፤ ስረ ቃሉም የመጣው “ጃህ” ወይም “ጃሄቫ” ይሆንና አንድ ላይ ተጠቃለው ሲነበቡ “ጄሆቫ” ይሆናል፤ ትርጉሙም “በእምነት መዳን” ማለት ነው። በላቲን “ኪርስቱስ” ሲባል ደግሞ በግሪክ “ክርስቶስ” ይባላል፤ ይህም ማለት ስሙ ወደ ግሥ ተለዉጦ “መቀባት” ይሆናል፤ “ክርስቶስ” በተናጠል ሲተረጎም “አዳኝ” ማለት ነው። “ክርስትና” ማለት ደግሞ ለመዳን ሲል “ክርስቶስን” የተቀበለ ሰው ማለት ነው። የክርስቶስ አመጣጥን ቅዱስ ዮሐንስ በምዕራፉ መጀመሪያ ምስክርነቱን ሲስጥ እንዲህ ይላል።

በመጀመሪያው ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሒር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሒር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሒር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነዉም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች፤ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል፤ ጨለማም አላሽነፈውም [ዮሐንስ 1-1-5]። ከእግዚአብሒር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመስክር ዘንድ ለምስክር መጣ። ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ብርሃን አልነበረም [ዮሐንስ 1፡ 6-8]

ዮሐንስ ስለ “ክርስቶስ” አምላክነት ሲመሰክር “ቃል ሥጋ ሆነ” ይላል፤ እላይ እንደተጻፈው “በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ያም ቃል እግዚአብሒር ነበረ” ከአለ በኋላ “መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሲወርድ አየሁ” አለ። ለዚህ ተአምር ሉቃስ ምስክርነቱን ሲሰጥ እንዲህ ይላል፤

መላአኩ ገብርኢል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሒር ዘንድ ተላከ፤ የድንጊልቱም ስም ማርያም ነበረ። መላእኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፤ ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፤ ጌታ ከአንቺ ር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። እርስዋም ባየችው ጊዚ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና ይህ እንዲት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች። መላእኩም እንዲህ አላት፤ ማርያም ሆይ በእግዘአብሒር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም ትፅንሻለሽ ወንድ ለጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ። እርሱ ታላቅ ነው፤ የልዑል ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል። በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ይነግሳል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም። ማርያምም መለአኩን ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዲት ይሆናል? አለችው፤ መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፤ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሒር ልጅ ይባላል፤ ሉቃስ [1፡27-37] 

የመለኮትን ሂደት በቀላሉ እንመልከት፤ ወረደ ቃል……ማለት ቃል ወደ መሪት ወረደ ማለት ነው። ሥገወ ቃል….ማለት ደግሞ ቃል ሥጋ ሆነ ማለት ነው። ልብሰ ቃል ማለት ደግሞ ቃሉ አካል ሆነ ማለት ነው፤ ሥላሲ ሶወስት ናቸው የምንለው በዚህ ምክናያት ነው፤ ክርስቶስ እነዚህን አዋህዶ አምላክም ሰውም  ሆነ። በሉቃስ ላይ እንደተጠቀሰው ማርያም ከሴቶች ሁሉ ተመርጣ የቃሉ ማደሪያ ሆነች፤ ማርያም ሰው ነች የአዳምም ዘር ስለሆነች የሰው ልጅ የሰራው ኃጢአት ሁሉ አለባት። የክርስቶስም አካል ሰው የሆነው  በእናቱ በማርያም ማህጸን በቃል ተጸንሶ ስለተወለደ ነው። ጥንተ ተሃብሶ የለባትም የሚሉ ክርስቶስም ማርያምም የሰውን ሥጋ አለበሱም ማለት ስለሆነ “ቃ ሌ ወርዶ ሥጋ ሆኖ የስውን ልጅ አድናለሁ” ያለዉን ቃል ያለመቀበል ይሆናል። በዚህ ላይ በዙ ውይይት ተድርጎ አብያተ ቤክርስቲያናት  መሃል ሥነ መለኮት ልዩነት ስለተፈጠረ የም ዕራብና የምስራቅ ክፍል ሆነው ተከፍለዋል። የመጀመሪያው ጉባኤ በ325 ዓመተ ምህረት ሁለትኛው በቻልሰደን በ425 ዓመተ ምህረት ተካሄዶ በሥነ መለኮት ከፍ ያለ ልዩነት ስለተፈጠረ የምዕራብና የምስራቅ እምነት ተከታዮች በመባል ተለያይተው የየራሳቸዉን ሥርዓት በጉባኤ ደንግገዋል። ምንም እንኳን በዓለም አቀፉ ጉባኤ ተካፋይ ባትሆንም  ትዮጵያ የምስራቁን ሥራዓት ተቀብላ ከግሪክ በተረጎመው “ተዋህዶ” በሚለው ሥነ መለኮት እምነቷን አጠናክራ ኖራለች። የተዋህዶ ሥረ ቃል የመጣው ከግሪክ ሆሙሲየስ [homoouisious, born, and being begotten] ከሚለው ነው። እንግዲህ አዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን መለኮትና ፍጥረት እንዲት እንደተዋሃዱ ነው፤ ለምሳሌ አነዚህን የግሪክ ቃላት አሰካኮች እንመልከት፤ “essence” [ousia], “substance” [hypostasis], “nature” [physis], “person” [proson] የተባሉት ቃላት የሚሰጡት ትርጉም የተለያየ ቢሆንም ጸንሰ ኃሳቡ ስለክርስቶስ አምላክነተና ሰውነት ነው። እንግዲህ “ተዋህዶ” ማለት መለኮት ከፍጥረት ክርስቶስን ሆኖ ተወሀደ ማለት ነው።  እንግዲህ አንባቢ ሥለ ሚስጥረ ሥሴ ማወቅ ከፈለገ ሥላሴ ስንት ናቸው? ብሎ መጠየቅ አለበት፤ አብ፤ወልድ፤መንፈስ ቅዱስ ከአለ በኋሏ ወረደ ቃል፤ሥገወ ቃል፤ልብሰ ቃል የሚለዉን በጥንቃቂ መገንዘብ ይኖርበታል። በተጨማሪ ማወቅ የሚያስፈልገው አለም አቀፍ በሆነው ጉባኤ ላየተደነገገውን ሕግ ነው። ለምሳሌ በ325 ንቅያ ላይ በተደረገው ጉባኤ ላይ ኤርያንዝም ወይም የኤርያን እምነትና ትምሕርት በሚባል የታወቀዉን እንመልከት። የኤርያን ትውልደ አገር ሊቢያ በምትባል በሰሜን አፍርቃ የምትገኝ አገር ነው፤ ግን ለትምህርት ወደ ግብፅ ሂዶ ቅስና ተቀብሎ በአልክሳንድርያ ቤተ ክርስቴያን አንጋፋ ከሚባሉት አንዱ የሃይማኖት አባት ነበር፤ በተጨማሪም አሉ ከሚባሉት የቤተክርስቲያን ሊቃዉንት ቀደምተኛ አዋቂ እንደነበር ይነገርለታል፤ ሆኖም ስለ ሥነ መለኮትና ስለክርስቶስ ፍጥረት ያስተምር የነበረው ከክርስቲያን እምነት ዉጭ ስለነበር ተቀባይነተን አላገኝም። ትምርቱ በአጭሩ እንደዚህ ነበር፤ ክርስቶስ ፍጡር ነው፤ ሳይፈጠር በፊት አልነበረም፤ ነገር ግን በእግዚአብሒር ፈቃድ ተወልዷል፤ ሰለተወለደም ፉጡር እንጄ አምላክ ሊሆን አይችልም። እንደማንኛዉም ፉጡር በጎም መጥፎም ነገር ሊሰራ ይችላል። ይህንንም ትምርት ሲያሰተምር ሐዋርያ ዮሐንስን እየጠቀሰ ነበር ። “ሰምታችሁኛል፤ እሄዳለሁ፤ ወደእናተም ተመልሼ እመጣለሁ፤ ከወደዳቹሁኝም ወደ አባቴ መሄዴ ያስተደስታችኋል፤ አባቴም ከእኔ በላይ ስለሆነ” [14፤ 28]። ከላይ እንደተጠቀሰው የኤርያን ትምርት ወረደ ቃል፤ ሥገወ ቃል፤ ልብሰ ቃል የሚለዉን የመለኮት መዋሐድን ይክዳል፤ ስለዚህ  ነው ንቅያ በተተደረገው ጉባኤ ላይ የተወገዘው፤ ይህንን የኤትዮጵያ ተዋህዶ አማኞች እንዲያዎቁት ያስፈልጋል። የኤርያን እምነት ሙሉ በሙሉ አልጠፋም፤ የጆሆባ እምነት ተክታይች ከኤርያን ጋር ይመሳሰላል።

ሁለተኛው የሥነ መለኮት ትምሕርት ደግሞ ኤርያንን አጥብቆ ይቃወማል፤ የዚህም ትምርት አስተማሪ የሶርያው ሊቀ ጳጳስ አፖሊናሪስ ይባልል፤ ሊቀ ጳጳሱ ኤርያንን አጥብቆ ይቃወማል፤ የሶወስቱ ሥላሴዎችን ፍጥረትን ይቀበልና ልብሰ ቃል የሚለዉን ይገድፈዋል፤ ቃል ወርዶ ሲወለድ አምላክነቱ ወደስጋ አልተለወጠም፤ ፍጹም አምላክ ሆኖ ተወለደ እንጂ የሰው አካል ባሕርይ የለዉም ይላል፤ መለኮት ፍጥረትን ስለፈጠረ የፈጠረዉን ፉጡር አልሆነም በማለት ከማኝኛዉም ቤተክርስቲያን የተለየ አቋም ስለወሰደ እሱም እንደ ኤርያን በአጠቃላይ ጉባኤ ተወግዟል፤ ይህም የሆነበት የሰው ልጅ በክርስቶስ ደም ከኃጢአቱ የዳነው መለኮት ከሰው ሥጋ ጋር ተዋህዶ ሰው ሆኖ በስቅለት ደሙን ስለአፈሰሰስ ነው፤ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ምሳሌዎች ስለ ሚስጥረ ሥላሴዎች በሚገባ ያስተምሩናል ። ክሥነ መለኮት ሌላ ብዙ ጥቃቅን ልዩነቶች አ። ነገር ግን እነዚህ ልዩነቶች ሰው ሰራሽ ስለሆኑ የአንድ ሰዉን እምነት ሊቀንስም ሊጨምርም አይችልም፤ የክርስቲያን እምነት መሰረቱ ሥነ መለኮትን መቀበል ነው፤ ሚስጥረ ሥላሲን ጠንቅቆ ከአወቀና የክርስቶስ አዳኝነትን ከተቀበለ በቂ ነው። ሆኖም የካቶሊኮች ሥነ መለኮት ልዩነት ጥልቅ መሆኑን ከግንዛቤ ማስገባት አስፈላጊ ነው፤ ወረደ ቃል፤ ሥገወ ቃል፤ ለብሰ ቃልን ሙሉ በሙሉ ይቀበሉና ማርያም ፍጹም ንጽህት ነች፤ የአዳምም ኃጢአት የለባትም ይላሉ፤ ከአባቷና እናቷ የተወለደችው በመለኮት ኃይል ነው [immaculate conception]፤ እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን ውልደቷን እንጂ ጽንሰቷን አይደለም፤ በአባቷና በእናቷ እንደንኛውም ሰው ተጸንሳለች፤ ነገር ግን ስትወለድ በመለኮት ኃይል ንጽሕት ሆና ወደፊት ለሚወለደው ክርስቶስ ማደሪያ ትሆን ዘንድ  የተመረጠች ልዩ ሰው ነች ይላሉ። እዚህ ላይ የሚያስቸግረው በቡልይም ሆነ በሐዲስ መጻሕፍት በማሕጸን እንዳለች መለኮት ንጽሕት እንዳደረጋት የተጻፈ ነገር የለም፤ በተጨማሪ ደግሞ ክርስቶስ ኃጢአተኛ የሆነዉን ሥጋ ተዋህዶ በደሙ አዳነን የሚለዉን ይፃረራል፤ ይህ የሚያሳየን ማርያም እንደሰው ተጸንሳ እንደ ሰው ተወልዳ ክርስቶስ እንደሰው ሥጋ ለብሶ እንዲወለድ በቡሉይ ተጽፏል፤ ደግሞ እንደ ሰው ሥጋ ለብሶ እንደተወለደ በሐዲስም ተጽፏል፤ ሰለዚህ immaculate conception የሚለው የሥነ መለኮት መገለጫ ከባድ ነው፤ የካቶሊክ ካህናትና ሊቃዉንት ብሉይን እና ሐዲሰን ከማንኛዉም በላይ ከማወቃቸዉም በላይ የሐርያቱ ሥራ የተጀመረው እዚያ ስለሆነ የማርያምን ጽንስትና ዉልደት በመለኮት መሆኑን ማስረዳት አለባቸው፤ ይህ እስከ አልሆነ ድረስ የማርያምን ሰዉነት መቀበል ግዲታ ነው፤ ማርያም ፍጹም ንጽሕት ሰው ነች ማለት የክርስቶስ አካል ክፍል ፍጹም ንጹህ ነው ማለት ነው፤ ይህ ከሆነ ደግሞ ስቅለት ባላስፈለገ ነበር፤ ክርስቶስ የኃጢአኝዉን ሰው አካል ለብሶ በደሙ አድኖቷል፤ ማርያምም እንደማንኛዉም ሰው ድናለች፤ ይህ ከፍተኛ የሥነ መለኮት ልዩነት ነው። ይህንን ከግንዛቤ ከአስገባን በኋሏ ስለማርያም ቅዱስነት በአጭሩ እንመልከታለን።

በተዋህዶ ሃይማኖት ቅድስት ማርያም የተለየ አክብሮት ተሰጧቷል፤ የእግዝአቤሕር እናት [Theothokos] ስለሆነች ወላዴተ አምላክ ትባላለች፤ ይህም ማለት አምላከን የወለደች ማለት ነው፤ አንዳንድ የክርስቲያን ተከታዮች ደግሞ ማርያም የክርስቶስ እናት ነች ይላሉ [Christotokos] ይህም ማለት ማርያም የክርስቶስ እናት እንጂ የእግዝአብሒር  አይደለችም ይላሉ፤ እየሱስ ወይም ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ከተወለደ በኋሏ የተሰጠው መጠሪያ ስሙ እንጂ አምላክነቱንና መለኮቱን አይገልጽም፤ የእግዝአብሒር ቃል ወርዶ በመለኮት ስለተጸነሰ ማርያም የእግዝአብሒር እናት ነች። በቅዱስ ማቴዎስ ላይ እንደተጻፈው  “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል ትርጓሜዉም  እግዚአብሔር ከእኛ  ጋር ነው የሚል ነው። ይህም ማለት ማርያም እግዚአብሒርን ወልዳ ልብሰ አካሉን እየሱስ ብለዋለች። ሥነ መለኮትን ስንመለከት ከታሪካዌ ሄደቱ አንጻር መሆን አለበት–ወረደ ቃል፤ ሥገወ ቃል፤ ልብሰ ቃል። እዚህ ላይ “እየሱስ” ወይም “ክርስቶስ” የስጋ አካሉ መጠሪያ ነው። ማርያም የእግዚአብሔር እናት ስለሆነች ከሁሉ በላይ የተከበረች ነች። በኢትዮጵያ አገራችን አፄ ዘርዓ ያዕቆብ [1436-1468] ስለማርያም ታላቅነት ከፍተኛዉን መስተዋጻኦ ያደረገ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት እንደነበረ ይነገርለታል። ተአምረ ማርያም፤ መጽሐፈ ብርሃን፤ ዉዳሴ ማርያም፤ መጽሐፈ ምላድ፤ ዋላስ ባጅ የተባለው እንግሌዚያዌ የጻፈው  የማርያም “አንድ መቶ አስር ተአምራት” የቅድስት ማርያምን ታላቅነት የሜመሰክሩ ናቸው።

አፂ ዘርዓ ያዕቆብ 366 የያዘዉን ተአምረ ማርያም ከአረብኛ ወደ ግዕዝ በማስተርጎም  ዓመቱን በሙሉ በዕለቱ አንድ ተአምር  እንዲነበብ እና በዕለተ ሰንበት ደግሞ ከቅዳሲ በፊት ኪዳን እንዲደረስ በኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕግ እንዲወሰን አድርል። በተጨማሪ ግብፅ ላይ በነበረው ደብረ ምጥማቅ ገዳም ላይ አክራሪ እስላሞች ጉዳት አድርሰው ስለአጠፉት ሰሚን ሽዋ ዉስጥ ደብሩን አሰርታላቁን “የደበረ ምጥማቅ ጉባኤን” በማድረግ ለሁለት ተከፍለው የነበሩትን ሊቃዉንት አንድ እንዲሆኑ አድርጓል። በዚህ ጉባኤ ላይ ለብዙ ዘመን ያወዛግብ የነበረዉን የሁለት ሰንበት ክርክርን [ሕገ ኦሪት፤ሕገ ወንጌል] በሰላም ስምምነት ላይ እንዲደረስ አድርል። ስምምነቱም  ሁለቱ ሰንበት [ቅዳሚ እና ዕሁድ] ሰንበት ሆነው እንዲከብሩ በቢተክርስቲያኑ ሥርዓት ዉስጥ ተካቷል። ቤተ መቅደስ እና ቤተ ክርስቲያን በመዋሃድ ሕገ ኦሪት እና ሕገ ወንጌልን ኢትዮጵያ እንድትቀበል በሕግ ተወስኗል። ንጉሡ ድጓን፤ ጾመ ድጓን፤ሥዋስው፤ ቅኔ፤ በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኑን ታሪክና  ሥርዓት በልጅነቱ ገዳም ዉስጥ ስለተማረ በአገር ዉስጥ ፈላስፋው ንጉሥ እየተባለ ይጠራ ነበር። በአውሮፓውያን ታሪክ ጳጳሱ ንጉሥ [ Prestor John] እየተባለ ክ14ኛው እስክ 17ኛው መቶ ዘመን ድረስ ይጠራ ነበር፤ ዝናዉም በታሪክ ዉስጥ እስክ አለንበት ዘመን ድረስ የሚነገርለት ታላቅ ንጉሥ ነው።  ዘርዓ ያዕቆብ የላቀ ትምህርት ያለው የመጀመሪያው ንጉሠ ነገሥት ነው። በዘመኑ ቅድስት ማርያም የሰራችውን ተአምራት  ታላቅነት በኢትዪኦጵያ ገኖ እንዲታወቅ ራሱ በጻፋቸው መጻሕፍት ዉስጥ ይገኛሉ። ዘርያዕቆብ ታላቅ ደራሴ ነበር። ስለ ዘርዓ ያዕቆብ ታላቅነት ያስተምሩ የነበሩትና  በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከፍተኛ ዕዉቀት የነበራቸው አለቃ ኪዳነማርያም ሀብቴ ነበሩ፤ ምናልባት ጽሑፋቸው በጉር ሥላሴ ወይም በሰላ ደንጋይ ሥላሴ ወይም በአጃና ሜካኤል ወይም በዶቃቄት ሜካኤል ስለማይጠፋ የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሐፌዎች እንዲፈልጉት ጥቆማ ማድረግ አስፈላጌ ነው። ተከታዩ በክፍል ሰወስት ላይ ይቀርባል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.