የህወሐት በጥልቀት የመታደስ በፎርፌ ተጠናቀቀ፣ከተገመተ ወጭም አልሆነም [ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ]

ህወሐትበህዳር 25 / 3 /2009 ዓ ም አሸካይ የክልሉ ምክርቤት በመጥራት የጥልቅ ተሀድሶ ውጤት  ይፋ አድርጓል ። የክልሉ ፕረዝዳንት አት አባይ ወልዱ የመክፈቻ ንግግራቸው ሲያደርጉ ፣አምና በካቢኔው ላይ ትርጉም ያለው የመስተካከል መስራታቸውን ለምክርቤቱ ገልጸው የነበሩ ቢሆንም አሁንም ባደረግነው ጥልቅ ግምገማ ተነስተን ዳግም የማስተካከል እርምጃ መውሰድ የግድይለናል በማለት፣የእርምጃው መነሻ ሲያብራሩም ፣
1ኛ  ማን የት ላይ ቢመደብ ወጤታማ ይሆናል ፣
2 ኛ  የቶኞች ሴክቶሮች በየተኛው ሙያና የተማረ ሀይልቢመራይሻላልከሚል መነሻ መሆኑን አብሯርቷል።
ይህንን የሚያመለክተው ነገር ካለ ካቢኔም ህዝቡ ካነሳቸው የፖለቲካ ብልሽት ( የመንግስት ስልጣን ለግል ጥቅም ማዋል ፣ የህዝብ ሀብት መውረር ፣ፀረዲመክራሲ እንዲሰፍን ማድረግ እና ጠላትና ወዳጅ በመፍጠር ህዝቡ እርሱ በእርሱ እንዲጣላ የማድረግ እስትራተጅን  ማስተካከል የማያካትት መሆኑን ነው ።ተጠያቂነት ለወረዳና አማራሮች እና ለመንግስት(ፓብሊክ ሰርቢስ )
ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግተሀደሶመሆኑን ያመለክታል።
በዚህም መሰረት  የአምስት ቢሮዏች በአዳዲስ ሙሁራን ተተክተዋል  ተብለዋል ። ከነዚህም ?
የትምህርት ቢሮ
የእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ በአንድ ዘርፍ ኪሮስ ቢተው በማይነካ ፣
የትምህርት ስልጠና እና ተክኒክና ሙያ ቢሮ ፣
የውኃና መአድን ቢሮ
የዋና ኦዲተር ጽ / ቤት  ናቸው ።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት መተካት ያስፈለገው  የጥሮታ ጊዚያቸው በመድረሱ እና በጤና ጉድለት ምክንያት መሆኑን ነው የተገለጸው  ።
ከላይ የተጠቀሱ የቢሮ ሀላፊዏች የተተኩ ለትግራይ ህዝብ አዲስ ሰዏች አይደሉም  ወደ የዳኞች ፕረዝዳንትነት የመጡ ከሁሉም የጸዱ ከመሆናቸው ውጭ ሌሎች ካሁን በፊትም በሙሱናም ፣በኪራይሰብሳቢነት ተሳታፊ የነበሩና የአንባ ገነኑ አቤታዊ ዲሞክራሲ  ታማኞች ካድሬዏች ሆነው ከከፍተኛ አማራር ቦታ ወሳኞች የነበሩ  ናቸው ከአክሱም እና ከመቀሌ ዩንቨርሲቲዏች የመጡ ናቸው ተብሎው የሚነገርባቸውም በየነበሩበት በታ እጅግ ብዙ ሙሱና የተፈጸመበት ሴክተር በከፍተኛ ሀላፍነት የነበሩ ናቸወ።
እነዚህ ለፋሽን ሲባል ህብረተሰብ ለማታለልና የአስተሳሰብ አቅጣጫ ለመቀልበስ በደጉተሮች  ሙሁራን መጥሉን ሊባልላቸው ነው እንጅ ፣ በህወሐት አመራር ውስጥ  ከ12 በላይ ደጉተሮች  ግማሾቹም አሁንም በስልጣን ላይ አሉ ፣ በሁሉም ሴክቶሮች በከቢኒ ደረጃ ከ26  በላይ ማስተርስ ዲግሪ የነበራቸው ቡቁ ሙሁራኖች በተለያዬ ወቅት ቢሮ ሀላፊዎች ወይ የካቢኔ አባላት   ነበሩ ፣ነባሩ አባታዊ የህወሐት አመራር ግን የፓርቲ አባል አልሆናችሁም በማለት እነሱን በመባረር ቢሮዏች ወይ ካቢኔ በታማኝ ካድርዏች ተይዞ ነው የቆዬው  አሁንም ካቢኒ እነሱ ናቸው  ። እነዛ ቢሮ ሀላፊዏች የነበሩ ቅን ሙሁራን አሁንም አሉ  ዳኛ ቢገኝ ንሮ ለምስክርነት ሊቀርቡ ይችላሉ ። ሌላስ በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ክልል በተለያዩ ቢሮዏች በመቶ የሚቆጠሩ በተለያዩ ሴክተር በሙያቸው የሚሰሩ ደጉቶሮች  ማስተርስ የተማሩ ተመራማሪዏች ፣ምንም አቅም በሌላቸው  ካድሬዏች እየመሩዋቸው ይገኛሉ ።
ስለዚህ ህወሀት እች አገር በሳይንስ ልትመራ ቢፈልግ ንሮ  ከዲግሪ እስከ ፕሮፌሰር ያለው በሽ የሚቆጠር  ሙሁር በየሙያው ቢያሰማራው ንሮ እቺ  ክልል  በተቀየረች ነበር ።  ግን እንዴት ብሎ በእወሐት ላብላቶሪ ተመርምሮ በመርፌ አይን ካላለፈ ዘበኛ ሆኖ ሊጠብቃቸው አይችልምና ።
ህወሐት  አሁን ተገዶ በህዝብ ተጽእኖ ሙሁራን ወደስልጣን አመጣለሁ ቢልም  ሊያደርገው አይችልም ከተፈጠረበት ጀሞሮ በፕሮግራም ደረጃ በአንደኛ ጠላትነት ፈርጆዋቸው  የእተጓዘ  የመጣ ነው ።
በመሆኑም እነዚህ ሰዏች  በትግራይ ህዝብ የሚያመጡት ፍትህ አይኖርም  ።
በመሆኑም ይህ የትግራይ  ካቢኒ የማስተካከያ ጥልቅ ተኃድሶ በመያያዝ ስንመለከተው ከነበረው የበሰበሰ አማራር በጥልቅ ተሀድሶ ከነበራቸው ሀላፍነት የተገለሉ  ሁለት ብቻ ናቸው   ሌሎች ግን ታማኞች በመሆናቸው ከአነድ ቢሮ ወደ አንድ ቢሮ  እየተዘዋወሩ የመጡ ናቸው ።  ነበርና የለሸቀ የትግራይ ካቢኔ አልተነካም  ከ90% በላይ በቦታው ነው ያለው ።
ያምሆኖ ይህ የካቢኔ ምልመላ ማን የት ላይ ቢመደብ የተሻለ ውጤታማ ይሆናል ነው መነሻው  እንጅ እያንዳንዱ የካቢኔ አባል በነበረው  ሀላፍነት ተመሰርቶ ተጠያቂ በሚያደርግ  አኳኃን አይደለም ሊስተካከል የተደረገው ።ይህ ከሆነ በጥልቅ መታደስ ህወሀት  ተደሰ ወይስ ከማጡ ወደ ድጡ  ገባ ?  ለሚለው ጥያቄ መልሱ የህወሐት በጥልቅ ተሀድሶ በፎርፌ ወጣ ነው መባል ያለበት ።
ያሁሉ ችግር ይደረደር የነበረው ( የመንግስ ስልጣን የግልመጠቀምያ በማድረግ ፣ ኪራይ ሰብሳቢነት ፣ኔትዏርክ ፣ህዝብን አለመገልገል በአጠቃላይ የመልካም አስተዳደር ችግር ተብሎ ተብሎ የተገመገመው ተጠያቂው ታድያ ማን ሆነ ?? ይህ ነው የውሸት ጥልቅ ተሀድሶ  የሚባለው ፣
ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂው ከፍተኛ አማራር እና የህወሀት አመራር መሆነ በየደረጃው  ባካያዳቸው ስብሰባዎች ሲገለጽ ሰምተናል  በተለይ  ዶ / ር ደብረጽዮን አጽንኦት ሰጥተው በተደጋጋሚ በኢቢሲ ሲገልጹ  ሰምተናል ።በራሱ ሳንባ የሚያስተነፍሱ  የራሱ ሚዲያዏች ችግራችን እስከአሁን  ሳትነግሩን በመቆዬታችሁ እናንተም ከልማታዊ ጋዜጠኝነት አፈንግጣችሁ  ቆይታችኃል እና ተሎ ብላችሁ ወደ ልማታውነት ተመለሱ ካባችሁ እራቃታችሁ እንዳላያችሁ ብሎ ገለጻቸው ። ይህ አገላለጽ ለነሱ ምን ማለት መሆኑን ሰምና ወርቁ አብጠርጥረው ስለሚረዱት ።የካቢኔው ማስተካከያ ከተደረገ ከተወሰነ ደቂቃ በኃላ የትግራይ ክልል ካቢኔ በጥልቀት መታደሱን አበሰሩት ።
የድርጅቱ አፈቀላጤዏች  በየጎደናው በህቡእ መልምለው በማስቀመጥ በመጠየቅም ይህንን በጥልቀት መታደሱን አበሰሩት ። የህወሐት አፈቀላጤዏችም በመጠየቅ ይህንን በጥልቀት መታደስ ደስ  እንደአሰኛቸው እና ይህንን የአብነትነት ተግባር በክልሉ ካቢኔ ብቻ ታጥሮ መቅረት የለበትም ፣እስከ ታች መውረድ አለበት ተብሎ እንዲስተጋባ ተደረገ
ልማታዊ ጋዜጠኛ ከዚህ የተለዬ ሀሳብ ያለው ፣ በጥልቀት  መታደስ  መታደስ ማለት ይህ አይደለም  ስለሆነ ህወሐት አልታደሰም ። የመንግስት የክልል ካቢኔ አልታደሰም ፣ በሙሱና የተዘፈቀው የካቢኔ አባልና የህወሐት አመራር ተጠያቂ ተደርጎ ህግ ፊት መቅረብ አለበት የሚል የህዝብ ሀሳብና ፍላጎት ማስተናገድ አልቻለም ። የተለዬ ሀሳብ ያለው ዜጋ ሀሳቡን የመግለጽ መብት አልተፈቀደም ። የተከለከለ ነው ።በዚህም መመሪያ ልማታዊ ጋዜጠኛ ህወሐት ሊነገርለት የሚፈልገው ብቻ እየፈለጉ ድጋፉን እንዲነግራቸው  እና ለህወሐት አማራር እንዲታጭም  ሪከርድ ይያዘለታል ።
በእርግጥ የህወሐት ኢህአደግ  አማራርና ካድሬዎቹ   ሊታደሱ    እንደማይችሉ   ቀድሞውም የታወቀ ነበር ።  በትክክል በጥልቀት ሊታደስ ከሆነ ከመሰረቱ የላሸቀው  የፓለቲካ አስተሳሰቡና ፖሊሲው መቀየር አለበት ።
የመንግስትን ስልጣን የግሉን መጠቀምያ ከማድረግ ሊቆጠብ አይችልም ።ከሙሱና ውጭ መኖር ፣ያለአድልዏ ፣አንዱን ጎድቶ ሌላውን ከመጠቀም ውጭ የላሸቀው ፓርቲው ከነ የተባላሸ አስተሳሰቡ ሊያስቀጥል አይችልም ። ከዚህ ውጭ ህልውና የለውም  ።
ህወሐት ኢህአደግ  የህዝቡን ዲሞክራሲ ሳያፍን ፣የፈለገውን እንዳይናገር በነጻነት እንዳይእንቀሳቀስ  ሳይጨቁን በስልጣን መኖር አይችልም ምክንያቱ ከአቤታዊ ዲሞክራሲና የኮሚኒስት አስተሳሰብ ከዚህ ውጭ ሊናገር አይችልምና  ።
ምክንያቱም ይህ አስተሳሰብ አንዱ ጠላት ሌላው ወዳጅ ብሎ ሳይፈርጅ ህልውና የለውም ።አንድ አንድ ወገኖች የኢህአደግ አስተሳሰብ ለመላው ህዝባች ወዳጅና ጠላት ፣ማኸል ሰፋሪ ብሎ ጸረ ህዝብ የሆነ አስተሳሰብ እንደመኮነን  ፈንታ ጣታቸው ለአንድ ቢሄር ህዝብ በመቀሰር እንደጠላት በማየት ጊዚያቸው ያጠፋሉ ። ምክንያቱ ይህ ሀይል ለዜጋው በዜግነቱ ተቀብሎ ይጠቅመኛል የሚለውን አመለካከት ይዞ እንዲጓዝ የሚፈቅድ አይደለም አቤታዊ ዲሞክራሲ ።
አቤታዊ ዲሞክራሲ ለጥቂቶች ለህወሐት ኢህአደግ አማራርና ካድሬዏቻቸው ፣ሸሪኮቻቸው  ገነት ፣ ለብዙሀን ጭቁኖች ጋህነም ( ጨለማ )በማድረግ ነው ህልውናው  የሚረጋገጥና ቀጣይነት የሚነረው ።
አቤታዊ  ዲሞክራሲ በህዝቦች  እኩልነት ላይ የሚመሰረት አመለካከት አይደለም ። አቤታዊ ዲሞክራሲ  የዜጎች እኩልነት ፣የሀይማኖት እኩልነት የማይቀበል የግለሰው መብት ፈጽሞ የማያምን ፣ዜጎች  በሀገራቸው፣በዜግነታቸው ተፈቃቅረው እንዳይኖሩ  ጠላትና ወዳጅ ብሎ  ተከፋፍሎ እንዲኖር ይፈልጋል ።ከሌሉም ይፈጥራቸዋል ።
ይህንንም ካልተከተለ ጥልቅ ተሀድሶ ይኖራል ።ጥልቅ ተሀድሶ ካለ በስልጣን የባለገ የመንግስት ስልጣን ለራሱ የግል  ጥቅም ያዋለ ይባረራል፣ህግ ፊት ይቀርባል።
እንዲህ ከተደረገ የሀሳብ ነጻነት ፣ህዝቡ ለበዳዮች ጮኽ ብሎ ለመናገር ወደ ህግ ፊት ማቅረብ አቅም ይኖረዋል ።
ይህንን ከተደረገ ፍትህን ይሰፍናል  ሙሶኞች  መደበቂያ አያገኙም  ምክንያቱም  ህዝብ ነጻ ወጥቷል  ይህንን ከሰፈነ መልካም አስተዳደር  ይሰፍናል ።፣ የህዝቦች አንድነት መፈቃቀር ፣ የቢሄር ቢሄረሰብ እኩልነት ይረጋገጣል የህወሐት ኢህአደግ ጠባብነትና ትምክህት  መፈልፈያ ቦታ ይቀበራል ( ይደርቃል ) ።
የህወሐት ኢህአደግ  አማራር ከላይ የተጠቀሱትን ስለ
ማይፈልግ ነው መታደስ ያለቻለውና በጥልቅ መታደስ በፎርፌ ወጣ ያልኩበት  ። ከመፎከርና ከመዘመር አልፈው መታደስ  ቢፈልግ ንሮ   ሙሶኞቹ  ከስልጣን በማስወገድ ህግ ፊት ማቅረብ  ይቻል ነበር ፍትህ ያጣ ህዝብፍትህ እንዲያገኝ  ያደርግ ነበር ።
ህወሐት ኢህአደግ  መታደስ ቢፈልግ ንሮ አጥፊዏች የህዝብ ሀብት የወረሩ ፣በሀገር ደረጃ ያሉት ትላልቅ ከተሞች ያሉ ምርጥ መሬት እየቸበቸቡ  የሸጡ  ምንጩ ያልታወቀ ቀዋሚና ተንቀሳቃሲ ሀብት የደለቡ  በከባድ መቅጣት ይችል ነበር ። የህወሐት መሪዏች የህዝብ ሀሳብና ፍላጎት  ተግባራዊ ለማድረግ ቢፈልግ ቢፈልግ ንሮ ፣በጥልቀት መታደስ ቢፈልጉ ንሮ  ከክልሉ ፕረዝንዳንት  አበይወልዱና ምክትሉ አዲስ አለም ባሌማ  ሌሎችም መጀመር ነበረበት ። ህዝቡ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚፈልጋቸው  እነማን መሆናቸው ህወሐት በሚገባ ያውቃል  ።በሰላዮቹና በካድሬዏቹ መረብ በሚሰበሰበው መረጃ  ያውቃል ። የትግራይ ህዝብ ከህጻን እስከሽማግሌ  ከስልጣን ሊወገድለት  የሚፈልጋቸው ባለስልጣናት  ፣ አባይ ወልዱን አዲስ አለም ባሌማን ፣ኪሮስ ቢተውን ፣ አለም ገብረዋህድን  ወዘተ  ናቸው ።
።ይህ ጥላቻ ማንም ሰው በጎዳና የሚናገረው ነው ። ነገር ግን የህወሐት አመራር  ህዝቡ ፍትህ ሰላም መፈቃቀር ፣ከጥላቻ ነጻ የሆነ መንደር  ህዝቡ ሊመሰርት  የህወሐት አመራር ፍላጎት አይደለም ። በተለያዬ መንገድ ራሱ በሚቆጣጠራቸው  መገናኛ ውሼት በመግዛት  ህዝብን በመደናገር ፣ በከፋፍለህ ግዛ ስልቱ  መኖር የመረጠ ፓርቲ ( ስርአት ) ነው ።
ከዚህ በመነሳት ነው ህዝቡ በጥልቀት  መታደስ ሳይጀመር  በፖርፌ የከሸፈ ፣በመፎከር ነው እየመራው የሚገኜው ።
የትግራይ ህዝብ በትግርኛ  እንዲህ ይላል ፣
ናይ ሎብዘመን ጥልቅ ተሀድሶ  ከም ሕማቅ ስዋ ነፊሳ  እያለ ይገኛል
( የዘንድሮ የህወሐት ኢሀአደግ ጥልቂ ተሀድሶ እንደተበላሸ ጠላ ነፍሷል ወይ ተባላሽታል !!!!
ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ፣
29  / 3 / 2009  / ዓ  ም

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.