የጣና በለስ ታሪካዊ የልማት ፕሮጀክት፤ ከመፈራረስና ውድመት እስከ መሸጥ የጣና በለስ ታሪካዊ የልማት ፕሮጀክት፤ ከመፈራረስና ውድመት እስከ መሸጥ

• የጣና በለስ ፕሮጀክት አጭር ታሪክ
• የጣና በለስ ፕሮጀክት ልማታዊ ግቦች/ህልሞች ምን ነበሩ?
• የጣና በለስ ፕሮጀክት በአፄው ስርዓት ተጠንስሶ፥ በደርግ አብቦ፥ በህወሀት/ኢህአዴግ እንዴትና ለምን ፈራረሰ?
• ዛሬ በጣና በለስ ላይ የተጋረጠው አዲስ እና አስደንጋጭ አደጋስ ምንድን ነው? መፍትሄውስ?

መግቢያ

የአባይ ተፋሰስ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ተፋሰሶች የላቀ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለው ልዩ ቦታ በመሆኑ በርካታ ጥናቶች ተደርገውበታል:: የመጀመርያው የአባይና ጣና ዳሰሳ ጥናት የተካሄደው በእንግሊዞች ነበር:: ቀጣዩ ዝርዝርና ጥልቅ ጥናት የተካሄደው በአጼ ኃይለሥላሴ ልዩ ጥያቄ ሲሆን ምክንያቱም አወዛጋቢው የእንግሊዝና ጣልያን በ1925 ዓ.ም የተፈራረሙት ውል ነበር:: ይህ የወራሪ ሃይሎች ውል ጣልያን ኤርትራ የሚገኘውን ቅኝ ግዛቷንና ሶማሌ ያለውን ቅኝ ግዛቷን ለማገናኘት በኢትዮጵያ ላይ የባቡር ሀዲድ ግንባታ እንድትሰራ የሚፈቅድ ሲሆን እንግሊዝ ደግሞ በበኩሏ ጣና ኃይቅ ላይ ግድብ ገድባ ውሃውን በወቅቱ ቅኝ ግዛቷ ወደነበረችው ሱዳን እንድትልክ የሚያደርጋት ነበር::

ይሄው ውል የተንኮልና የኮሎኒያሊዝም ዳርዳርታ መሆኑ የገባቸው አጼ ኃይለሥላሴ፣ ለጣልያንና ለእንግሊዝ መንግስታት አለመስማማታቸውን አሳውቀው በልዩ ፍጥነት ከአሜሪካ ጋር መደራደር ጀመሩ:: ድርድሩም አሜሪካውያኑ ወደሀገራችን መጥተው የጣና ኃይቅ ዳርቻ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመሆን ግድብ እንዲሰሩ ፣ ከግድቡም ተለቆ ወደ ሱዳን የሚፈሰውን ውሃ የሱዳን ባለትልልቅ እርሻ ባለቤቶች ውሃውን በገንዘብ እንዲገዙ ስምምነት ተደርሶ አሜሪካውያኖቹ ስራ ጀመሩ:: ከስራው በፊትም ተፋሰሱ እንዲጠና ኢትዮጵያ በመጠየቋ ኒውዮርክ የሚገኘው ጂፒ ኋይት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተፋሰሱን ጥናት ማጥናት ጀመረ:: ከ1930 – 1934 እ.ኤ.ኣ ይሄው ኩባንያ የጣናና የዓባይ ተፋሰሶችን ሙሉ በሙሉ አጥንቶ ፣ለኢትዮጵያ መንግስት ያስረከበ ሲሆን፤ ጎን ለጎንም የአስር ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በመቅረጽ በጣና ሓይቅ ዙርያ የታሰበውን የግድብና የውሃ ልማት ፕሮጀክት ለመተግበር እንቅስቃሴ ጀመረ:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን እንግሊዝ ፕሮጀክቱን አስመልክቶ ክፉኛ ተቃውሞዋን አሰማች:: ጥቂት ቆይቶም ጣልያን ኢትዮጵያን ወረረች:: ሊሰራ የታሰበውም የጣና ተፋሰስ ልማታዊ እንቅስቃሴ ተቋረጠ:: አሜሪካዊው ኩባንያም ኢትዮጵያን ለቆ ወጣ::

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.