የኢትዮጵያ ካርታ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ዘመን በ1916 ዓ.ም

ይህ የኢትዮጵያ ካርታ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ዘመን በ1916 ዓ.ም. የነበረ ሲሆን፣ የዛሬዪቱን ኢትዮጵያ ገጽታ ይመስላል፤ በወቅቱ አልጋ ወራሽ የነበሩት በልዑል
ራስ ተፈሪ መኰንን (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) ቤተ መንግሥት ውስጥ ተሰቅሎ ነበር፡፡ በብራና ላይ በተሣለው ካርታ ላይ የንግሥቲቱና የአልጋወራሹ ፎቶዎች፣ ሞአ አንበሳ (የአሸናፊው አንበሳ ምስል) ሲገኝበት፣ የካርታው መግለጫ የተጻፈው በአማርኛ ቋንቋ ብቻ ነበር፡፡

በወቅቱ የኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች በሙሉ መጠሪያቸው በቅኝ የያዙዋቸው አገሮች ስም የታከለበት ነበር፡፡ በሰሜን የጣሊያን ግዛት ኤሪጥሪያ፣ በምዕራብ የእንግሊዝና የምስር ሱዳን፣ በደቡብ የእንግሊዝ የምሥራቅ አፍሪካ ግዛት፣ በደቡብ ምዕራብ የሱማሊ አገር የጣሊያን ግዛት፣ በደቡብ ምሥራቅ የሱማሊ አገር የእንግሊዝ ግዛት፣ በምሥራቅ የሱማሊ አገር የፈረንሳዊ ግዛት፡፡ ከ‹‹Vault Map Collection›› የተገኘ፡፡

(ሔኖክ መደብር)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.